በመንግሥታዊ የዘር ማጥፋት ውስጥ የቤተ ክርስቲያን ሚዲያዎችና የሰባኪያን ሚና
በኦርቶዶክሳዊያን ላይ መንግስታዊ የዘር ማጥፋት (ጀኖሳይድ) በገሀድ፣ በስፋትና በተደጋጋሚ እየተካሄደባቸው እንደሆነ ይታወቃል። ባለፉት 15 ቀናት ብቻ አርሲ፣ ወለጋና ቤኒሻንጉል ጉምዝ ውስጥ ከ3,000 በላይ በኦርቶዶክሳዊያን በመንግታዊ ታጣቂዎችና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ሚሊሻዎች መጨፍጨፋቸውና ከእልቂቱ አምልጠው በመሸሽ ላይ የነበሩት ላይ አየር ኃይል በድሮን በርካታ ቁጥር ያላቸውን እንደፈጃቸው ማስረጃዎች ያሳያሉ። በርካታ ቤቶችና ቤተክርስቲያናትም ተቃጥለዋል። በመሆኑም ይህንን ጭፍጨፋ እየተከታተሉ ለህዝብ የሚያቀርቡ ኦርቶዶክሳዊ ሚዲያዎች ማድረግ ስለሚገባቸው ተግባሮችና መውሰድ ስለሚገባቸው ጥንቃቄ መምህር ፋንታሁን ዋቄ ከቀሲስ አስተርአየ ጽጌ ጋር እጅግ ወሳኝና ወቅታዊ ውይይት አድርገዋል። ቀሲስ እንዳሉት
“በሚዲያ ያላችሁ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን እንቆረቆራለን ያሳስበናል የምትሉ ዘመኑ ስለፈቀደላችሁ ሀይ የሚል ስለጠፋ እባካችሁ ሳትናበቡ የተለያየ ኢንፎርሜሽን እያመጣችሁ ህዝቦችን ጭንቅላት ላይ አትድፉበት። እባካችሁ ስለ እግዚአብሔር እባካችሁ ሰው የቱን ይስማው ሰው የቱን ያዳምጠው እንዴ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ካደጋችሁ መጀመሪያ ወደ ህዝቡ ከመቅረባችሁ በፊት እርስ በእርሳችሁ ተናበቡ ተነጋገሩ። ህዝብ ምን ይላል ምን ይነግረናል ብላችሁ ጠይቁ። እባካችሁ ሲሆን ከሁለት ሳምንት አንድ ቀን እርስ በእርሳችሁ ተነጋገሩ። በወር አንድ ቀን የራሳችሁ ጉባኤ ይኑራችሁ። ተራረሙ፣ ተደማመጡ። እናንተ የሚዲያ ሰዎች ዩቱብ ከፍታችሁ የምትጮሁ አንድነት ይኑራችሁ። ጸልዩ በእንተ ማህበረ የምትሉ ከሆነ መጀመሪያ የራሳችሁን አንድ ድምጽ ይኑራችሁ። በአንድ ሳምንት አንድ አጀንዳ ይዛችሁ ውጡ። የተዘበራረቀ ነገር እያመጣችሁ ህዝቡ ላይ አትድፉበት።
ከዚህም በተጨማሪ ቀሲስ ከአራጆች ጋር ማዕድ እየተቋደሱ መለስ ብለው ደግሞ የሚጨፈጨፈው ህዝብ የሚቀልባቸውና የህልውናቸው መሠረት ስለሆነ ህዝቡን የሚያወናብዱ እንደ መምህር ዘበነ ለማ ዓይነቶችን እውግዘዋል። “ዘበነ ወቅት እያየ የህዝቡን ቀልብ ለመሳብ የታለ ተብሎ ሲጠየቅ የጠፋ ላለመምሰል አቅጣጫ እየቀየረ የሚመጣ ሁሉ የማክዶናል ነጋዴ ነው ብዬ ነው የማየው” ብለዋል ቀሲስ። በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ የመምህር ዘበነ ለማን እንቅስቃሴዎች የሚከታተሉ ሰዎች እንደሚሉት ከሆነ መምህር ዘበነ ለማ በተለያዩ ጊዜዎች ህዝብን ማወናበዱንና ከቤተ ክርስቲያኒቷ ሥርዓት ውጭ መንቀሳቀሱን ይናገራሉ። ለምሳሌ ዓውደ ምህረት ላይ በተለያየ ጊዜዎች ላለፉት 20 ዓመታት ከተናገራቸው ቅጥፈቶች መካክል የሚከተሉት መጥቀስ ይቻላል፤
- ክህነት እየሩሳሌም እንዳልቀበል አቡነ ማቲያስ ስለከለከሉኝ አቡነ አብሳዲ የተባሉ አባት በግላቸው ክህነት ስለሰጡኝ የክህነት ማስረጃ አላቀርብም።
- አቡነ ጳውሎስ ሳልጠራቸው ነው ሰርጌ ላይ የተገኙት። (ፓትርያርኩን ድንኳን ሰባሪና ቀላዋጭ አድርጓቸዋል)
- የሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስ መስቀል በስጦታ ተበርክቶልኛል።
- የሊቢያ ሰማዕታት መታሰቢያ የጸሎት ዝግጅት ላይ ከተሳተፍኩ ከመንግስት ያነካካኛልና አልሳተፍም።
- አሜሪካ ከመምጣቴ በፊት ምዕመናን ከነጫማቸው ቤተክርስቲያን ውስጥ ይገቡ የነበረውን አስቁሜያለሁ።
ስለሆነም ቀሲስ አስተርአየ እንዳሉት መምህር ዘበነ ለማ የኦርቶዶክሳዊያን ደም እንደ ጎርፍ እየፈሰሰ በሚገኝበት ወቅት ገዳዮችን ማውገዝና ምዕመናን እራሳቸውን እንዲከላከሉ በመምከር ፋንታ ዘበነ ለማ እያወናበድ ሲለሚገኝ ከዚህ እኩይ ድርጊት እንዲታቀብ አሳስበውታል። ቀሲስ አስተርአየ በአክሱም ጽዮን ቤተ ክርስቲያን የተደረገውን ምህላ እንዲሁም ለቤተክርስቲያን ስትል እራሷን አሳልፋ ሰጥታ ቤተ ክርስቲያንን የታደገችውን ሮዛ ገብረሚካኤልን አመስግነዋታል። በአክሱም ጽዮን የተደረገውን ምህላ አስመልክተው እንዲህ ብለዋል
“በአክስም ያሉ እናቶች የተጨነቁ ሁሉ እስካሁን መከራው መከራው ጭንቁ ስቃዩ የነደደባቸው ሰዎች እናቶች የተሳተፉበት እንባ እግዚዎታ ነው። ጳጳስ አላየሁበትም፣ ቆሞስ አላየሁበትም። ጽላቱ ጃንጥላው ዲያቆናቱ ቀሳው ናቸው የመሩት። ህዝቡ ነው የጎረፈው። ይሄ እንግዲህ የነበረ በመከራ በጭንቅ በችግር የኢትዮጵያ ህዝብ ድምጹን ወደ እግዚአብሔር የሚያሰማበት መንገድ ይሄ ነበር። ትግራይ ላይ ዛሬ ምንኩስናው ጳጳሱ ከመጨቅየቱ በፊት ህዝብ እንዲህ ነበር ችግር ሲመጣበት ምህላ የሚይዘው። ጳጳስ ቆሞስ በሌለበት ዘመን በጳጳስ በቆሞስ ሰው ኮንፊውዝ ከመሆኑ በፊት አካሄዱ ይህ ነበር።