ኤፍሬም እሸቴ: ብትስማማ ነው እንጂ የሚያስደምመው ባለመስማማትህ ምን ይደንቃል?
ጥብቅ ማሳሰቢያ: ጽሑፉ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር በመደገፍ የተጻፈ ጽሑፍ አይደለም:: ጽሑፉ ኤፍሬም እሽቴ የተባለው አንድ “የማህበረ ቅዱሳን” የስራ አመራር አባል ግለሰብ “ጠ/ሚኒስትሩ ስለ ማኅበረ ቅዱሳን በተናገሩት አልስማማም” ሲል ከግንዛቤ እጥረት የተነሳ በጻፈው የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን አስተምህሮ የማይወክል ዝርው ይዘት ያለው ጥሬ ጽሑፍ አስቸኳይ እርምት እንዲደረግበትና በክርስትና ስም በአንባቢያን ላይ የፈጠረውን ብዥታ ግምት ውስጥ በማስገባት የተጣራ ምስል ለመስጠት ኩልል ቅልብጭ ባለ መልኩ የተዘጀ ጽሑፍ ነው::
“ማህበረ ቅዱሳን” የቤተ-ክርስቲያን የቆሎ ት/ቤት ያልቀመሰ፣ የዜማ፣ የቅኔ፣ የመጽህፍት ትርጓሜያት፣ የቅዳሴ፣ የአቡሻክር … ወዘተ ባህር ያልዳሰሰ የቤተ-ክርስቲያን ጥንተ ታሪክ ያልመረመረ፣ ጥምጥም ያለው ጥቁር ጎማሳ፣ ሆኖ እያለ እምነበሃን የማያውቅ ዲያቆን፣ አሀዱ አብን የማያውቅ ቄስ፣ አአትብ ገጽየን የማያውቅ ክርስቲያን፣ የሴቶችና የወንዶችን መግቢያ በር
በቅጡ የማያውቅ፣ ሱቅ ከፍቶ ቄስ ቀጥሮና አቁሞ ስለ ነገደ ቄስ የሆነ የሚመስለው ጠባቂ ነኝ የሚል አጽራረ ቤተ-ክርስቲያን ጿሚ መሳይ አጋሰስ፣ የማይሰግድ አሰጋጅ፣ ለማስተማር የማይበቃ አቃቤ መቃብር ባለ ዲግሪ፣ አስራት የማይከፍል በዝባዥና አስከፋይ፣ የማይቀድስ አስቀዳሽ፣ ያልተለወጠ ለዋጭ አስመሳይ የጎበዝ ጥርቅም ማኅበር ነው ሲባልኮ ተራ ውንጀላ ወይንም ደግሞ ክስ ሳይሆን ምስክርነታች ጭብጥ ላይ የተመሰረተ እውነት ነው::
ይህች ጦማር የቀድሞ የማህበሩ አውራ ቂስ ኤፍሬም እሸቴ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር በዕለተ ማክሰኞ ሚያዚያ 9/2004 ዓ.ም በፓርላማቸው ተገኝተው ያደረጉትን ንግግር ተከክትሎ “ጠቅላይ ሚኒስትሩ እግረ መንገዳቸውን ያነሱትን እና በኢትዮጵያ ውስጥ አለውን “አክራሪነት” በክርስቲያኑ በኩል “ይወክልልናል” ብለው የጠቀሱትን ማኅበረ ቅዱሳንን በተመለከተ እኔም እንደ አንድ አባል የማምንበት አቀርባለኹ። ማኅበሩ በኃላፊዎቹ በኩል የሚሰጠው መልስ እንደተጠበቀ ሆኖ ለሁለት አሥር ዓመታት አባል የሆንኩበት እና መንፈሳዊ እና ማኅበራዊ አገልግሎቶችን በመስጠት በሁሉም ዘንድ የተመሰከረለት ማኅበር “አክራሪ” አለመሆኑን በግሌ ለመመስከር እገደዳለኹ።” ሲል ባልዋለበትና ባላለፈበት የቅድሳት መጻህፍት ቃል ዓውዱን ባላገናዘበ አኳኃን ምክርን ለማጨለም ባደረገው ሙከራ የተፋለሰውን የክርስትና አስተምሮና በማን አለብኝነት መንፈስ የፈጠረውን እጅግ ግዙፍ የሆነ ስህተት
ኩልል ባለ መልኩ ያስቃኛናለች:: መልካም ንባብ!
