ሀገራዊ ጥሪ በሻርለትና አካባቢው ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን

ሀገራችንን ረግጦ በሕዝባችን ላይ ሊደረግ ቀርቶ ሊታሰብ የማይችለውን የግፍ ዓይነት ሁሉ በማከናወን ላይ የሚገኘውን የአምባገነንና ዘረኛ ቡድን በሕዝባዊ እምቢተኝነት አሽቀንጥሮ ለመጣል በሚደረገውና ሊደረግ ይገባዋል ብለን በምናስበው የትግል ስልት ሁሉ መወያየት ለተግባራዊነቱም መንቀሳቀስ ስለምንችልባቸው ጉዳዮች ላይ ሁሉ በመምከር ታላቅ የታሪክ አደራን መወጣት ያስፈልጋል። ስለሆነም የኢትዮጵያ ሕዝብ ስቃይና መከራ መከራዬ ነው ብለው ካመኑና በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለው ኢሰብአዊ ተግባርና በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ላይ ያነጣጠረ አፍራሽ ሂደት መገታት የሚችለው የጠባቡና የአምባገነኑ ቡድን መወገድ ነው ብለው ከወሰኑ በኢትዮጵያውያን መካከል በሚደረግ ግልፅ ውይይት ተሳታፊ እንዲሆኑ ሀገራዊ ጥሪ እናደርጋለን።

የስብሰባ ቀን ስዓትና ቦታ
CountryHearth INN
February 27, 2011 at 3:30 PM
5301 Equipment Drive
Charlotte NC