የአማራ መደራጀት አስፈላጊነትና ድጋፍ

የጐንቻው

የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ ሰሞኑን የአማራውን መደራጀት አስመልክቶ ከአንዳንድ ታዋቂ ሰዎች፤ ምሁራኖች፤ ተቆርቋሪ ወገኖች የቀረበውን ወቅታዊ ጥሪ ለመደገፍና የበኩሌንም አስተዋጽዖ ለመግለጽ ነው።

የአደረጃጀቱ ይዘትና አቋም እንደ ብሄረ የፓለቲካ ድርጅት (ፓርቲ) ሳይሆን ካለው ተጨባጭ ሁኔታ ተነስቶ፡ እሮሮ አሰሚ፤ አቤቱታ ለዓለም አቅራቢ፤እንባ ጠባቂ፤ የሰብዓዊ መብት ጥሰት አስከባሪ፤ ዓይነ ቁራኛ ጠባቂ እና እንደ ሁኔታውና አቅሙ ደግሞ የማቴሪያልና የሞራል ድጋፍ ሰጭ ግብረ ሃይል ይሆናል።

ይህንን ሃሳብና አደርጃት ተከትሎ ጥያቄ ለሚያንሱ ሁሉ፦

፩. ለወያኔዎችና ተቀጥላዎቻቸው፡- ይህንን አጋጣሚ ተጠቅመው የተጀመረውን የጥምረት፤ የመቀራረብና የአንድነት መድረክ እንዲሚያፈርስ አድረገውና፤ አስመስለው ወሬ ለሚያነጉቱ፤ በየመደረኩ ለሚንጣጡና እንደ እግር እሳት ለሚፈጃⶨው ሁሉ፤ በደም ብዛት ድብን በሉ እንጅ ማንም አይሰማቹሁ በሏቸው።

፪. በተቃዋሚ ጎራ የተሰለፉ ፓርቲዎችና አባሎቻቸው፦ ድንገት ለሚያድርባቸው ስጋት፤ ይህ አደርጃጀት አማራውን አጎልብቶ ለእነርሱም የበለጠ የትግል አጋር ለመፍጠርና ተሳትፎውን ለማጠናከር እንጂ የተለዬ የመገንጠል አጀንዳ (ጉዳይ)፤ አባዜ አይኖረውም፤ እንዲያውም የመረጃ፤ የሃሳብና፤ የልምድ ልውውጥ፤ ድጋፍ፤ ከእነርሱም፤ ሊቀበልና ሊሰጥ ይችላል።

፫. የአማራው ብሔር ተውላጆች፦ ይህንን ሃሳብ የብሔር ፓርቲ እንደማቋቋምና ትንሽ ወያኔያዊ አካሄድ አድረገው ሊያስቡት ይችላሉ፤ አንዳንዶቹም ‘የማይወግኑ’ መሆናቸውን ለማስረገጥ ብዙ ሊራቀቁበትና ሊያወግዙትም ይችላሉ፡ እናንተም በማይቋጭ ሃሳብ አንጋጣችሁ፤ ስታንቃቁ፤ የሃሳብ ጎርፍ አንጋግቶ እንዳይወስዳችሁ፤ ምድር ጥግ ያዙና፤ አደብ ግዙ፤ እስኪ ቢያንስ ለአዲስ ሃሳብ እድል ስጡ።

ወያኔ በአማራ ላይ የደቀነው አደጋ፤የክፍት፤መቀመቅ ጥልቀት፦

የዚህ ጽሁፍ አቅራቢ ወያኔ በማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ በየክልሎች፤ ትግራይን ጨምሮ የሚያደርሰውን ግፍና በደል እንደማንኛውም ዜጋ ጠንቅቆ ይረዳል፤ በብሶትና በስቃያቸው፤ በትግላቸው ሁሉ እረፍትና ሰላም አጥቶ ሲዘግብ ኖሯል።

ነገር ግን ወያኔ በተለይ፤ በተለይ፤ በአማራ ላይ ጥሎበት፤ ከሰላሳ ዓመታት በላይ ያቀነቀነው መቀመቅ የሆነ ሴራ እንዳለም ይረዳልና በይበለጥ ለመደራጀቱ፤ሃሳብ ድጋፉን ይሰጣል፡ የሴራውን ጥልቀት እስካሁን ጠንቅቀን የተረዳነው አይመስልምና መንቃት አለብን ባይም ነው፡፡

