የትግራይ ኃይሎች የመቀለ አውሮፕላን ማረፊያን “መቆጣጠራቸው” ከተሰማ በኋላ ወደ ክልሉ የሚደረጉ በረራዎች ተቋረጡ

የትግራይ ኃይሎች ዛሬ ማለዳ በክልሉ ዋና ከተማ መቀለ የሚገኘውን አሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያን መቆጣጠራቸው ከተሰማ በኋላ ወደ ትግራይ በረራዎች ተቋረጡ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬ ረቡዕ ረፋድ ላይ በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ ላይ ባወጣው መግለጫ በትግራይ ክልል የሚያደርገውን በረራ "ለጊዜው መቋረጡን" አስታውቋል።