ግለሰቡ ምንም እንኳን ራሱ እንደ አንድ ተራ የማህበሩ አባል አድርጎ ለመቅረብ ቢሞክርም ለረጅም ዓመታት በማህበሩ የስራ አመራር አባል: በማህበሩ የተለያዩ የሃላፊነት ቦታችም
ሲሰራ የቆየ: አሁንም ቢሆን ከቤተ-ክርስቲያን ጫንቃ ያልወረደ: በቤተ-ክርስቲያን የምጽዋት ገንዘብ ኑሮውን ያደላደለ በዋናነት ከተጣያቂነት የማያመልጡ የማህበሩ ልሂቃን መካከል ለመሆኑ የማህበሩ ስም በተነሳ ቁጥር ይህን እውነታ ሳያውቅ የሚቀር ያለ አይመስለኝም:: ግለሰቡ ወደ አሜሪካ እንዴት መጣ አሁንስ የማህበሩን ተልዕኮ ከማከናወን አንጻር ምን እየሰራ ይገኛል የሚሉትና ሌሎች ተጓዳኝ ጥያቄዎች በቅርብ በስፋት የምንመለከተው ይሆናል:: ለጊዜው ግን የተነሳንበትን ዋና ርእስ እንጠበጥባለን::
“በመጀመሪያ “አንድ ሃይማኖት” የሚለው መሠረታዊ ሐሳብ ለብዙ ውይይቶች በር የሚከፍት ትልቅ ጉዳይ ነው። ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚያስተምረን እና የጥምቀት አክባሪ ክርስቲያኖች በቲ-ሸርቶቻቸው ላይ አትመውት በፎቶግራፍ የተመለከትኩት ኃይለ ቃል ቅዱስ ጳውሎስ በኤፌሶን መልእክቱ ምዕራፍ 4 ቁጥር 5 ላይ የጻፈው “አንድ ጌታ፣ አንድ ሃይማኖት፣ አንዲት ጥምቀት” የሚለው ሐዋርያዊ ቃል ነው። ይህ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል እንጂ የጥምቀት አክባሪዎቹ የፈለሰፉት አይደለም። የትኛውም ክርስቲያን “አንድ ሃይማኖት” ቢል የሐዋርያውን ቃል መጥቀሱ እንጂ ሌላ እምነት ላላቸው ኢትዮጵያውያን ጥላቻ አለው ማለት አይደለም። የጥምቀት አክባሪ ወጣቶች ቲ-ሸርቶች ላይ የተጻፈውን የሐዋርያውን ቃል የምረዳው በዚህ መንፈስ ነው።” (ውድ አንባቢ: የዚህ ጽሐፍ ዋና ዓላማ የኤፌሶን መልዕክት መንፈሱን በሚገባ መተንተን: መመስከር ነው)::
ይህ ሰው ሌላው ቢቀር የተጠቀሰውን ቃል ፊደላትን ከማንበብና ከማነብነብ ባልዘለለ መልእክቱን በሚገባ አለመረዳቱና አለማወቁ ብቻ ሳይሆን የፈጠረውን ስህተትና ያፋለሰውን አስተምህሮ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን ሊቃውንት ጨምሮ አባባሉን ሌሎች እንደሚጋሩት ሃፍረት ሳይሰማው እንዲህ ሲል መግለጽ ነው “በዚህ የሐዋርያው ቃል ውስጥ ያለው “አንድ ሃይማኖት”
የሚለው አገላለጽ የሚናገረው ስለ ክርስትና ሃይማኖት ነው። ሌሎች እምነቶች የሉም፣ መኖርም የለባቸው የሚል የጨፍላቂነት ትምህርት ለመሆኑን ሊቃውንቱ አምልተው አስፍተው ሲያስተምሩ ኖረዋል፤ እያስተማሩም ነው። አሁን ደርሶ የሚለወጥ ነገር የለም።” እዚህ ላይ ሊቃውንት የሚላቸው በሰው የእአምሮ ንብረት ስርቆት ላይ የተሰማሩ እንደነ ዳንኤል ክብረት የመሳሰሉ በጠራራ ጸሐይ ፎቶግራፍ የሚያነሱ ከሆነ እስማማለሁ::
በዚህ ሳይገታም (ጽሑፉ የሚያጠነጥነው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር እስከ ሆነ ድረስ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መጎንተሉ ነው) በትልቁ ከቃሉ ጋር ፈጽመው የማይታወቁ ራሱ አቶ ኤፍሬም ጨምሮ ማህበሩና አባላቱ እያሉ በተጨማሪም አራት ገጽ ያስጻፈበት ምክንያት ፊደል እንደቆጠረ እንደማንኛው ሰው መልእክቱ ሲያነበው (ኤፌ. 4:5 ለማለት ነው) ነገር ቆስቋሽ ሰላም
