አስራ አንደኛው ሰአት ለወያኔ ወይስ ለህዝቡ
ዋለልኝ መኮንን
ኢትዮጵያ ላለፉት ረጅም አመታት በተለያዩ ጨካኝና አምባገንን መንግስትና የመንግስት ስርአቶች አስተናግዳለች::እነዚህም ስርአቶችን ለማስወገድ ከፍተኛ መስዋትነት ተከፍሉል አሁንም እየተክፈለ ይገኛል:: አሁን ኢትዮጵያን አስተዳድራለው የሚለው የወያኔ ቡድን ከሁሉም የባሰውንና በታሪኩ አይቶ የማያውቀውን ከፍተኛ ግፍ:በደል:ጭቆናና ውርደት በሕዝቡ ላይ እያደረሠበት ይገኛል:: አምባገነኑና ፋሽስታዊው የወያኔ ቡድን ላለፉት 21 አመታት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ በጉልበት: እጅግ በጣም ሁዋላ ቀርና የህዝብን ጥቅም ይማያስጠብቅ የአገዛዝ ስርአት በመጫን የስልጣን ዕድሜውን ማራዘም; የአገር የማፈራረስና የኢትዮጵያዊንትን ታሪክና ባህልን የማጥፋትና ተልኮውን መፈጸም እና የህዝብና የሀገር ሀብት መዝረፋን መጠነ ሰፊ በሆነ ሁኔታ እየፈጸም ይገኛል::ህዝቡን በጥመንጃ በማስፈራራትና ከታች የተዘረዘሩትን ተፈጥሮዊና ህገመንግስታዊ መብቶችን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በመከልከል የባንዳንትና የሌብነት ተግባሩን በመፈፅም ላይ ይገኛል::
-ህዝቦችን በዘር: በብሄር: በቋንቋ: በሀይማኖት: በቀለም: ብሎም በጎጥ እንዲለያዩ ማድረግና ክፍተኛ የጥላቻ ፖለቲካ ቅስቀሳ በህዝቡ ዘንድ ማሰረጨት:: እርስ በእርስ እንዳይስማሙ: አብረው እንዳይኖሩ: አንድንት እንዳይፈጥሩ: በህብረት ማህበራዊና ፖለቲካዊና እኮኖሚያዊ ችግሮቹን እንዳይፈቱ: የሀገር ውስጥና የውጭ ጥላቶቹን ለመታገል አቅምና ስምምነት እንዳያጎለብቱ በዘር ፖለቲካ እንዲወጠሩ ማድረግ: ከእያንዳንዱ ብሄረሰብና ሀይማኖቶች ለሆዳቸው ያደሩትን ጥቂት ግለሰቦችን ቆንጥሮ እምነትህ ቀቀንቀህ ባህልህ ጥቅምህ ተከብሮልሀል ብሎ በህዝብ ላይ መሳለቅ::
-በርካታ የህዝብን ተፈጥሮዊና ህገመንግስታዊ መብቶችን፧የመናገር:የመፃፍ:የመሰብሰብ:በቡድን የመደራጀት:ሀሳብን በአደባባይ ወጥቶ የምግለፅ: በሀገሩ ላይ የመሬት ባለቤት መሆን: የፈለገውን እምነት መከተልና የመሳሰሉትን በኢትዮጵያ ተፈፃሚ እንዳይሆኑ ማድረግ ወይንም በመሸራረፍና ለጥቂት የወያኔ አባላትና ደጋፊዎች ብቻ ተፈፃሚ እንዲሆን ማድረግ::
-ታዋቂና ለወደፊት ለአምባገነኑና ለፋሽስቱ ለወያኔ ቡድን የስልጣን ቆይታ አደገኛ ሊሆኑ ይችላሉ ብሎ የሚያስባቸውንና በህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነትና ታማኝነት ያላቸውንና አላቸው ብሎ የሚጠረጥራቸውን የተቃዋሚ የፖለቲካ መሪዎችን: አባላቶችን: ደጋፊዎችን: ምሁሮችን: መምህራኖችን: ጋዜጠኞችን: ዘፋኞችን: ነፃ አሳቢ ዜጎችንና በተለያዩ የዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ላይ የሚሳተፉ ግለሰቦችን ማስፈራራት:በእስር ማሰቃየት: በአካላቸውና በስነልቦናቸው ላይ ጉዳት ማድረስ:ንብረታቸውን መውረስ መዝረፍ ማውደም: አስፈራርቶ ከሀገር እንዲሰደዱ ማድርግ: የት እንደደረሱ እንዳይታወቅ ማድረግ: መግደልና ሌሎችንም የመሳሰሉ ወንጀሎችን በመፈፅም ሀገር የማፈራረስ ህዝብንና ሀገርን የማዋረድና የባንዳነት ተልኮውን መወጣት::