በመጀመሪያ አማራ ስለ ሃገሩ፤ ስለ ባንዲራው፤ ስለ ድንበሩና ስለ መንግሥቱ፤ እንደ ቅድመ አያቶቹ ሕይዎቱን እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሳይሳሳ የሚሰዋ ጀግና፤ ጨዋ፤ሰው አክብሪ፤ ፈጣሪውን አማኝ፤ ትሁትና ምስኪን ሕዝብ ነው። በተለይ በኑሮው አብዛኛው፤በግብርና ሙያ የሚተዳደርና የንብረትና የሃብት ክምችቱም ከእጅ ወዳፍ ዓይነት ነው። እንደ እውነቱ ከሆ ‘የክት’ ከሚላት አንድ ግጥም ልብሱና ምናልባትም ደግሞ ‘ለከፈን (አስከሬን ልባስ) ብሎ ቆጥ ሰቅሎ ከሚያኖራት ነጠላው በስተቀር የዘውትር ልብሱ እርቃነ ስጋውን እንደነገሩ ብቻ በምትሸፍን ‘የተጠቃቀመች ድሪቶ’ አገልድሞ በትክሻው የፍየል፤ የበግ፤ ወይም ከከብት ቆዳ የተሰራች፤ ‘ለምድ’አንጠልጥሎ በባዶ እግሩ፤ እየኳተነ ሜዳ፤ተራራውን ቆፍሮና አርሶ የሚያቀና፤ የሚያለማ፤ ኑሮውን ላቡን አንጠብጥቦ የሚቋቋም የመንግሥት ግብርና እዳም ከፋይ ጭቁን ሕዝብ ነው።

ሐቁ ይህ ይሁን እንጂ፤ወያኔዎች ለተነሱበት እኩይ አላማ ይረዳቸው ዘንድ የትግራይ ወገኑን በጥላቻና በቂም በደል ብሎም ለዓመጽና ለጦር ይነሳሳበት ዘንድ የአማራውን ስምና ክብር የሚያጎድፍ ጥላሸት ሲቀቡት ኖረዋል። አማራው ከሰማይ ዝናብ እንዲሚጦልባቸው፤ከምድር ማዕድን እንደሚሰርቃቸው፤ ከአውድማ እህል እንደሚነጥቃቸው አንዳች፤ሰይጣናዊና አስከፊ አድርገው በምናባቸው ሲስሉና በአምሮቸው ብራና ሲቀርጹ ባጅተዋል ለዚህም ከሰላሳ ዓመታታ በኋላ ሊፍቁት አልቻሉም፤በምድር የሚያዩትን ገሃድ መቀበል አቅቷቸው፤ አሁንም ያንንው የውንብድና ድግምታቸውን ነው የሚያነበንቡት።

መጥፎ የታሪክ አጋጣሚ ሆኖ አያት ቅደመ አያቶቹ ከመላው ኢትዮጵያዊያን ጋር ሆ ብሎ አማራው ጎራዴውን መዞ፤ለቨን ውጅግራውን አንግቶ ከጠላት ጋር ጉሮሮ ለጉሮሮ ተናንቆ፤ትልቅ ታሪክ፤ገድልና፤ድል ለኢትዮጵያና ለዓለም አስመዝግቦ አጽማቸውን አቆላልፈው ከወደቁባት ‘አድዋ’ ምድር በበቀሉ፤ ጥቂት የሰው ቂጥኞችና፤በሆዳቸው ከሚገዟቸው ደንገጡሮች ጋር በሸፍጥ አብረው በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊያን ላይ የአወጁት ወያኔዎች፤ ሕዝብና አገራችንን ከስሩ ገዝግዞ ለማምከን ሳያሰልሱ የጥፍት አባዜአቸውን ያውርዱባናል።

