“በኢትዮጵያ ውስጥ እጁን ያስገባ ምላሹን በእጥፍ እንደሚያገኝ ጥርጥር የለውም”

የኤርትራ ሠራዊት ድንበር ተሻግሮ ባለፉት ቀናት በተካሄዱ ውጊያዎች ውስጥ መሳተፉን በመግለጽ የኢትዮጵያ ምላሽ ከባድ እንደሚሆን ከፍተኛ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣን ተናገሩ። ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ ኒውክሌር ኃይል ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ሆነው የተሾሙት አብረሃም በላይ (ዶ/ር) የኤርትራ መንግሥት ጦር በጦርነቱ በቀጥታ መሣተፉን በመጥቀስ "እጁን እያስገባ የማያርፍ አካል ካለ ምላሹ ምን እንደሆነ በጣም ግልጽ ነው" ብለዋል።