ነሺ የአመጽ ቋንቋ ሆኖም ስለተሰማው ጳውሎስ ወይንም ደግሞ እግዚአብሔርን ላለማሳፈር “አንድ ሃይማኖት የሚለው አገላለጽ ከሃይማኖት ጋር በማይተዋወቁ ሰዎች ዓይን ከተመለከትነው መቻቻልን ለማስተናገድ ፈቃደኝነት የጎደለው አገላለጽ ሊመስል ይችላል።” በማለት አጉል ጥብቅና በመቆም ለመገንባትና ለማጣጣም በሚያደርገውና ባደረገው ሙከራ ቃሉን ማፋለሱ ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔርን ማሰደቡ ስመለከት አገላለጹ በቀላሉ የአብዬን ለምዬ አስብሎኛል::
ውድ አንባቢ: እንግዲህ እስከ አሁን ድረስ ያለነው መግቢያ ላይ ለመሆናችን ለመግለጽ እወዳለሁ ወደ ሚቀጥለው የጽሑፉ ዋና ክፍልና ዓላማ ስንሸጋገርም ብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ እንዳስተማረው እንዲሁ ህይወት የሆነውንና ህይወትን የሚሰጥ የመልእክቱ መንፈስ እናገኘው ዘንድ በታላቅ እርጋታና ማስተዋል ጽሑፉን እናነበው ዘንድ በድጋሜ በወንድማዊ መንፈስ በትህትና እጠይቃለሁ::
“እንግዲህ በጌታ እስር የሆንሁ እኔ በተጠራችሁበትመጠራታችሁእንደሚገባትመላለሱዘንድእለምናችኋለሁ፤
በትሕትናሁሉና በየዋህነትበትዕግሥትም፤
እርስበርሳችሁበፍቅርታገሡ፤
በሰላምማሰሪያየመንፈስንአንድነትለመጠበቅትጉ።
በመጠራታችሁ በአንድተስፋእንደተጠራችሁአንድአካልናአንድመንፈስአለ፤
አንድጌታአንድሃይማኖትአንዲትጥምቀት፤
ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ።” ኤፌ. 4: 5
ጳውሎስ እንዲህ ያለ መንፈስ ያለው የአማኞች ህብረትንና አንድነትን የሚያጠነክር መልእክት ሲጽፍ ለመጀመሪያ ጊዜው አይደለም:: የአማኞች በቁጥር መበራከትና ከተለያየ ልማድና ወግ መምጣታት ተከትሎ ይፈጠርው የነበረውን ችግር በማስመልከት ጳውሎስ በርካታ ገንቢ መልእክቶችን ጽፈዋል:: ለምሳሌ የተመለከትን እንደሆነ በኤፌሶን ከተማ ሳለ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች የጻፈውን አንደኛ መልእክቱ ለርእሳችን ተጠቃሽ ማጣቀሻ ነው::
የቆሮንቶስ ቤተ-ክርስቲያን ከተከሰቱ በርካታ ችግሮች መካከል ትልቁና ዋነኛ ችግር በእግዚአብሔር ቃል ካለማደግና ካለመብሰል ቃሉንም በሚገባ ካለማጥናት የተነሳ “እኔ የጳውሎስ ነኝ” “እኔ የኬፋ ነኝ” እያሉ ለአራት ተከፍለው ጎራ ለይተው እርስ በርሳቸው መቧቀሳቸው ነበር:: ይህንን የሰማ ጳውሎስ “ነገር ግን ወንድሞች ሆይ ሁላችሁ አንድንግግር እንድትናገሩ በአንድልብና በአንድሃሳብም ተባብራችሁ እንድትሆኑ እንጂ መለያየት በመካከላችሁ እንዳይሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እለምናችሃላሁ:: ወንድሞቼ ሆይ በእናንተ ክርክር እንዳለ ስለ እናንተ የቀሎዔ ቤተ ሰቦች አስታውቀውኛል:: ይህንም እላለሁ እያንዳንዳችሁ እኔ የጳውሎስ ነኝ፥ እኔስ የአጵሎስ ነኝ፥ እኔ ግን የኬፋ ነኝ፥ እኔስ የክርስቶስ ነኝ ትላላችሁ ክርስቶስ ተከፍሎአልን? ጳውሎስስ ስለ እናንተ ተሰቀለን? ወይስ በጳውሎስ ስም ተጠመቃችሁን? …“ (1ኛ ቆሮ. 1: 10) እያለ ይቀጥላል::
