የጳጳሳት በዝሙት መዋረድና በቤተክርስቲያኒቷ ላይ ያስከተለው መዘዝ
የጳጳሳት በዝሙት መዋረድና ያስከተለው መዘዝ
“መንበረ ሰላማ” በሚል ፖለቲከኞች የፈጠሩት የቅጥፈት ሲኖዶስ ውስጥ የሚገኙ የትግራይ ጳጳሳትን ውርደት ስሰማ አባታችን ቀሲስ አስተርአየ ቀደም ሲል ለቆሞስ አባ ሠረቀ ወ/ሳሙኤል የጻፏት ጦማር ትዝ ብላኝ እንደገና አነበብኳት፡፡ ቀሲስን ምን ተሰማዎ? ብዬ ጠየኳቸው፡፡ እሳቸውም የኔ ጽሑፍ እንዳስገረመህ እኔን ደግሞ “እግዚአብሔር ፈራጅ ነው፡፡ ይህን ያዋርዳል፡፡ ይህንንም ያከብራል፡፡ ጽዋው በእግዚአብሔር እጅ ነውና፡፡ ያልተቀላቀለ የወይን ጠጅ ሞላበት፡፡ ከዚህ ወደዚያ፡ ከዚያ ወደዚህ አገላበጠው፡፡ ነገር ግን አተላው አልፈሰሰም፡፡ የምድር ኃጢአተኞች ሁሉ ይጠጡታል፡፡ (መዝ 74፡7-9)፡፡ ብሎ የተናገረውን ቃል አስታወሰኝ አሉኝ፡፡ምን ማለት ነው ብዬ ጠየኳቸው፡፡ እግዚአብሔር ይፈርዳል፡፡ የኃጢአት ጽዋ እስኪሞላ ድረስ ግን ይታገሳል፡፡ ኃጢተኞች የኃጢአታቸውን ጽዋ እየተቀባበሉ ይጠጡታል፡፡ የሚታገሰው ኃጢአተኞች ቦታ እየተቀያየሩና የኃጢአቱን ጽዋ እየተቀባበሉ የሚጠጡት የኃጢአት አተላ ስኪጨልጡ እስከ ቀጠሮዋ ቀን ድረስ ነው፡፡ አተላውን ሲጨርሱት የሚዋረደው ይዋረዳል፡፡ የሐሰት ትርክት በተናገሩት ከንቱ ነገር ባወሩት ሁሉ ላይ የሚያብረቀረቅ ሰይፍ ባንገታቸው ላይ ይሰነዘራል፡፡ በተወለዱባት ምድር ይፈረድባቸዋል፡፡ መዓቱ በላያቸው ይፈሳል፡፡ የቁጠውም እሳት ይነድባቸዋል፡፡ ለጨካኞች ሰዎች አሳልፌ እሰጥሀለሁ፡፡ የእሳት ማገዶ ትሆናለህ፡፡ ደምህ በምድርህ ይፈሳል፡፡ ከእንግዲህ መታሰቢያ አይኖርህም(ሕዝ 21፡28-33)፡፡ ያለው እየተፈጸመ ነው፡፡ “በኃጢአተኞች የሚፈጸም በደል የሚያስከትለው መቅሰፍት በጻድቃን ላይ ይደርሳል”(መክ 8፡14) እንደተባለው ይህን ኃጢአት ጠንሥሠው ላማጡት ሰዎች ፍዳቸውን መክፈላቸው እየገረመኝ ነው፡፡ እግዚአብሔር “ቀኝና ግራቸውን ላይተው መናገር ለማይችሉ ከአንድ መቶ ሀያ ሽ በላይ ሰዎችና አያሌ እንስሣት ለሚኖሩባት ለታላቋ ከተማ ለነነዌ ማዘን አይገባኝምን? ” (ነቢዩ ዮናስ 3፡) እንዳለው በትግራይ ምድር ለሚኖሩት ንጹሐን ወገኖቻችን እናቶች አባቶች ሕጻናት ላይ የሚደርሰው መከራ ልናለቅስ ይገባል፡፡ “ኢትዮጵያን ትፏት” መቶ 20 ሚልዮን አካታ የያዘችውን ሲሉ የፈረዱት ሰዎች እንኳን በሲኖዶስ ስም በተራ ክርስቲያንነት መቆም ለማይገባቸው ሰዎች ልናዝንላቸው ይገባል፡፡ “እንኳን ደረሰባችሁ! ሳይሆን እንዴት ደረሰባችሁ? መርምሩት ራሳችሁንም ታዘቡት ልንላቸው ይገባል” አሉኝ፡፡