አማራው እንዳይሞግታቸው፤እንዳይቋቋማቸው እጅግ ‘የረቀቀ መሰሪ’ ደባ ሲፈጽሙበት ኖረዋል፤እየምፈፀሙበትም ይገኛሉ።

ለምሳሌ፡

አማራውን ሕዝብ ትጥቁን አስፈትተው የምርኳዙ፤ ሚዛን መጠበቂያ ‘ጀንፍ’ እንኳ ሳይቀር አስወልቀውታል።
እንኳንሥ ዝናርና ጀበርና በወገቡ ሊያዞረ ቀርቶ ወፈር- ጠንከር ያለ ቀበቶም እንዲታጠቅ አይፈቅዱም፤
በትምህርት በልማት፤ ሆን ተብሎ ወደ ኋላ እንዲቀር ተደርጓል፤
የአካባቢና የተፍጥሮ ሁቡቱ፤መሬቱ ሁሉ ተነጥቆ እስከ ወዳኛው ትውልድ እንዲያፍር እንዲከስር እንዳያንሰራራ፤በማቀድ ይባስ ብለውና ከክፋታቸው መብዛት መሬቱና ግዛቱ፤ለአማራ ከሚሆን ለባዕድ አገር፤ ለሱዳን ቢሆን ይመርጣሉ፤ይህንን በተግራር እያስመሰከሩ ነው፡፤በቅርቡም በጎንደር የወልቃይት አረሶ አደሮችን ገድሎ ከሚነጥቅ የሱዳን ተዋጊ ሰራዊት ጋር በአሻጥር ያስወጉታል።
ኧረ ስንቱ! የጥፋታቸውና የክፋታቸው እርቀት መጨረሻ የለውም፤ በየጫካው፤በየዋሻው፤በየእስር ቤቱ ጅምላ ያጎሩትን፤ገድለው የጣሉትን ቁጥሩን ማን ያውቃል? ቀን ሲወጣ አምላክና ሕዝብ ይቁጠረው። የአማራ ህዝብ በሚሌኖች ቀንሷል። አስረው፤ የሚገርፍት፤ የሚሰድቡት፤ መቀጣጫ የሚያደርጉት፤ በብሄሩ፤ በአማራነቱ ነው።
የአማራን ስምና ክብር በውጭ መንግሥታትና ተቋማት፤ማስጠፍት የዲፕሎማሲያቸው አንዱ ዘርፍ ነው። ለምሳሌ፤ በጡረታ ዘመኑ ሲቪል ሰርቪስ አግልግሎ ከመጣ አንድ ምዕራባዊ ጡረተኛ አፍ ስለ አማራ ‘ጸረ እድገትና ልማት፤ስንፍና ስለ ትግሬ ታታሪነት’ የተተረከለትን ሲፈተፍት፤ ሰምቼ በግል ለከረረ ጸብ ደርሰን ነበር።
አማራው ፍጹም ያልሆነውን ሆነ፤ያልፈጸመውን ፈጸምክ ብለው እንደመንግሥት የስልጣን ኮርቻ ላይ ተፈናጠው ፤ ፓሊሱ፤ ወታደሩ፤ ደህንነቱ፤ መሳሪያው በእጃቸው፤ ለ፳፩ ዓመታት ሲቀጠቅጡት ኖረዋል። ይህ ሕዝብ ለመንግሥት፤ለሕግ፤ ካለው ክብርና ቀናዒነት፤ በተጨማሪ ሌላውንም ወገኑን (ብሔረሰብ) በተወሰነ ደረጃ በጥቃት ረድፍ አስልፈው ስላስወጉት፤በስሙም ድርጅት (ብአዴን) ጠፍጥፈው፤ ስላዳከሙትና ስላዋከቡት፤ግራ አጋብተው፤መራራ ሕይዎቱን እንዲግፋ አስገዳዱት፡፤
‘ነፃ ነህ ምረጥ’ ብለውም ከመቅጽበት መሪዏችን እስርቤት ወርውረው እርሱን መሬት በመንጠቅ አስክ ዜግነት መብቱ ገፈው ፍዳ አሳዩት፤በተወሰነ ደረጃ አጋጣሚ ያገኙትም ‘ተወካይዎቹ’ ሲክዱት፤ ወይም አብረው ሲጨፈጭፉት ታዝቧል፡፡
ከትውልድ ቀዬው መሬቱን ይነጠቃል፤ ይባረራል፤ ሌላ ክልል ይሄዳል፤ ወደ ባዕድ አገር በህሕዎቱ ቆርጦ ይሰደዳል፤፡
በሌላው የኢትዮጵያ ክልል ሄዶ በቀን ሥራና በረዳትነት ተቀጥሮ አቅማና ሕጉ ሲፈቅድለት መልሶ ኑሮ ሲያቋቁም እንደገና ተከታትለው ያፈናቅሉታል፤ያሳድዱታል። ይኸው በቅርቡ በማጅ ዞንና ‘ጉራ ፋርዳ’ ወረዳ እንደታዘብነው።