የቆሮንቶስ ሰዎች በክርስቶስ ስም በቤተ ክርስቲያን ዙሪያ መሰባሰባቸው ሲያበቁ ኑሮአቸው ግን ፈጽሞ የምስራች (ወንጌል) ካልሰሙት አህዛብ በማይተናነስ ድርጊት ተጠምደው ወደ ቀድሞ ኑሮአቸው በመመልስ/ተመልሰው ልምምዳቸውን ሲገፉበት መሆናቸው ሲሰማ የሰማውንም ሁሉ እውነት መሆኑን ሲያረጋግጥ የጻፈው መልእክት የቆሙበት ስፍራ ለማመላከት ነበር:: ከዚህ የጳውሎስ መልእክት አንድ ትልቅ ቁምነገር ለመረዳት የሚቻለው ሰው ሲባል በእግዚአብሔር መንፈስ ካልተነካ በስተቀር በሃሳብም ሆነ በቃል አንድ ብሎ ነገር ፈጽሞ የማይታሰብ ነው የሚለውን አንድምታ እንደተጠበቀ ሆኖ የእግዚአብሔር መንፈስ የተቀበሉ: ብዙ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች የተገለጡባቸው: በአንድ ንግግር በአንድ ልብ በአንድ ሃሳብና ቃል ህብረታቸው ከማንም በላይ ያጠናክሩ ዘንድ የሚጠበቅባቸው የቆሮንቶስ ሰዎች በአንጻራዊ ገጽታ ሆነው ሲያገኛቸው በሌላ አነጋገር የተቀበላችሁት መንፈስ እኮ እንዲህ ለመነታረክ: ለመለያየት: ለመናቆር እርስ በርሳችሁም ለመናካስ ሳይሆን የተቀበላችሁት መንፈስ የተበተነውን የሚሰበስብ/አንድ የሚያደርግ: ልዩነትን በወንድማዊ ፍቅርና በመቻቻል የሚያጠብ: በጸብ ፈንታ ሰላምን ፍጹም መዋደድን የሚሰጥ: እግዚአብሔርን የሚያከብርና የሚያነግስ ነው ታድያ ይህ መንፈስ የትገባ? ምን ዋጠው? ወይስ የተቀበላችሁትን አታውቁምን? ለመሆኑ እንዲህ ያለ ግርግርና ኢ-ክርስቲያናዊ ምግባር ከማን የተማራችሁ ነው? ይህ ሁሉ ወከባ ምን ለመሆን: የትስ ለመድረስ ይሆን? ምክንያታችሁ ማወቅ እፈልጋለሁ:: ሰው ሲያምን ከስጋ ደዌ ከመንፈስ አባዜ ይፈወሳል እንጅ እንዲህ ያለ ነገርስ ትክክል አይደለም:: አይሁድ ብንሆን የግሪክ ሰዎችም ብንሆን ባሪያዎችም ብንሆን ጨዋዎችም ብንሆን እኛ ሁላችን በአንድመንፈስ አንድአካልእንድንሆን ተጠምቀናልና ሁላችንምአንዱንመንፈስጠጥተናል (1ኛ ወደ ቆሮንቶስ 12:13) በማለት ወደ ልቦናቸው ይመለሱ ዘንድ የሚያሳስብ ነው::
አሁን በዚህ መንፈስ ወደ ኤፈሶን መልእክት ተመልሰን እንመጣለን:: የኤፌሶን መልእክት የተጻፈው በተመሳሳይ ጸሐፊ በሐዋሪያው ቅዱስ ጳውሎስ ሲሆን መልእክቱ የተጻፈበት ምክንያትም
እንደ እንዳንዶቹ በሚገጥማቸው ችግሮችና መሰናክሎች የተነሳ ሳይሆን በመጽሐፉ ምዕራፍ አንድና ሁለት በተገለጸው መሰረት መልእክቱ የተጻፈበት ምክንያት በኤፌሶን የምትገኘውን ቤተ-ክርስቲያን ምእመናንና አባላት (ሌሎች) በዘመን ፍጻሜ የእግዚአብሔር ዘላለማዊ አሳብ ይረዱና ያውቁ ዘንድ: አማኞች በመንፈስ ቅዱስ ጠንክረው የክርስቶስ ፍቅር ለማስተዋልና ለማወቅ ይበረቱ ዘንድ እንዲሁም በእግዚአብሔር ጸጋ ዕለት ዕለት ወደ ምልዓት ያድጉ ዘንድ የተጻፈ መልእክት ነው::
እንግዲህ ጳውሎስ“አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት” ሲል በጌታ በማያምኑ: ሃይማኖትም በሌላቸው: በልተጠመቁ ወገኖች/አካላት ላይ ጣቱ እየቀሰረ ሳይሆን ያለው “አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት” ማለቱ የኤፌሶን ምእመናን በተጠሩበት መጠራት እንደሚገባ በሚገባ እንዲመላለሱ ቀደም ሲሉ ጌታ አምነው በእውቀት ለተጠመቁ ምእመናን በክርስቶስ የያዛችሁትን መንገዳችሁን አጽንታችሁ ያዙ: በትእግስት በየዋሃትና በፍቅርም እርስ በርሳችሁ ተጠባበቁ: ተዋደዱ ምንም የሚያጨቃጭቃችሁ: የሚያነታርካችሁና እርስ በርሳችሁ የሚያናክሳችሁ ነገር አይኑር የሁላችሁም ጌታ አንድ ጌታ ነው! ሃይማኖታችሁም እውነት መንገድም ህይወትም የሆነ ኢየሱስ አንድ ነው! ሁላችሁም የተጠመቃችሁት ጥምቀት እንዲት ጥምቀት ናት! ይኸውም:
v ግሪኩም አይሁዱም አንድ የሚያደርግ:
v ባሪያው ከጭዋው የሚያስተካክል:
v ሴቱም ከውንዱ እኩል የሚያደርግ (በእመነት)
v ክርስቶስን የሚያለብስ:
v ከክርስቶስ ጋር ሕብረት በሚፈጥር:
v ለምስክርነት የሚያበቃ ጥምቀት ነውና እንግዲህ ይህን መንፈሳችሁን ጠብቁ! በማለት የኤፌሶን ምእመናን
ü ፍቅር አጥብቀው እንዲይዙ:
ü መቻቻል እንዲለማመዱ:
ü በሕብረት/አንድነት የሚገኘውን በረከት ተካፋዮች እንዲሆኑ :
ü ወንድማማችነት እንዲያጣጥሙ:
ü ስለ የክርስትና ህይወት ትርጉም እንዲያውቁ:
ü በጥምቀት ስለተፈጸሙት ስርዓት እንዲያስቡ:
ü ከሁሉም በላይ ደግሞ በጌታ ስም ማመን ምን ማለት እንደሆነ እንዲያውቁ ጸጥ ረጭ ባለ በዝግታ መንፈስ የሚነበብ/የሚደመጥ: ተነቦም/ተሰምቶ ወደ ልብ ስለሚወርድና በልብም ስለሚጠበቅ ከሃጢአት: ከጥፋት: ከአመጽ ስለ ሚያተርፍ የተበተነውን ስለሚሰበስብ ህያው ቃል ላከላቸው (መከራቸው) እንጂ የኤፌሶን ምእመናን “አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት!” የሚል መፎክር ይዘው በኤፌሶን ጎዳናዎች አቧራ እንዲያስነሱ አይደለም! እዚህ ላይ ልብ ሊባል የሚገባ ነጥብ ቢኖር አቶ ኤፍሬም እንሳሰበውና እንደተረጎመው “ጥምቀት! ጥምቀት!” እየተባለ የሚጮክ ዝሩው ቃል ሳይሆን ጥምቀት ተብሎ የተጠቀሰውን የውሃ ጥምቀት የሚያመላክት ለመሆኑ ሊሰመርበት ይገባል:: አንድም እንዲት ማለቱ ይህችንም ጥምቀት አንዳዶቻችሁ በውሃ ሌሎቻችሁ በወተት አልተጠመቃችሁም እንዲል ነው::
በሰላም ማሰሪያ: የሚለው ትህትና: የዋህነት: ፍቅር ሁነኛ የአንድ በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያምን ክርስቲያን መታወቂያዎች ናቸው:: “የማህበረ ቅዱሳን” አባላት ክርስቲያን ናቸው ለማለት በራሱ ቀድመውኑ በክርስቶስ ብቸኛ አዳኝነት ሲያምኑ አይደለም ወይ? እንዲሁም በሌላ ስፍራ ጳውሎስ “ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና” እንዲል ኢየሱስን የለበሰ ኢየሱን ይመስላል!! የሀገሬ ሰው “ከአህያ ጋር የዋለ ኰርማ ሕላ (እንደ አህያ መጮህ) ባይማር ምን ይለምዳል” እንደሚለው እንደ “ማህበረ ቅዱሳንና” አባላቶቹ ያሉት ከቃሉ ጋር ምንም ዓይነት ግኑኝነትና ሕብረት የሌለው ደግሞ ጋንጩር መምሰሉ ሊደንቀን አይገባም::
መቼም በዚህ ሁሉ ሐተታ ጳውሎስ“አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት” በማለት የጻፈው መልእክትና “ማህበር ቅዱሳንና” አባላቱ ደግሞ በፊናቸው ባልገባቸው “አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት” ማለትና ምን እንደሆነ ግልጽ ነው ብዬ አምናለሁ የተቀረውን ደግሞ አንድ በአንድ ተለቅመው ለንባብ እስኪበቁ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ምሕረት ሰላማና ፍቅር ከሁላችን ጋር ይሁን::
ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
Email: [email protected]
April 26, 2012
United states of America
ኣይ ዲአቆን ሙሉገታ….ሰበከህ ሞተሃል. አንተ ነህ ማሰተዋል የተሳነህ…ሁሉ ነገረህ መናፊቃን ይመሰላል. በከንቱ አቲድከም ማህበረ ቅዱሳን ሁሉም ኦርቶዶክሰ ይዎዳችሀዋል…ሙሉገታ ግን ጎደሎ ግታ ቢየሃለሁ
This writer is really disgusting, you need to go ahead and read books before you write.
