የህወሓት ኃይሎች መቀለን ለቅቀው መውጣታቸው ተዘገበ

የህወሓት ኃይሎች መዲናዋን ለቅቀው መውጣታቸውን የክልሉን ጋዜጠኛ እና ነዋሪዎችን ጠቅሶ የፈረንሳይ የዜና ወኪል (ኤኤፍፒ) ዘገበ። ከፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት ጋር በመሆን ከትግራይ ኃይሎች ጋር እየተዋጋ ያለው 'የትግራይ የሰላም ኃይሎች' በበኩሉ የክልሉን ዋነኛ አውሮፕላን ማረፊያ መቆጣጠሩን መግለጹን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።