በደብረማርቆስ ዩንቨርስቲ በተነሳ ነውጥ ከ300 በላይ ተማሪዎች ታስሩ
ማለዳ ታይምስ — በደብረ ማርቆስ ዩንቨርስቲ የተማሪዎች የነውጥ እንቅስቃሴ እየተካሄደ መሆኑን ከስፍራው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል። በትላንትናው እለት የተጀመረው የተማሪዎች ረብሻ ዛሬ ረገብ ብሎ ቢዉልም የምንፈልገውን እስካላስተካከለልን እንቀጥላለን በማለት ተማሪዎቹ አስታውቀዋል። የረብሻው መንስኤ በትምህርት ቤት ዉስጥ የሚገኘው የምግብ ጥራትና ከፍተኛ የንጽህና ጉድለት ብዙ ተማሪዎችን ለምግብ-ወለድ በሽታ ያጋለጣቸው መሆኑን ጠቁመዋል። በግምት ከ300 ተማሪዎች በላይ ታስረዋል። እጅግ በጣም ብዙ ንብረት ወድሟል።፡አንድ አንድ ተማሪዎች አምልጠው ወደ ቤተሰቦቻቸው ሄደዋል። ለተማሪዎቹ የትራንስፖርተ አገልግሎት ለመስጠት ሲሯሯጡ የነበሩ ደላላዎችም ታስረዋል። በሌላም በኩል ከባህርዳር ወደ ደብረማርቆስ የተላከው ልዩ እዝ የመከላከያ ወታደር እና የፖሊስ ሰራዊት ወደ ግቢው በመግባት ተማሪዎቹን አፍሶ እንደወሰደ የደረሰን ሪፖርት ያመለከታል።