በጣም እጅግ ያሳዝናል! ይሕ የሚዘገንን ዜና ዐለምን ሲያዳርስ ቆይቶ እቦታው ላይ የተቀመጡት የነገሩ አራጊና ፈጣሪ ወይም ተላላኪና አስፈሳሚ አቶ ሺፈራው ሽጉጤ ድምጻቸውን አጥፍተው ከርመው እነሆ ከርስ በሆዱ እንደዛቀ ቅንቡርስ የሰው ቁርበት በተላበሰው የቆዳ ሶፋቸው፤ምቾታቸው ላይ ተሸጉጠውና ተዘርፍጠው ያፈናቀልኩት ፰፻ ወይም ፰፲፻ እያሉ ይሳለቃሉ፡፤ የሥራ ባልደረባቸው፤ አቶ ሳጂን ምስክር (የፓሊስ አዛዥ) ስለ ክቡር የሰው ኃይዎት ኅልፈት፤ አቶ እምቢበልን ደብድበው እንዴት ለሞት አንዳበቁት ሲጠየቁ፤ ሳቃቸው ነው የቀደማቸው፡ የራሳቸው ልጅ፤ ወንድም፤ እህት፤ አባት ሚስት ቢሆን ኖረ እንዲሁ ሳቅ በሳቅ ይሆኑ ይሆን? ለነገሩ፤ እንደሳቸውና እንደመንግስታችው የገደሉት አንድ ወገን፤ ተቆርቋሪ የሌለው (የሌላቸው) አማሮች ናቸውና አስጠይቋችው አያውቅም። ግን ያለንበት ዘመንና ጊዜ በፍጥነት ተለዋዋጭ ነውና ማን ያውቃል በዚህ የተዋጣለት ሳቅ ከቀጠሉ፡፤

ወያኔ እንደ እነ አቶ ሽፍራው ሽጉጤን መሰል ከየብሔረሰቡ የወሸቋቸው የሰው ደም የሚጋቱ፤ብዙ ደንገጡሮች አሉት።

በማጅ ዞን በጉራ ፋርዳ ወረዳ አማራን ነጥሎ የመምታት፤የማዋከብ አደጋ በነዚህ ጎጅሌ ዘረኛ ቁንጮዎች ተቀነባብሮ የሚፈጸም፤ የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው፡፤ ኢትዮጵያዊ በሙሉ፤ አማራም ልብ በል፡ ተጠንቀቅ፡ ለዘላቂ መፍትሔ ተዘጋጅ፡ ብዙ ጋህዶች፤ በፊታቻን ተደቅነዋል።

ወያኔ በአሁኑ ጊዜ በአራቱም አቅጣጫ የጥፋት ሰደድ ለኩሷል፡ ለጊዜው የሚፈጀው አማራን፤ጋምቤላን፤አፋርን፤ኦሮሞን ቢመስልም፤የተቀጣጠለችው የጋራ ቤታችን፤አገራችን ኢትዮጵያ መሆኗን አትዘንጉ። በመጨረሻ አቀጣጣዩም ይጋያል።

የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ወገኖቻችን፤ወያኔ በእምነታቸው ጣልቃ ገብቶ ባደርሰባቸው እጅግ ነወረኛና አስጸያፊ ተግብር ምክንያት ከተፋጠጡ ሳምንታት አስቆጥረዋል፤

በጋምቤላ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ነዋሪ ዜጎቻችንን እያፈናቀሉ፤እርስት መሬታቸውን ቀምተው ለባዕድ አገር ቱጃሮች፤ እየቸበቸቡ፤ በተፈጠረው ሕዝባዊ ተቃውሞ የፌደራል ወታደር ዘምቶ፤ቤት ጫካ አደባባይ ወሮ፤እያሰሰ ሰው አነጣጥሮ በየቀኑ ይገድላል።

በአፋርና በኦጋዴንም እንዲሁ፤

በቅርቡ የተነሳው ተቀጣጣይ የመምህራን አድማና የመንግሥት ዛቻ፤ከመጠን ያለፈ መቀጣጫነት የሚያስከትለው መዘዝ፤

በዋልድባና በታሪካዊ ገዳማትን በማረስ፤ የጻድቃንን አጽም በመቆፈር፤ ገዳማታን በማቃጠል፤ የቃጡት፤ፍጹም የሆነ ሰይጣናዊ ተልኮና የህዝቡ፤ የእመነቷ ተከታዮች ቁጣ፤

‘ቴሬሪዝም’ በሚል የጥፋት አዋጅ ዜጎችን በገፍ እያንጋጉ ‘እደሜ ይፍታችሁ’ አሳር፤ የማንን እድሜ ያሳጥር ይሆን?

