ሰበር ወሬ፤ ጋዜጠኛ አበበ ገላው አቶ መለስን በአዳራሽ ውስጥ ልክ ልካቸውን ነገራቸው!
በአሜሪካ ስብሰባ ላይ የሚገኙት አቶ መለስ ዜናዊ በስብሰባ አዳራሹ ውስጥ ገና መናገር ሲጀመሩ ጋዜጠኛ አበበ ገላው ከፍ ባለ ድምፅ፤ “ይህ ሰው ነብሰ ገዳይ ነው… ወንጀለኛ ነው… እዚህ ቦታ ሊገኝ አይገባውም” ሲል በተሰብሳቢዎች ፊት ልክ ልካቸውን ነገራቸው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአዳራሽ ውስጥ እንዲህ ያለ የተቃውሞ ድምፅ ያጋጥመኛል ብለው ስላላጠበቁ ተደናግጠው ንግግራቸውን አቆርጠው እንደነበር የዘገበው ኢሳት ዜና አበበን የፀጥታ ሀይሎች በሰላም ከአዳርሽ እንዳስወጡት ነግሮናል።
ኢሳትን እናመሰግናለን፤
በመጨረሻም
እኔ
አላልክዎትም አቶ መለስ ይቅርብዎ ስብሰባው በአፍንጫዎ ጥንቅር ይበል… ብዬዎ አልነበር። ለመሆኑ ከስብሰባው ውጪ ያለውንስ ተቃውሞ እንዴት ቻሉት!? እንግዲህ ይቻሉት!
ተጨማሪውን ነገ እናወራለን።
ቸር ያሳድረን!
Filed under: Uncategorized
![]()