ነፃነት ያጣ ነፃነት ወዳለበት አገር ሲሰደድ ነፃነት አመጣን ያሉት ወያኔዎችም ለምን አብረው ተሰደዱ?
ዋለልኝ መኮንን
ላለፉት 21 አመታት በኢትዮጵያ የአገሪቱን ሥልጣን በሙሉ ጠቅልሎ የያዘው የማፊያው የወያኔ አገዛዝ የአንድ ብሄርን የበላይነትን ለማረጋገጥ የስልጣን እድሜውን ለማራዘምና በቡድን ተደራጅተው የኢትዮጵያን ህዝብ ሀብትና ንብረት ለመዝረፍ ሲሉ በአገራችንና በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ባደረሱት ፖለቲካዊ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውሶች የተነሳ ህይወታቸውን ለማዳንና የተሻለ ህይወት ፍለጋ ለማግኝት በብዙ መቶሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን አገራቸውን ጥለው በየብስ፤ በምድርና በባህር አያቋረጡ ወደተለያዪ አገራትና አለማት ተሰደዋል አሁንም እየተሰደዱ ይገኛሉ:: የሚሰደደውም የህዝብ ቁጥር ከለት ወደለት እጅግ እየጨመረ እንደመጣ ጉዳዩ ያሳሰባቸው የተለያዩ አለማቀፍ ተቃማት ገልፅዋል::
የኢትዮጵያ ህዝብ በግለሰብና በቡድን ደረጃ ከሚደርስባቸው ፖለቲካዊ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ምስቅልቅሎች ለማምለጥና ህይወታቸውን ለማዳን የህይወትና ከፍተኛ የገንዘብ መሰዋትነት ከፍለው ሀገራቸውን የተወለዱባትንና የደጉባትን ቀያቸውን ሀብት ንብረታቸውን ቤተሰቦቻቸውን በግዴታ ጥለው እየሸሹ ይገኛሉ:: ይህንን ሁሉ መስዋትነት ከፍለው ህይወታቸውን ለማትረፍ በድንበር መሸሽ ከሞከሩት ውስጥ ግማሹ በመንገድ ላይ በወያኔ ወታደሮች ይያዛል ግማሹም በምግብና በውሀ እጥረት ህይወቱ ያልፋል ግማሹ ባህር ውስጥ ሰምጦ ይቀራል እጅግ በጣም ጥቂቱ እድል ቀንቶት ከሀገሩ ወጥቶ ለሌላ መከራ ሌላ አገር ይደርሳል (ከሀገር መሰደድ እድለኛ ባያስብልም ህይወትን መቆየት ግን እድለኛ ያስብላል):: ትንሽ የኢኮኖሚ አቅም ያለውና በስደት እጅግ የተዋጣለት ደግሞ አውሮፓና አሜሪካ ይደርሳል::
የህንን ሁሉ በሀገራቸውና በስደት ጉዞ ላይ የሚያጋጥማቸውን መከራ አልፈው በተለያዩ አገራት ከደረሱም በሁዋላ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን አምባገነንና ለስደትና ለባርነት መንስኤ የሆናቸውን የወያኔን የማፍያ ቡድን ከስልጣን አስወግዶ ሁሉም ሰው እኩል የሚሆንባት የህግ የበላይነት የሰፈነባት የአመለካከት የመፃፍና የመናገር ነፃነት የተረጋገጠባት የሀብት ክፍፍል ሚዛናዊ የሆነባት ሰብአዊና ተፈጥሮአዊ መብቶች የሚከበርባትን የጋራ ኢትዮጵያን ለመመስረት በሚደረገው ትግል ውስጥ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በመሳተፍ ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ:: ይህንንም ትግል ውጤታማና የተጠናከረ ለማድረግ በተለያዩ የተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅቶችና ማህበራዊ ተቃማት ውስጥ በቀጥታ በመሳተፍ በእውቀታቸውና በጉልበታቸው በመርዳት በገንዘብ ማዋጣትና በማሰባሰብ ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ:: በአንፃሩ ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚደርስባቸው ኢሰብአዊና ኢተፈጥሮአዊ ግፎች አምልጠው በተለያዩ በውጭ አገሮች በስደት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሚደርጉት ከፍተኛ የፍትህ የኩልነትና የአገር የማዳን የተጠናከረ ትግል እጅግ በጣም ያሳሰበው የወያኔ የማፊያ ቡድን የህዝብን ትግል ለማጥፋት መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል::
