ከከብት ጥበቃ ወደ እስራኤል የገቡ ጥቂት አረመኔዎች ያሰሙትን የዝንጀሮ ጩኸት በኢየሩሳሌም

ከከብት ጥበቃ ወደ እስራኤል የገቡ ጥቂት አረመኔዎች ያሰሙትን የዝንጀሮ ጩኸት በኢየሩሳሌም

በዚህ ሳምንት እንከተለዋለን የሚሉትን የኦሪቱን እምነትና የእስራኤልን ሕገ መንግሥት ያልተረዱ ከከብት ጥበቃ ወደ እስራኤል የገቡት ጥቂት አረመኔዎች ያሰሙትን የዝንጀሮ የሚመስል ጩኸት በኢየሩሳሌም አደባባይ ሰማን፡፡ ንግግራቸው ያበሳጫት አንዲት የጰንጤቆስጤዋ ሴት ፓስተር በቁጣ የሰጠችውንም መልስ ሰማን፡፡ ከስምንት ወራት በፊት (Ethiopia and the Judoe _Chrstian tradition Antiquty to Modernity) በሚል ርእስ ዶ/ር ጌታቸው መታፈሪያ ባሳተሙት መጽሐፍ ላይ ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ ዲሰምበር 20 ቀን 2025 ባቀረቡትም ግምገማ ሁሉም የተናገሩትን እንደገና እንድንቃኘው የሚያደርግ መልካም አጋጣሚ ነው፡፡ ዶ/ጌታቸው ቤተ እስራኤልንና ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን አሰናስለው ያቀረቧቸውን ቀሲስ አስተርአየ ከህዝብና ከቤተክርስቲያን አባቶች የሰሟቸውንና በልብሳችንና በምግባችን የሚታዩትን የጋራ ባህሎችን አብራርተው አቅርበዋቸው ነበር፡፡ከይሁዲው ጥንትነት ራሳቸውን ካገለሉ ከምዕራቡ ዘመናዊ ክርስትና ይልቅ ከቤተ መቅደሱ ጀምሮ በህዝበ ክርስቲያኑ ላይ በሚታዩት ኦሪታውያን እሴቶች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስትና Judoe-Christianity ተብላ የተሰየመች ናት። በአብዛኛው ቤተ እስራኤል ስም ወደ ወደ ኢየሩሳሌም የገቡት በይሁዲው እምነትና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስትና መካከል ያለውን ልዩነትና አንድነት የተረዱ አይደሉም፡፡ የኢትዮጵያውነት ተክለ ሰውነታችውንና ደም ግባታቸውን ያልተገነዘቡ ናቸው፡፡

በኢየሩሳሌውም አደባባይ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚያካሂዱት ሰልፍ ሰላማዊ ሳይሆን አረማዊ ሰልፍ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ አብያተ ክርስቲያናትን ከሚቃጥሉ ክርስቲያኖችን በጦር ከሚወጉ በሰይፍ ከሚያርዱ አረመኔወች ጋራበባህልና ባረመኔ እምነት ጥብቅ ግኙነት ያላቸው አረመኔዎች ናቸው፡፡ የአስራኤል አምላክ ከኢትዮጵያ ምድር እንድትወጡ ባያደርጋችሁና በዚህ ወቅት እዚያው ኢትዮጵያ ብትሆኑ ኖሮ፦አሁን ባሳያችሁት አረመኔ ጭካኔያችሁ በኢትዮጵያ ምድር አንድ ሰው አይተርፋችሁም ነበር፡፡ ከኛ ተለይታችሁ እስራኤል የገባችሁት ከሌሎች አገሮች ወደ እስራኤል ከገቡት ይሁዲወች ይልቅ ከኦሪቱ ጋራ ባላችሁ ቅርብነት የአብርