ፍትሕ የተጠሙ የፆታዊ ጥቃት ሰለባዎች አቤቱታ እና የፍትሕ ሚኒስቴር ምላሽ
በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ውስጥ በሴቶች እና በሕጻናት ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች፣ አሰቃቂ ግፎች እና ግድያዎች ከፍተኛ ትኩረትን እየሳቡ በየጊዜው መነጋጋሪያ ሆነው ሲያልፉ ቆይተዋል። ከእነዚህ በሕዝቡ ውስጥ ቁጣን ከቀሰቀሱ ጥቃቶች ጋር በተያያዘ እየተነሳ ያለው ጥያቄ ወንጀሉን የፈጸሙ ሰዎች ተገቢውን ቅጣት አግኝተዋል ወይ የሚለው ነው? ነገር ግን በተለይ ከፍተኛ ትኩረትን ስበው የነበሩ የጥቃት እና የግድያ ወንጀሎች መቋጫቸው ምን እንደሆነ ሳይታወቅ ተድበስብስው መቅረታቸው ወይም ፈጻሚዎቹ ነጻ የሚሆኑበት አጋጣሚዎች ታይተዋል።