የወያኔው ቡድን በመጀመሪያ ያደረገው ልክ እንደነሱ እኩይ ተግባር ካላቸው ከአምባገነን ጎረቤቶቹ አገሮች ጋር ስምምነት ፈጥሮ ምንም አይነት የተቃዋሚ ቡድን መጠለያ እንዳይሰጣጡ መማማል ነበር( እንደውም ለሱዳን መንግስት የወያኔ መሪ መሬት እጅ መንሻ አቅርባል):: የዚህ ስምምነት አባል አገሮች ልክ እንደወያኔ መሪዎች ህዝብን አፍነው የስልጣንና የዘረፋ ዘመናቸውን ለማራዘም የተጠቀሙበት ነው:: ሁለተኛው የወያኔ ቅጥፈት ደግሞ ለምዕራቡ አገሮች ምንም አይነት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈፅሙ ኢሰብአዊና ኢተፈጥሮአዊ ድርጊቶች የሉም ብሎ በምዕራቡ አገራት የሚደርጉትን ከፍተኛ የፍትህ የኩልነትና የአገር የማዳን የተጠናከረ ትግል ለማዳፈን መሞከር ነበረ::የምዕራብ አገሮች የወያኔ የማፊያ ቡድን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚፈፅማቸውን ኢሰብአዊና ኢተፈጥሮአዊ ድርጊቶች ጠንቅቀው ቢያውቁትም በምስራቅ አፍሪካ ጥሩ ተላላኪያቸው ስለሆነ ከወረቀት ያለፈ እርምጃ ለመውሰድ አልፈለጉም:: ሌላው አሁን ወያኔ እየሞከረው ያለውና በጣም አደገኛውና በጋራ ልንታገለው የሚገባው እንደተኩላ የበግ ለምድ ለብሰው በአውሮፓና አሜሪካ ወያኔ አምባገነን ቡድን ሊፈልጠን ሊቆርጠን ሲል ሸሽተን ነው የመጣነው ብለው የጥገኝነት ጥያቄ አቅርበው ፍቃድ አግኝተው የሚኖሩ ነገር ግን ኢትዮጵያን የሚደርጉትን ከፍተኛ የፍትህ የኩልነትና የአገር የማዳን የተጠናከረ ትግል ለመበታተንና ለማጥፋት የተለመደ የመከፋፈል መሰሪ ስራውን እየሰራ ይገኛል::
አነዚህ ከኢትዮጵያ ህዝብ መሀል የወጡ ጭንቅላታቸው ሆድ የሆነባቸውና አርቆ አስተዋይነት አይምሮ ያጡ የወያኔ አሽከሮችና የአንድ ብሄር የበላይነት ናፋቂዎችና የበታችነት ስሜት ያናወዛቸው ጠባብ ትምክህተኞች በአውሮፓና በአሜሪካ እየተንቀሳቀሱ በወያኔ ፊት እውራሪነት ኢትዮጵያ ውስጥ በደረሰባቸው ኢሰብአዊና ኢፍታዊ ግፎችና ጭቆናዎች ካገሩ ከቀየውና ከቤተሰቦቻቸው በግዳጅ ሸሽተው የወጡትንና ለነፃነፃነታቸው የሚታገሉትን በማስፈራራት አሁን እየተደረገ ያለውን የነፃነት የፍትህ የኩልነትና አገር የማዳን እንቅስቃሴ ለማክሸፍና ለማጥፋት ሲሮጡ ተስተውለዋል:: ከዚህም አልፎ ቤተሰቦቻቸውን ማስፈራራት በማሰቃየት አገር ቤት ያለውን ንብረቶቻቸውን በመዝረፍ ሌላ የወያኔ ግዛት እየፈጠሩ ነው:: እነዚህ በአሜሪካና በአውሮፓ የሚገኙት ሆድአደሮች ካለማፈራቸው የተነሳ የተለያዩ የወያኔን የስልጣንና የዘረፋ እድሜ የሚያራዝሙ በተቃራኒው ከሀገራቸው በደረሰባቸው ኢሰብአዊና ኢፍታዊ ድርጊት ሸሽተው ያመለጡትንና ለየነፃነት ለፍትህ ለኩልነትና አገር ለማዳን የሚታገሉትን አንገት ማስደፊያና ተስፋ ማስቆረጫ ስራዎች እየሰሩ እንደሆነ ሁላችንም እናውቃለን::
አሁን በጋራ ተሰባስበን እነዚህን ጭንቅላታቸው ሆድ የሆነባቸውና አርቆ አስተዋይነት አይምሮ ያጡ የወያኔ አሽከሮችና የአንድ ብሄር የበላይነት ናፋቂዎችና የበታችነት ስሜት ያናወዛቸው ጠባብ ትምክህተኞችን ከስልጣን በጊዜ አስወግደን ሁሉም ሰው እኩል የሚሆንባት የህግ የበላይነት የሰፈነባት የአመለካከት የመፃፍና የመናገር ነፃነት የተረጋገጠባት የሀብት ክፍፍል ሚዛናዊ የሆነባት ሰብአዊና ተፈጥሮአዊ መብቶች የሚከበርባትን የጋራ ኢትዮጵያን ለመመስረት ካልቻልን እንዳበደ ውሻ የሚቅበዘበዙት ወያኔና ሆድአደሮቹ ሸሽተን ከምንኖርበት ሀገርም እንድንፈራና በነፃነት እንዳንኖር እያደረጉን ይገኛሉ:: እነዚህን በአውሮፓና በአሜሪካ የሚኖሩና የኢትዮጵያውያንን የፍትህ የኩልነትና የአገር የማዳን ትግል በማስፈራራትና የውሸት ፕሮፓጋንዳ በማሰራጨት የማኮላሸት ወንጀል እየፈፅሙ ያሉትን ወያኔዎችና የወያኔ ተላላኪዎችን አጋልጠን ማውጣትና ለፍርድ እንዲቀርቡ ማድረግ አለብን::