ተባረክ:: አምላክ ከአንተ ጋር ይሁን:: ጥሩ ብለሃል::
I thought you should be the only one who understood what you wrote. Frankly speaking, I am totally lost. Would you please tell us the difference between your idea and Yared Eshetie’s? It seems to me that you are complaining about Yared being the first to write.
My apologies,
Please read Yared as Ephrem.
I can’t sey you are a true ‘Deacon’. What is the importance of those you listed if you are not living in them? First of all whether you believe or not I am not Mahbere KIdusan. But I can obserbe how you guys are livng and what you guys are doing.
I guess most Deacons where Deacons before they join the university. Anyway, they live in understanding God than those who claim they are.
I think it is mahbere kidusan who opened your eyes when you Deacons where runing away from the church. I think it envy, you guys were the thiefs and all wrong doings around the church. I am in US, one deacon stay max 2 years in one church and mess up and run away to other church creating brand new history. Now days even the priests…. You don’t believe in God but you are in his home. Sadly some of them were establishing a kind of protestant, trying to modernize in their hope to get more money from outsiders, Who messed up the church at first? who is still messing the church taking back and forth gossip from one another?
Don’t insult all together, I think it is your friends whom they think they are smart and want to advantge messed them up. Even though those(MK) who didn’t go to kollo timhit bet like you guys, they love God truly and defend truly. they were at first dedicated them selves to save our church and serve God. they were effective and hope they will continue after they fix the problems they have faced. Where as you and your bodies were almost distroying the church. You can’t say anything to them especially like you. Because I read most of your articles. You wandering here and there,
But after you deacons joined them every thing gets messed up again. Go around the states who are messing the church and running here and there. I can understand there are some croocked people who are joined them to fulfilled thier ajenda and now messing them up. But I can’t blame at all. Still they better generation. You and other go ahead on your blog, I guess you are no more working in the church.
Because I am watching you guys whom you think have better qualification for the church.
Dear Mulugeta,
You looks desperate. Inferiority complex is the worst of all psychological problems. So please stay calm. Peoples in Ethiopia know how MK works with the Christian. If you are assigned to do this job by EPDRF, you can continue but you are less competent for the job.
Tadios
Elias, what I have to beg you is that please follow what divisive policy Diakon Mulugeta is following like woyanne hodames. I swear to God, Diakon Mulugeta has some secret plan. Any one living in Ethiopia can understand who is learning Geez and Kidase even while attending higher education in Ethiopia? Diakon, are you crazy? If you are okay, please take time and consider what Mahibere Kidusan is. One thing I don’t agree with mahibere kidusan is only its submission to the cruel politician and dictator Paulos to secure its existence and avoid removal by mad Zenawi. Had the legitimate Synod been in Ethiopia, I would say Mahibere Kidusan Could have done alot. One thing I have to say here is that even though Diakon Mulugeta’s Biblical explanations are right and don’t have substantive contradiction with what has been written by members of mahibere kidusan except manipulation of words in bad faith, there is something we have to smell beyond that. He has taken some position in advance and I am reading many totally fabricated accusations which we can’t expect from spiritual persons like him.
So, I am compelled to beg everyone to dig deep what this diakon is for our religion and beloved country Ethiopia. We have to interpret his attitude and know on whose side he stands. If he stands with crazy Zenawi and the evil patriarch, then we have to stand against him. If he stands for our religion and Ethiopia truly then his position against Mahibere Kidusan is not a big problem as at the end of the day they will have similar goal.
God bless Ethiopia and its people….death for dictatorship
Elias, what I have to beg you is that please follow what divisive policy Diakon Mulugeta is following like woyanne hodames. I swear to God, Diakon Mulugeta has some secret plan. Any one living in Ethiopia can understand who is learning Geez and Kidase even while attending higher education in Ethiopia? Diakon, are you crazy? If you are okay, please take time and consider what Mahibere Kidusan is. One thing I don’t agree with mahibere kidusan is only its submission to the cruel politician and dictator Paulos to secure its existence and avoid removal by mad Zenawi. Had the legitimate Synod been in Ethiopia, I would say Mahibere Kidusan Could have done alot. One thing I have to say here is that even though Diakon Mulugeta’s Biblical explanations are right and don’t have substantive contradiction with what has been written by members of mahibere kidusan except manipulation of words in bad faith, there is something we have to smell beyond that. He has taken some position in advance and I am reading many totally fabricated accusations which we can’t expect from spiritual persons like him.
