ሁለተኛ ግፌ ጫንቃዬን ተገርፌ ልብሴን መገፈፌ! ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
በሀገሬ ሳለሁ፥ ለዓመታት ከለፋሁበት የትምህርት ገበታዬ ተፈናቅዬ: ያለፍርድ ቤት ማዘዣ ወረቀት ተይዜ ከአንዴም ሁለቴ ለእስር የተዳረግኩ: በሞትና በህይወት መካከል የተገረፍኩና
የተደበደብኩ: በመጨረሻም ሀገሬን ለቅቄ በባዕድ ምድር ያለ አንዳች ረዳትና የህይወት ዋስትና በእንግድነት እንድኖር የተገደድኩ ስዘርፍ: ሳምጽና የሰው ሚስት ሳማግጥ ተገኝቼ ወይም ተደርሶብኝ ሳይሆን ሕገ መንግስታዊ (አንቀጽ 29) መብቴን በመጠቀም ጸረ- ቤተ ክርስቲያን: ጸረ ሀገርና ጸረ ትውልድ በሆነው ድብቅ አጀንዳ ያለው ማህበር ላይ “ማህበረ ቅዱሳን ወይስ ማህበረ ሰይጣን?” በማለት በበርካታ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሕጋዊ ሰነዶችና ደብዳቤዎች የተደገፈ ከጻፍኩት መጽሐፍ የተነሳ ነበር:: የታሪኩ አንዳኛ ምዕራፍ መሆኑ ነው!
ሁለተኛውሳ? ማለታችሁ አይቀርም:: የሁለተኛው ነገርማ ደግሞ የከፋ የሚያደርገው ሰሞኑ ለንባብ ከበቁ ጽሑፎች ተያይዞ ከወደ “ሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች”: “የነጻነትና የፍትሕ ታጋዮች”: “ዲሞክራቶችና ነጻ አውጪዎቻች” ሰፈር እየታየ: እየተሰማና እየተንጸባረቀ ያለው እውነታ መሆኑ ነው:: ሰው ሃሳቡን ገለጸ ተብሎ ሃሳቡን ሳይሆን ዕድሜውን ለማሳጠርና ዘመኑን ለማጨናገፍ የሚታየው የሚሰማውና የሚወርደው መብረቅና ነጎድጓ እንዲሁም ከጥቂቶች የሚወረወረው ጦርና ፍላጻም ከጽሑፉ አዘጋጅ አልፎ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የድረ ገጾች ባለቤቶችን ጭምር እያዳረሰና እያጠቃ መምጣቱ ይባስ ጉዳዩ አሳሳቢ አድርጎታል:: ስቀለው! ስቀለው! ባይ ቁጥርም ተበራክተዋል:: ቁምነገሩ ሰው ሃሳቡን ገለጸ ተብሎ እንዲህ ያለ ልቅነት ምን አመጣው የሚል ነው? ሌላው ቢቀር ሕግ ባለበት ሀገር በርስትህና በሚስትህ የተገኘ ሰው እንኳን ቢሆን እንዲህ አታንጓጥጠውና ጉዳዩ ፍጹም ሌላ መልክ ይዞ የከፋ አደጋ ከማድረሱ በፊት ለመመካከር ያክል እንዲህ ያለ ጽሑፍ ለማዘጋጀት ግድ ብለዋል::
እንግዲህ “ሁላችን” እንደምናውቀው የሰው ልጆች ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን በተመልከተ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌ አንቀጽ 19 ቀዳሚ ተጠቃሽ ለመሆኑ የምንስተው አይመስለኝም:: የዛሬ ማወያያ ርእሳችንም ከዚህ አንቀጽ በመነሳት ይሆናል::
አንቀጽ፡ 19 “እያንዳንዱ ሰው የሐሳብና ሐሳቡን የመግለጽ መብት አለው።
ይህም መብት ያለጣልቃ ገብነት በሐሳብ የመጽናትንና ዜናን ወይም
ሐሳቦችን ያላንዳች የድንበር ገደብ የማግኘትን የመቀበልንና ወይም የማካፈልን ነጻነትም ይጨምራል።”
የሚል ሲሆን በዚህ አንቀጽ ውስጥ የተመላከቱ ነጥቦችም በጥቂቱ የተመለከትን እንደሆን: “እያንዳንዱ ሰው የሐሳብና ሐሳቡን የመግለጽ መብት አለው“ እንዲል በዋናነት አንድ ሰው የሌላውን ወገን ሃሳብ የመቀበል: የማስተናገድ: የማስተጋባት: የማንጸባረቅና የማመን በአንጻሩ ደግሞ መስሎ ያልታየውን ሃሳብን በሃሳብ የመቃወምና ያለመቀበል በተጨማሪም የራሱን ሃሳብ በማንኛውም ዓይነት መንገድ በቃልም ሆነ በጽሑፍ የመግለጽ መብት እንዳለው የሚያትት አንቀጽ ነው:: ልብ ይበሉ! “መብት አለው” እንዲል ይህ ዓይነቱ መብት ደግሞ በሕግ የተጠበቀ ነው:: ሲሞቀን የምቆፈቅፈው ሲበርደን ቁልቁሊት የምንደፋውም አይደለም:: በሌላ አገላለጽ የሰውን ሃሳብ: በሃሳብ የመቃወም መብት እንደተጠበቀ ሆኖ በአንድም በሌላም መልኩ የሰውን በነጻነት ሃሳብን የመግለጽ መብት ተከትሎ የሰውን መብት መግሰስ ግን በሕግ እንደሚያስጠይቅ ነው:: አክሎም “ይህም መብት ያለጣልቃ ገብነት … የመቀበልንና ወይም የማካፈልን ነጻነትም ይጨምራል” እንዲል ይህን ነጻነት በመጋፋት ሕጋዊ ነጻነቱን ተጠቅሞ ሃሳቡን በሚገልጽ ግለሰብም ላይ ማንኛውም ዓይነት ጫና ለማሳደር ሙከራ ማድረግ: ይህ በል እንዲህ ግን አትበል: ይህን ጻፍ እንዲህ ግን አትጻፍ በማለት ሃሳቡን በነጻነት በሚገልጽ ግለሰብ ትክሻ ላይ መንጠላጠል ጸረ- ሰብዓዊ ነጻነት ከመሆኑ በላይ ጋጠ-ወጥነት ለመሆኑ ምንም አያጠያይቅም::
አሁን እንግዲህ ይህን ትንታኔ ይዘን የአንድ ግለሰብ ሃሳብን/ጽሑፍ ተከትለው ወደ ሚሰጡት “አስተያየቶችና” ወደ ሚሰነዘሩት የተቃውሞ ቃላቶች የተመለስን እንደሆነ በበኩሌ ብዙ ከማለት በመቆጠብ ከተባለ ዘንዳ “ዲሞክራሲን ያያችሁ?” ማለት አሁን ነው ለማለት እወዳለሁ:: ምንነው ቢሉ?
ü ከዚህ በላይ ፍትሕን ማሳጣት:
ü ከዚህ በላይ ጸረ- ዲሞክራሲ እንቅስቃሴ:
ü ከዚህ በላይ አንባገነናዊ አስተሳሰብ:
ü ከዚህ በላይ የዜጎችን ነጻነት መጋፋት:
ü ከዚህ በላይ ሰብዓዊ መብትን መርገጥ:
ü ከዚህ በላይ የዜጎች ድምጽ ማፈን:
ü ከዚህ በላይ ዳግም የባርነት ቀንበር መጫን:
ü ከዚህ በላይ የዜጋ ሃሳብን በነጻነት የመግልጽ መብት ከመከልከል ገደብ ከማኖርና ድንበር ከማበጀት በላይ ወንጀል የለምና:: “ሁለተኛ ግፌ ጫንቃዬን ተገርፌ ልብሴን መገፈፌ!” ለማለት የደፈርኩበት ምክንያትም ከዚህ የማይካድ ተጨባጭ ገጽታችን የተነሳ ነው::
ስለ ፍትሕ: ነጻነትና ዲሞክራሲ መቆም ማለት ፍትሃዊ አመላካከት ያላቸውን ዜጎች በተራ ቃላት ማሳደድ: መመንጠር: መልቀምና ማጥፋት ከሆነ የተያያዝነው አገርን የማልማትና ትውልድን የማዳን ስራ ሳይሆን በአንጻሩ ራርሳችንን የመግደል ከፍተኛ ወንጀል ላይ መሰማራታችንን መሆኑ ልናሰምርበት ይገባል:: በነገራችን ላይ የዚህ ሁሉ ግርግር ምንጭ ሌላ ምንም ሳይሆን መሰረቱ በተበላሸ ፖለቲካ ለመቆማችን የሚያሳይ ሁነኛ ምሳሌ ለመሆኑ ለመጥቀስ እወዳለሁ:: በተረፈ ግን ያገናኘን ሀገርና ሕዝብ እስከሆነ ድረስ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ስለ ሀገሬ ሀገራዊ: ሃይማኖታዊና ማህበረሰብአዊ ጉዳዮች ከራሴ አልፌ ሕዝብን ይጠቅማል ያንጻል ሀገርንም ይበጃል ያቀናል የምለውን ከቅዱሳት መጻሕፍት የተማርኩትን ያለመከልከልና ያለገደብ ያለምንም ተጽእኖም የመጻፍ: የመናገር: ሃሳብን በነጻነት የመግለጽና የማንሸራሸር ተፈሮአዊ: ሕጋዊና ሞራላዊ መብት አለኝ:: ስራዎቼንም በተመለከተ እንደማንኛውም ንጹሕ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ኢትዮጵያዊ ራዕይ ባላቸውና በኢትዮጵያ አንድነት በሚያምኑ ድረ ገጽች ላይ አቅሜ በፈቀደው በመሳተፍ ረገድ ባለ ሙሉ መብት መሆኔን ስገልጽ በአክብሮት ነው::