-ለህዝብ ዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ በጣም አስፈላጊ የሆኑ ለምሳሌ በሰባዊ መብት:በመልካም አስተዳደር:በህግ የበላይነትና የመሳሰሉ ጉዳዮች ላይ መጥነኛም ሆነ ጥልቅ ግንዛቤ እንዳያገኝና እንዳይኖረው ተግተው በመስራት ህዝቡ በዲሞክራሲያዊ ስርአቱ ግንባታ ላይ ምንም አይነት ተሳትፎ እንዳይኖረው ማድረግ:: ስለ ሰባዊ መብት መልካም አስተዳደር የህግ የበላይነትን ለህዝቡ በማስተማርና በማስረፅ ላይ የተሰማሩትን መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች: ነፃ ጋዜጦች: የራዲዮና የቴሌ ፕሮግራሞችን ሆን ብሎ የተለያዩ አፋኝና ሰንካላ ሰላማዊዮቹንና የብዙሀኑን መብት የሚያቀጭጩ የሌቦችንና የጥቂቶችን ቡድኖችን ስልጣን የሚያፋፋ ህጎችንና መመሪያዎችን አውጥቶ ለህዝቡ እንዳይደርሱ ማድርግ:: ህዝቡም መብቶቹን እንዳያውቅና እንዳይጠቅም ማድረግ::
-የኢትዮጵያን ህዝብ የሀገር የመሬትና የንብረት አልባ አድርጎ የወያኔ አባላት ብቻ የመሬትና የንብረት ባለቤት እንዲሆኑ ማድርግ:: ሀገርንና መሬትን ለባእዳን መሸጥና ለጎረቤት ሀገሮችም ትላልቅ መሬቶችን ቆርሶ በመስጥትን በመሸጥ አሳልፎ መስጠት; እኛ ብቅርጽና በመጠን የምናውቃትን ታሪካዊ ኢትዮጵያን ማጥፋት; ህዝቡም በሀገሩ ላይ ስለ መሬት እንዳይጥይቅ በጠመንጃ ማስፈራራት; ምንም እንደማያመጣ በጥጋብና በስድብ ንቀቱን መግለፅ::
-የኢትዮጵያን የ3000 አመት ታሪክ መካድ: አሳፋሪ በሆነ መልኩ ማቅረብ: ታሪክን መበረዝ: የፈጠራ ታሪክ መፍጠር:: የኢትዮጵያን ህዝብ ባህል: ስብእና: ዕምነት: ኩራት: ማንነት: ብሄራዊ እሴቱን: አንድነቱንና ብሄራዊ መገለጫዎቹን ማጥፋት:: የኢትዮጵያን ታራክ የወያኔን ታሪክ ብቻ አድርጎ በካድሬዎቹና ለሆዳቸው ባደሩ ተራ ግለሰቦች ገንዘብ ከፍሎ ማፃፍ:: ልክ እንደ ውጭ ጠላቶቻችን ኢትዮጵያዊነትን ማዋረድ: ማጥላላት: ማናናቅና የመሳሰሉትን አስነዋሪ የቅጥረኝነቱን ተግባር እየፈፅመ ይገኛል::
-በብሄርና በጎጥ የተደራጁ ጥቂት የወያኔ ማፊያዎች የሌብነት ተግባራቸውን በከፍተኛ ሁኔታ ለማስፈፅም ወንበዴ ዘራፊ ድርጅት ማቋቋምና ህዝቡንና ሀገሪቱን መዝረፍ: ማደህየት: ማስራብ: የበዪ ተመልካች ማድረግ:: በዘመናዊ ቤት መኖር: የብዙ ቤቶች ባለቤት መሆን: ዘመናዊ መኪናዎችን መቀያየር: በመቶ ሚሊዮኖች የሚጨርስ ህንፃና ፋብሪካዎች መገንባት ለወያኔ ብቻ የተፈቀደ እስኪመስል ድረስ ማግበስበስ:: በጣም የከፋው ደግሞ ከሀገርና ከህዝብ የሚዘረፈው ከፍተኛ ሀብቶች ከኢትዮጵያ ማሸሽና በተለያዩ የውጭ ሀገር ባንኮች መደበቅ ይህም ሳያንስ በባእዳን ሀገር በቢሊየን የሚቆጥሩ ዶላሮችን አውጥቶ ህንፃ መገንባትን ሥራዬ ብለው ተያይዘውታል::
