ለክርስቲያኖች መጨፍጨፍ ፓትርያርኩና ሲኖዶሱ ከተጠያቂነት አያመልጡም

ለክርስቲያኖች መጨፍጨፍ ፓትርያርኩና ሲኖዶሱ ከተጠያቂነት አያመልጡም

አብይ አህመድ ስልጣን ማማ ላይ ከተቆናጠጠበት ጊዜ እስከ ዛሬዋ ዕለት ድረስ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኦርቶዶክሳዊያን በኃይማኖታቸው ብቻ ተለይተው ተጨፍጭፈዋል፣ ተፈናቅለዋል እንዲሁም በርካታ ቤተ ክርስቲያኖች በእሳት ጋይተዋል።ካህናት በጠራራ ጸሃይ እንደ ኦሪት ዘመን በድንጋይ ተጨፍጭፈዋል። የቤተክርሲያን አገልጋይ ዲያቆን በአደባባይ ተረሽኗል። ጭፍጨፋውና ግድያው ሳያሰልስና ሳይቋረጥ የሚካሄድ በመሆኑ የክርስቲያኖች ግድያ እንደ ተራ ነገር እንዲቆጠርና የህዝብ ጆሮ እንዲለምደው ተደርጓል። ይህ የሆነበት ምክንያት ፓትርያርኩና ሲኖዶሱ ነፍሳቸውን ትተው ስጋቸውን በመውደዳቸው ምክንያት ነው። የግብጽ ፓትርያርክ የነበሩት ሽኖዳ በክርስቲያኖች ላይ ግድያ ሲካሄድና ሌሎችም በደሎች ሲደርሱባቸው መንበራቸውን ትትው በበረሃ በሚገኝ ገዳም ውስጥ ዘግተው ሲባኤ ይይዛሉ። በመሆኑም በፓትርያርኩ የዕምነት ፅናታቸውና ቆራጥነታቸው ምክንያት የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ሙባረክ ላይ ጫና በማሳደራቸው ፕሬዝዳንቱ ገዳማቸው ድረስ በመሄድ ለምነውና ተማጽነው ጥያቄያቸውን መልስ ይሰጧቸው ነበር። በዚህም መሰረት ፓትርያርክ ሽኖዳ በክርስቲያኖች ላይ የሚደርሰው ግድያ ያስቆሙ ነበር። ይህንን የሚያደርጉት አባታዊ ኃላፊነታቸው ሲለሚያስገድዳቸውና እራሳቸው በኃይማኖታቸው ጠንካራ ስለሆኑና ዘሙትን፣ ጎሰኝነትን፣ ፍቅረ ንዋያንና በአጠቃላይ ዓለማዊ ኑሮንና ምቾትን የተጠየፉ ስለነበሩ ነው።

ሆኖም የኢትዮጵያዊ ፓትርያርክና ሲኖዶስ ከእግዚአብሔር የተሰጣቸውን አደራና  ቃል ኪዳን ቅርጥፍ አድርገው በልተዋል። በሐዋርያት ስራ ምዕራፍ 20 ቁጥር 28 የሚከተለው ተደንግጓል። “በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ፥ ደቀ መዛሙርትንም ወደ ኋላቸው ይስቡ ዘንድ ጠማማ ነገርን የሚናገሩ ሰዎች በመካከላችሁ እንዲነሡ እኔ አውቃለሁ።” ፓትርያርኩና ሲኖዶሱ ለስጋዊ ፍላጎታቸው እንጅ እንዲጠብቁትና እንዲከባከቡት እራሳቸውንም መስዋዕት አድርገው እንዲሰጡለት አደራ የተሰጣቸውን ቤተክርስቲያንና ምዕመናንን ለጠላታቶቻቸውና አራጆቻቸው አሳልፈው ሰጥተዋቸዋል። በቅርቡ በቱምቢ ሚዲያ ላይ ቀሲስ አስተርአየና መምህር ፈንታሁ ዋቄ ያደረጉት ውይይት እጅግ በሳልና ጊዜውን የዋጀ ነው። ፓትርያርኩና ሲኖዶሱ እንዴት ለክርስቲያኖች መጨፍጨፍ ምክንያት እንደሆኑ በዝርዝር ማስረጃዎች እያቀረቡ ያብራሩበትን የውይይት ቪዲዮ አቅርበንላችኋል። https://www.youtube.com/live/ZReMw0l1YT4

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*