እዚህ ላይ አንባቢያን እንደ ግለስብ የአንድን ሰው ጽሑፍ የማንበብና ያለማበብ ባለሙሉ መብቶች ሆነን ሳለን ልዩነትን የማስተናገድ ግዴታ ባለባቸው መገናኛ ብዙሐን ላይ ጫና ለመፍጠርና የፈላጭ ቆራጭነት የመጫወት ሚና ለማሳየት የምናደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ፍጹም ኢ-ዲሞክራሲያዊ እንቅስቃሴ መሆኑን ተገንዝበን ከአንዲህ ዓይነቱ የሀገርንና የትውልድን ዕድገት የሚያጨናግፍ ተግባር እንድንታቀብ በአክብሮት እጠይቃለሁ:: አሁንም ቢሆን ጽሑፌን ከማገባደዴ ቤፊት በድጋሜ ለማለት የምፈልገው ነጥብ ቢኖር ያገናኘን ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ሕዝብ እስከ ሆነ ድረስ ማንም የነጻነት ሰጪ ናነሺ ሊኖር እንደማይችል አውቀን ያዋጣኛል ብለን በተያያዝነውና በያዝነው አቋም እንግፋበት እላለሁ::
ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
May 6, 2012
You are educating us about democracy poor mulugeta??????????? Shame on you. Ethiopians know what democracy is long before you know what it is. The problem is woyyane and people like you who are full of lies and lies are dividing us and making it difficult for our dreams to be a reality if not impossible in the near future. You make me laugh Ato Mulugeta (I can’t call u diakon any more since your lies have taken your title away from u)????? You make me laugh!!!!!!!!!!! Did woyanne arrest you because you stand against Mahibere Kidusan?????????? Really???? What a white lie. We all know how much woyanne will be happy with people trying their best to delete mahibere kidusan from history. Why u keep lying by the way? Who comes first when our orthodox church forests are caught by fire. Church leaders from arat killo????????????? Never. You liar mulugeta, who writes the truth about walidiba? I haven’t seen an article from you criticizing wayyanes act of destroying waldiba and other monastries. Instead, you are insulting true monks in the countryside while the problem is with the devil patriarch at Arat killo. Though we will not have trust in u any more, please try to write the truth as Ethiopia is at a cross road than ever.
kediakon yihin yahil yefetera wushet mesmat betam betam tesfa yaskorital. Ebakih endih eyewasheh kefetari atrak sewochinim atasasit.