ዝሙት፣ ዝርፊያና ቅጥፈት የሚፈጸመው በትግራይ ክፍለ ሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በመላው ኢትዮጵያና በውጭ አገሮችም ውስጥ ነው። ኤጲስ ቆጶሳትን በብሔር ማንነትና በደም ጥራት “ንጹህ ኦሮሞ” ብቻ ጵጵስና ይሰጥ ብሎ ጸረ ክርስትና የሆነ ወራዳ ስራ ከሚሰራና ሸፍጥ ከሚፈጽም ሲኖዶስ ምንም በጎ ነገር አይጠበቅም። ማ ማንን ያወግዛል? ሁሉም በዝሙቱ፣ በዝርፊያውና በጎሰኝነቱ የተጨማለቁና የወደቁ ናቸው። ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ በተለያዩ ጊዜዎች ዝሙት የፈጸሙ ካህናትና ጳጳሳት ከቤተክርስቲያን አገልጋይነት እንዲወገዱ ሲማጸኑና ሲያሳስቡ ኖረዋል። ቀሲስ አስተርአየ ከ12 ዓመታት በፊት በቀድሞ ስማቸው “ቀሲስ ታደሰ ሲሳይ” ይባሉ የነበሩት ሰው ዝሙት ለመፈጸማቸው በማስረጃ ስለተረጋገጠባቸው ከሌሎች ሁለት ካህናት ጋር ሆነው ስልጣነ ክህነታቸውን በመግፈፍ “አቶ” እንዲባሉ አድርገዋል። አባ መላኩ (አቡነ ፋኑኤል) የተባሉት የመርገምት ጨርቅ ታደሰ ሲሳይ በሶስት ካህናት ቢወገዝም አይናቸውን በጉቦ ስለሸፈነው ውግዘቱን ምንም ሳይቆጥሩት ታደሰ ሲሳይ ቤተ ክርስቲያንን እያረከሰ እንዲቀጥልበት ሽፋን ሰጥተውታል። ከዚህም በተጨማሪ የሲኖዶስ አባል የሆኑት አቡነ ኤውስጣጢዎስ ዋሽንግተን እስቴት ውስጥ በሚገኘው የኦርቶዶክስ ዩኒቨርስቲ ውስጥ በትምህርት ላይ በነበሩ ጊዜ ከሁለት ሴቶች ጋር በፈጸሙት ዝሙት ከዩኒቨርስቲው መባረራቸውን ከፕሬዝዳንቱ ለቀሲስ አስተርአየ በደባዳቤ በተገለጸላቸው መሠረት አቡነ ኤውስጣጢዎስ የክህነት አገልግሎት መፈጸም እንደማይችሉና ጵጵስናቸው እንዲሰረዝ ለሲኖዶሱ ቢያሳውቁም አቡነ ማቲያስ ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው ይኸው እስከዛሬ አብረዋቸው ዝሙት ከፈዘሙት ከአቡነ ኤውስጣጢዎስ ጋር ቤተ ክርስቲያንን እያረከሱና እያበሻቀጡ ይገኛሉ። “ምን ለምን አብረህ እዝግም” የሚባለው መሆን አለበት እንጂ እንዴት እንደዚህ ያለ በገሀድ የተረጋገጠ ማስረጃ እያለ ወንጀለኛ ተሽሞንሙኖ ተሸፍኖለት ይኖራል? ከዚህ በታች የማቀርብላችሁ ቀሲስ የጻፏት መጣጥፍ ስትሆን መምህር ፈንታሁን ዋቄ በራሳቸው ሚዲያ እያቀረቧት ነው። ጽሁፉን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። ለቆሞስ-አባ-ሠረቀ-ከቀሲስ-አስተርአየ-ጽጌ