እነሆ እንደዚህ አጣብቂኝ የገቡ ‘ተናካሽ አውሬዎች’ እና የጥፋት መልዕክተኞች፤ ፍጻሚያቸው አፋፍ ላይ ሲደርሱ፤ የፍራትና አጥፍቶ የመጥፋት በትራቸውን በዚሁ አለአበሳው በጠላትነት በፈረጁት አማራ ብሄረሰብ ላይ እንዳያሳርፉ ከፍተኛ ስጋት አለ።

ስለሆነም፡ይህንን የተደቀነ አደጋ ለመካላከል፤ለመመከት፤ለማጋለጥ፤ለዚህ አስቸኳይ ጉዳይና ድንገተኛ ሁኔታዎችን ለመከታተል የአማራ ሕዝብ ለማዳን መደራጀት እጅግ አስፈለጊና በጣም አጣዳፊ ተግባር ነው።

በድጋሜ ለማሳሰብ ያህል ይህ አደረጃጀት የተደቀነውን አደጋ ነቅቶ ለመጠበቅ እንጂ የአማራ ሕዝብ ዘለቄታዊ ህልውናና ፍላጎት ከመላው የኢዮጵያ ሕዝብ ጋር በአንድነት በሰላም፤በፍቅርር አብሮ መኖር ብቻ መሆኑ አያጠያይቅም።

ይህንን ሁሉ የአደባባይ ሚስጥር ማብራራትና ከዚህ በላይ እንደተተነተነው በሃተታ ለመዘርዘር ያስፈለገው ብዙ ሰበብ ፈላጊ፤ፈሪ፤አስመሳይ፤አሳሳች ስላሉ፤ ቀዳዳ ለመድፈን እንጂ እውነታው ያፈጠጠ ገሃድ ነው።

ማጠቃለያ፡
አለማቀፋዊ የአማራ ድርጀትና ድጋፍ ሰጪ በአስቸኳይ እንዲቋቋም፤ይህ ሕዝብ አይዞህ የሚለው፤በመከራ ሰዓት ጠበቂ ያስፈልገዋል፡ ቆርጦ ከተነሳ ጀግንነቱን ያውቅበታል፤ኬላውን ሁሉ ዘግቶ በፍርሃት ብርክ አስይዞ እጅ ያሰጣቸዋል፡ሃይል የፈጣሪ ነው፡፡እስካሁን ዝም ብሎ የመከራ ገፈታ የቀመሰው ሁሉም በጠላትነት የፈረጀው ስለመሰለው ይሆናል፡

አደረጃጃቱን ሞያዊ ተክⶈና ልምድ ያላቸው እንዲሰሩት ሆኖ በቅድሚያ ለአሰራር፤አመችነት፤ሎጆስቲክስና ቅንጅት የአማራ ብሄር ተውላጆችን ቢያቅፍም በመንፈሱ፤ሁሉንም የሚይቅፍና፤ የሚደግፍ፤ ምክርና ድጋፍ የሚቀበልም የሚሰጥም ይሆናል፡፤

ከዚህ ባለፈ ጸጉር ለምትሰነጥቁ፤የወሬ ጎፈሬ ለምታበጥሩ፤ ከነሚዷቹሁ ወደ ጓዳ ቆዩ፡፡

የዚህ ጽሁፍ አቅራቢ ምንጊዜም ኢትዮጵያዊነቱን የሚያስቀድም ሲሆን ለዚህ አጣዳፊ ጉዳይ ምላሽ በአማራ መደራጀትና አደረጃጀት ላይ ደግሞ የበኩሌን ድጋፍና የተጠየቀውን ሁሉ ለመክፈል ሙሉ ዝግጁነቴን በቁርጠኝነት ለመግለጽም ነው።

ትግል እሰከመስዋትነት!
አምላክ ኢትዮጵያን ይባርክ!
የጐንቻው! [email protected]