ማቅ አንዳንድ አባላት የሲ,አይ,ኤ አባላት ናቸው ላልከው እንደ አንድ ታዛቢ የምለው እንኳን ሆኑ:እሰይ ድንቅ አደረጉ የማቅ አባላት;ሙሉ ጋኔን እፈር::ስለዚህ ቢሆኑማ ጥሩ ነው አሁን ካለህበት አሜሪካ ሊያባርሩህ ይችላሉ ማለት ነው::ያልከው ዉሸት ነው እንጂ ቢሆንማ መለስም ማኅበሩን እንዲህ በሚዲያ አይሰድበዉም ነበር;አምላኩ አሜሪካ ስለሆነ::እውነት ነው ብለህ ከተቀብክማ አፍህን ዝጋ::እግዚአብሔርን ለማይፈራ እንደ አንተ ላለው ሙሉጋኔን አሜሪካ አምላኩ ስለሆነ እነሱንም ፍራቸው::አንተ እንደሳልከውና እንደምትለው እንዲህ ጨካኝ ማኅበር ከሆነ እኮ አንተንም እንደ ገነት ቆጥረህ ከምትመጻደቅበት አሜሪካ እንዳያስወጣህ:መለስንም ከስልጣኑ እንዳያወርደው ተጠንቀቁ::
This message is for Elias. Elias you are our hero! you have a lot of admirers. But now I hate to open your website mainly because of this stupid guy ” Mulugeta w/gebriel. Do you think he is contributing some thing positive for our struggle? I don’t think so…because he is trying to divide Orthodox people and insulting time and again our custom and tradition. Please block him from pasting in your site. It looks that he is some how crazy with protestant ideology and would like to behave like orthodox. His belief is up to him but he don’t have to insult other’s believe. He mention time and again about constitution but does it give him right to insult and undermine other belief. I don’t know how old he is but he behaves like a child who is too emotional and has no logic. Anyway, Elias before we turn to you…please block this guy from wrting on this page that all of us come here to read something good…never at all like his shit!!
Dear Degu,I fully agree with your comment and I hope Elias will understand and accept our concern.
To Everyone! Please don’t read or respond to this sick, rubbish, and deluded person. This is the only way we can discourage him from making such an immoral and baseless comments. Just ignore him. Let’s not make him feel that he is getting our attention. The only thing I with for him is to get some therapy for his mental disorder before he lose it. Please my brother, Mulugeta, this is not normal and I urge you to get some help.
I personally believe that you are over using the constitution Ch.29. Do you remember what Meles said one time? He said “You have the right to extend your leg, unless you touch somebody’s nose.” I don’t know you or MK but from what you writing, your articles are more than touching somebody’s nose. For example, the one you wrote response for AZEB, please read it back!! I was thinking about your articles, and the right of expressing ideas and opinions freedom.
Where is our Ethiopian politeness and respectfulness????
Egziabhere Libona Yistih, Let God help you to look back to yourself.
Tazabi
የሞትክ እና የተረሳክ ወራዳ ፍጡር ነክ ከማለት ውጭ ምን ይባላል!የኛ ተቆርቁዋሪ;አንተን ብሎ ደግሞ የበተ-ክርስቲያን ተቆርቁዋሪ;
በጣም ጅል ነክ!::
I don’t usually understand what this Wofefe talks about.
And my other question is, How Ealias kifle analyzed the benefit if this guys article?
‘’Deacon” it is good to know that you have gone through article 19.Indeed every one has the right to express his/her own opinion freely, but does article 19 states that insulting others or fabricating lies and confusing others is also the right of expressing yourself ???
May GOD be with you
የፈለግከውን መትጻፍና መቀብጠር ትችላለህ ነገር ግን በዚህ አንደበትህ ያጠለከውን የበግ ለምድ አውልቀው::
አስሩም ኮመንት የተሰጠው ከአንድ ሰው ነው መሰለኝ!?
Pastor Mulugeta,You are fine ignorant person.
ወያኔን አሜሪካ ሆኖ መሳደብ መብት ነው። ግን ወያኔን ከኢትዮጵያ በፍጹም አያስወጣውም። አራት ነጥብ! ሙሉጌታን መተቸት መንቀፍ ይቻላል፤ ግን የሙሉጌታን ጽሁፍ ማስቆም አይቻልም። አራት ነጥብ!