-የኢትዮጵያ ህዝብ ትክክለኛ እውነተኛና ሚዛናዊ መረጃዎችን እንዳያገኝና በኢኮኖሚ: በማህበራዊ: በፖለቲካ: በዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ላይ ቀጥተኛ ተሳታፊ እንዳይሆን ማድረግ:: እኔ አውቅልሀለው የምነግርህን ብቻ ተቀበል ብሎ ህዝብን በወያኔ የመረጃ ማሰራጫዎቹ ማደንቆር:: ትክክለኛ እውነተኛና ሚዛናዊ መረጃዎችን ለህዝቡ የሚያደርሱትን የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር የመረጃ ተቃማትን የግል ጋዜጣዎችን ራዲዮዎች ቴሌቪዥን እና ድህረ ገዕች መረጃዎችን ለህዝቡ እንዳያደርሱ ለማድረግ አታሚ ድርጅቶችን መዝጋት: ፈቃድ መከልከል: ባለቤቶቹን ማስፈራራት: ማሰር: ከሀገር እንዲሰደዱ ማድረግ:: በራዲዮና የቴሌቢጅን የሚሰራጩትን መረጃዎች ከፍተኛ ገንዘብ በማውጥት ሞገዳቸውን ማፈን::
ወያኔ በጠመንጃ ስልጣን ላይ ከተቀመጠ ጀምሮ የኢትዮጵያ ህዝብ መብቶቹን ለማስከበር ያላሰለሰ ትግል እያካሄደ ይገኛል:: ሆኖም እስከ አሁን የተደረገው የትግል መስዋትነት የተፈለገውን ውጥት ማስገኝት አላስቻለም:: ለተፈለገው ውጠት አለመገኝት እንደ ምክንያት ሆነው የተቀመጥት; ብዙና የተለያዩ የትግል ስልቶችን አለመጠቀም: የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ ድርጅቶች በጋራ ተቀራርቦ አለመስራት: የፓርቲዎቹን አላማና የተለያዩ መረጃዎችን ሰብስቦ ወደ ህዝቡ ለማድረስ የሚያስችል ጠንካራ ተቋም አለመኖር: የአባላቶችና የደጋፊዎች ቁጥር አነስተኛ መሆንና ከአባላቶችና ከደጋፊዎች የሚሠበሠበው ገንዘብ በጣም አነስተኛ መሆን ከብዙ በጥቂቶቹ ናቸው::
የወያኔን ዘረኛና ፋሽስታዊ የአገዛዝ ስርአት ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ከስለጣን ለማስወገድ በመላው ኢትዮጵያ ከፍተኛ የሆነ የእኩልነትና የፍትህ ጥያቄዎች ከሁሉም አቅጣጫ እየጎረፈ ይገኛል:: ማንኛችንም የሀገሬ ሠላምና ደህንንት ይመለከተናል የምንል ግለሠቦችም ሆንን የፖለቲካ ፓርቲ ድርጅት አባላትና ደጋፊዎች በጋራ ተሰባስበን የተቀጣጠለውንና እየተፋፋመ የመጣውን ታላቅ የህዝብ አመፅ በሁለንተናዊ የትግል እስትራቴጂ እንዲታገዝ አድርጎ የወያኔን የማፊያ ስርአት ከጫንቃችን ላይ አስወግደን እኩልነት: ፍትህ: ዲሞክራሲና: እውነተኛ ፌደራላዊ ስርአት የሰፈነባት ኢትዮጵያን ለመገንባት ከሌላው ግዜ በበለጥ መረባረብ አለብን:: የወያኔን ሀገር የማፍረስ የመዝረፍ ታሪክን የማበላሸትና የማጥፋት ተልኮውን አሁን ተባብረን ማስቆም ካልቻልን መስዋቱ ውድመቱ የህዝብና የሃገር ውርደት የከፋ ይሆናል::