So, I am compelled to beg everyone to dig deep what this diakon is for our religion and beloved country Ethiopia. We have to interpret his attitude and know on whose side he stands. If he stands with crazy Zenawi and the evil patriarch, then we have to stand against him. If he stands for our religion and Ethiopia truly then his position against Mahibere Kidusan is not a big problem as at the end of the day they will have similar goal.
God bless Ethiopia and its people….death for dictatorship
Betam ameseginalehu D/ Mulugta W/g. Enazihin abugnoch ena biltabilt ye haimanot
negedaiawoch linegarachew yigebal. Telatochacin Meles woyim Dr. paulos sayhonu enazih ye haimanto kadirawoch(mehibere kidusan ) nachew.
Ethiopia tebetsih habe egziaabeher. { Berta katil)
ስለግለሰብ ማውራት አቁሙ እትዮጵያ ችግር ላይ ናት ጠላታችን መለስ ብቻ ነው
kkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkk
kkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkk
kkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkk
I just wonder if people can be chited with your nonsence words. It is not about Eferem or MK,
you are trying to poisen the Orthodox Church blives and Dogmas, you are not from Orthodox why doe u worry? why don’t you write about TEHADESO, directly?
Insulting poeple or some one is none sence.
Diakon hono negerochn lemasredat sewechn mezilef, menak yelebetm new yager betun bahl restehewal diakon…
Muluget …poor… I think you are getting mad about MK. Let me advise you…just forget MK and restore your health. Really you are sick about it. Your bitter but trash words are telling how you are sick about MK. Otherwise, you will go soon to the street. May God help you.
TW.
Mulgata
Why you want to write all this lie sitting in USA? Why not you go to school and change your life. I think most of Ethiopia know what is good and what is bad at this time. Any way let God forgive for all your sin.
At Mk did something great but most of the church people, ….. not better than Woyane. All people are tired of finding the true Deacon and priests.
ይህ ሁሉ ተራ ነገር እና እባክህ ዲኮን ሙሉገታ አንተም ሲሂተቲህን ዛረ ተማር ለመሁኑ ቅነ ማወክ ከኪርሲትና ጋር ምን አገናግነው; ዪሀን የምቲሉ ይበሰበሰ ባሂላዊ እንጂ ሃይማኖታዊ ያልሆነ አትሰሳሰቢህን ዪዘህ እንደ አዋቂ ኪዳሰ ዉዳሰ ቲላለህ……
u are usless too !!!
In this difficult time what made our church weakening is the division of two brothers from same mother womb fighting one another for nothing. As we all know kayel killed his brother Abel because of Jealousy and he do not love God. Today we see two brothers writing each other and their letters have no spiritual content inside and is not expecting from followers of Jesus. Everybody wants to be a leader, preacher, named famous and get credit by writing too much but is it what is expecting from the so called Christian????
In the Holy Scripture it is written that Jesus told his disciples to serve one another in respect and Love and Jesus made himself as an example before them and washed their feet. So what is the purpose of celebrating the Holy Thursday and washing our feet one to another? If we don’t do it with love that is fake and we are joking on our selves. Jesus also told us In Mathew 20:26 “Whoever wants to be a leader among you must be your servant. So what are we doing today? Everybody wants to be a teacher…everybody carried the same holy book but deep inside we are divided. In this kind of life we can’t join the kingdom of God instead we are opening the door to our enemies to divide us much more and we are reveling our secret to DOGS. The bible says Matthew 7:6 “Do not give dogs what is sacred; do not throw your pearls to pigs. If you do, they may trample them under their feet, and then turn and tear you to pieces.
And we have to always understand before criticizing one to anther someone must see himself and the bible tell us in Mathew 7:5 “You hypocrite, first take the plank out of your own eye, and then you will see clearly to remove the speck from your brother’s eye.” So criticizing one another or talk back or re- writing to defame individual personalities does not help our church to grow. So let we unite and do what is Holy and love in one another
Ye Egizabher chernet ye dingil Mariam amalajinet ayleyen Amen!!!!!!
Wesbihat le egiabher
I just read some of your articles and just from your first sentence, I can guess what you are going to talk about. May be I am mistaken but I should tell that I am bored of your very narrowed attitude of things.
Why is it always our problem to think only ourselves are right? Come on man, your brother Ephrem said he doesn’t agree with his own understanding. But the way you gave a title is a bit rude. Is that you who think as if you are right and others like Mahbere kidusan are completely joke?
Take note of your self man, I don’t know what is you are in but I Just want to say, We know we have alot of problems here and there. Others may not be right as so do we. Lets make our selves better. The one who respect and tolerates others, not too quick to blame others. I see that you are respected “Diakon”, please write some posts about how we love eachother more, how to share our happiness and hard times together and forgive each other.