ምድረ ጉረኛ ሀገር ወዳድ፤ አሽቃባጭ ሁላ!! ወያኔ ለምን ሃያ ዓመት እንደአህያ ረግጦ፤ እንደውሃ ደማችንን አፍሥሶ፤ እንደ ሸንኮራ አገዳ ግጦና መጥጦ የተጫወተብን ለምን እንደሆነ ታውቃላችሁ? እዚህ ድረ ገጽ ላይ ዘራፍ የሚሉ ግን ጠባብ ሱሪ ታጥቀው መዋጋት የማይችሉ ቡከኖች ስለበዙ ብቻ ነው። በርገር እየገመጡ የሚፎክሩና የሚያቅራሩ ቡከኖች ከአሜሪካ ይሁን ከየትኛውም ውጪ ሀገር ኢትዮጵያን ነጻ አያውጡም! አራት ነጥብ!! በረሃብ እየተሰቃየ፣ በጥይት እየተገደለ፤ በስለላ መዋቅር እየተጨነቀ ያለው የሀገር ቤቱ ወጣት እንደግብጽ ሆ ብሎ መንግሥት እስኪገለብጥለት የሚጠብቅ የማክዶናልድ ጀግና እንኳን ሙሉጌታን ይቅርና ጠላት የሆነውን ወያኔን የመሳደብ ብቃት የለውም!! አራት ነጥብ!! ጠላትህን የምትንቀው በልጠኸው ወይም ተፎካክረኸው ስትገኝ ብቻ ነው! ገባህ ምድረ ቡከን ፈሪ ሁላ!
ወንድ የሆነ ፊከራውን ትቶ ይምጣ! ከዚያ ውጪ ሰላማዊ ሰልፍ፤ ጩኸት፤ ገንዘብ መዋጮ፣ አክቲቪስት ገለመሌ ምንም አይገባኝም!! ወያኔን ለመጣል ታጥቀህ መዋጋት አለበለዚያም ዝም ብለህ ሳህንህን እጠብ!!ጊዜው የወሬ አይደለም!
ገሞራው ከጁባ ላንድ፤ ደቡብ ሱዳን
Elias, where is my comment on this wefefe guy? I sent it yesterday… is moderation means scensoring? why don`t u scensor the writing of this good for nothing guy… it seems you are also at the back of him… ayeeee…. antes dehena sew meselehegn neber…. tuuuu
why this person hammering Mahber kdusan in particular at this time ? when burning issues like waldba,movement of our Muslim brothers,the struggle of Ethiopians in Gambela,gojjam ,gonder ,the massacre and cold blood killings of the woyane in wolayta and other places in Ethiopia.he can choose from thse historical events if genuinly interested in to expose than dwelling 1000 times on Mahbere kudsan which is targetd by woyane either to divide it or dismantle it into pieces.So mulugeta has to show that he is not part of the woyane conspiracy by condemning and expose the woyane’s grand plan of destrying the church and above all our Ethiopia.
You are coverd by “Deacon” Mulugeta W/Gabriel,but we know already you are
“woyane’s” spy. Because your duty is the witness.”enough!!!” you are trying to split
the idea of peoples of diaspora like woyane does.
“YOU ARE THE SON OF CATASRROPHE!!!
ርዕሱ ገርሞኛል, ‘ሁለተኛ ግፌ ጫንቃዬን ተገርፌ ልብሴን መገፈፌ!, እንደ ክርስቶስ???!!||
አይ አቅምን አለማወቅ;
Dear readers,
You need to understand the man from his amharic grammer. He is one of Meles’s/ Aba paulo’s relatives. In all his aricles; he jumps from one point to the other, no fullstop, no prepositions, he uses wrong words, above all no respect for others. He is typical Tigre( sorry to say that). I think Elias is also the same in his manner. Even though it seems that he is against Weyane, actually he is not. Most probably he is the one giving the names and profiles of people who are contributing articles and proving informations against the rulling party. Just think the journalist who are in preason. The govenment might have got their profile from these two guys. Please forget people like these(Kehadis) and unite and do something to overthrow the mad man in power.