የኢራን ሚሳዔሎች ወደ ታላላቆቹ የአውሮፓ ከተሞች ሊደርሱ ይችላሉ?

ኢራን በሕንድ ውቅያኖስ ዲያጎ ጋርሲያ ደሴት ላይ ወደሚገኘው የዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) እና የአሜሪካ የጋራ ወታደራዊ ሰፈር ላይ የረዥም ርቀት ባለስቲክ ሚሳዔሎችን ማስወንጨፏ በመካከለኛው ምሥራቅ ያለውን ግጭት እየተባባሰ መምጣቱን ያሳያል። በእርግጥ ሚሳዔሎቹ ወደታቀደላቸው ዒላማ ሳይደርሱ ቀርተዋል። ነገር ግን የእስራኤል የመከላከያ ሠራዊት ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ እንዲህ ዓይነት የረዥም ርቀት ሚሳዔሎች ጥቅም ላይ ሲውሉ ይህ የመጀመሪያው እንደሆነ ተናግሯል።