እሴት (ግንባታ) በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ
እሴት (ግንባታ) በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ
ቀሲስ አስተርአየ በዚህች በታላቂቷና ታላላቅ ተዓምራትና ቁም ነገር በሚሰራባት የፍልሰታ ጾም ወቅት የተባ ብዕራቸውን እንስተው ከወረቀት ጋር አገናኝተው እጅግ እንገብጋቢና ወሳኝ ጉዳይ አንስተዋል። ኦርቶዶክሳዊው ምዕመን በቤተ ክርስቲያን ላይ ዐቢይ አህመድ የከፈተባትን ጦርነት እንዳይመክትና እንዳይከላከል በተለያየ መንገድ ፓትርያርኩ፣ ሲኖዶሱና ጳጳሳቱ አድንዝዘውታል፣ አላሽቀውታል፣ አስተኝተውታል። ቀሲስ ይህንን ጉዳይ አፅንዖት ሰጥተው እንዲህ ብለዋል። “ከአማራውና ከኦርቶዶክስ ክርስትና ጋራ ንክኪ ያለው ሁሉ እየተመረጠ በሚጨፈጨፍበት ባሁኑ ወቅት የቆየ ቂምና በቀል ያላቸው የሚደርሰው መከራ ሠርግና መልስ የሆነላቸው ሰዎች ሊሸፍኑት ቢጥሩም እጅግ ጎልቶ ዓለም እየተመለከተው ስለሆነ ሊደብቁት አልቻሉም። ሕዝቡ ራሱን እንዳይከላከል ለማፍዘዝና የባሰ ይመጣልና አሁን የሚደርስባችሁን መከራ ቻሉት የሚሉት ጫጫታ ደምቆ እየተሰማ ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ በሰላሙ ጊዜ ከነበረው ባህርዩና ቦታ ሳይንቀሳቀስ በሰላም ጊዜ እንደነበረው እንደ ቋጥኝ ድንጋይ ተጎልቶ የሚታይ ማነው ብየ ስፈልግ እኔን የመሰሉ ቄሶች ብቻ መሰሉኝ፡፡ ይህች የፍልስታ ሳምንት የማያርፈውን ሕሊናችንን የምንፈትሽባት የተለየች የሱባዔ ወቅት ናትና ከዚህ ጫጫታ ውስጥ ራሴን ፈልጌ ለማግኘት ከራሴ ሕሊና ጋራ መታገል ጀመርኩ። ከወጭም ከውስጥም በሚነፍሰው ሀሳብ ከሚያንገላታው ሰው አንዱ እንደመሆኔ ከኢትዮጵያና ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ብዙ የተለያዩ የሐሳብ ማዕበላት ወደኔ እየጎረፉ ሕሊናየን አጥለቀለቁት፡፡” ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። እሴት (ግንባታ)