Cheers,
P.S. Sorry for my poor english, and I couldn’t write with amharic too since I am new to commenting .
Guys,
I don’t think Mulugeta is a Deacon at this time but the lost Mergeta or Kesis trying to get attention through his attacking articles. He knew the church words very well except the blessings and performing good things. So He uses them twisting to attack people. Look for instance, about Dr. Fiseha, he was a professor at TikurAmbessa and MD doctor, He got new idea, he opened college and then university and helped thousands, become a publisher unity Gazetta and radio(unity) to help us to learn each other, and many more others things. He is our mentor. He showed us practically if it were really possible to work without involving in politics in Ethiopia. But, impossible. Now he started another new idea, to establish new transitional government with full freedom for every group, I think this may be good for woyane too to transfer his govt. without blood shed. So, why he is attacking him?
Mulugeta is abusing the good people siding Woyane. Though I am not MK, I knew almost when they started and up to now. So they are ‘ le bete christianiachin, Yequrt qen Lijoch neberu, nachewum ‘ so I have a credit for them. Still there are genuine people among them working hard. When there are getting bigger in number, I think those sneaky wayane joined them and created contradiction on the behalf of them with other church fathers.
So my call is let us give them credit for their previous good work and keep giving them our support instead of dragging them to the ditch where woyane want them to be.
Besides, as human beings there are mistakes, so when there are mistakes let us try to fix and go with the right direction rather than accusing and demolishing the whole activity and story that was done on crucial time that required great scarification.
Really!! with no doubt this man Mulugeta is typical woyane serving as sleeper agent in the opposition camp.Mind you he seem to be in woyane’s pay roll to dispell woyanes venomous propaganda against Mehber kdusan in cordinated manner with ETV and Crime mnister .We have witnessed how his crime minister branded Mahber Kudsan as terrorist organization,with the same breath woyane Mulugeta echoing the woyane cheap propaganda right in our back yard by using such websites managed by forces opposing the woyane thugs.I think it is time that woyane Mulugeta has to be challenged aggressively and exposed before too late.Becuse what this guy repeatedly writes on various issues calls to question why he ,at this particular moment, engaged in lambasting Mahber kdusan ?
እባክህን በምታወጣቸው ስድብ በተሞሉ መጣጥፎችህ ላይ የክህነት ስምህን ባትጠቀምበት ስውን ከመሰናከል ታድናለህና አስብበት!!!ብትችል ተሳዳቢነትህንም ብትተወውና አቑምህን ብታራምድ ጥሩ ነው::አመሰግናለሁ!!!
Mulugeta W/Gebriel (??Deacon,)
I would like to say one thing on your response to the article by Deacon Ephrem Eshete. If you really are a Deacon and religious enough to cry towards God about your sins for His forgiveness, you shouldn’t have opened your mouth the way you did. By using foul language not expected from a humble Christian, you just elongated your list of sins. Your whole article was filled with hatred clearly depicting you as a lonely and tired person. You have thrown away the grace of God and are constantly haunted by your fear. Look into yourself and you will really know what I am talking about. You first need to sit down, pacify your soul and come in good terms with yourself. You, for the time being, need to forget your ambition to inform and teach others about politics or religion. Have the humility to accept that God always has his own humble persons to pass his words, those who don’t quench their thirst by rebuking others. If you are someone who is deliberately twisting words to confuse others for one or other reason, then you are really cheap and deserve no due attention. Either way, you need to save yourself from yourself and it will be much better the earlier you do it. You may not always get the chance that awakens you from your lust for dividing people in the pretext of defending the truth. Let God give you the heart that is willing to judge yourself but not others as the book says: “Don’t judge for you will be judged.”
Ladies and gentle men:
Please be kind and considerate when you write any commentary. Practice what you preach. Be polite even if you disagree with anyone’s idea. Make sure you make your points precisely, but be respectful and make sure your criticism is based informed ideas and reference materials to support you claim.
Labora,
thanks you nailed him. I guess he has lost his ‘kihnet’. Mostly those who has lost their ‘kihnet’ do such trash gossips being hidden in the back of the public. Sneaky man.
Amesale Dabilose,Ye Satenael Yegebre Lege,Menafeke,Kesati,Alawi,Hasawi,Achberbari “Diacon” Tenektobachehuale.Paster Godolo beyahalehu.Haimanote ena Megbare Godolo Menafeke.
Your comments odors asif you are Pastor.Pastor Mula Lebona yesteh Fetariachen Medhanialem.Lebona yesetehe Amelakachen Medhanialem.
I think your brain is full of poison.
እኔ ምለው አንጎልህን አውጥተህ ፈጥፍጠኽዋል እንዴ?
ሙሉጌታ ለስድብ አፉን በከፈተ ቁጥር ባዶ ጭንቅላቱ ይታያል::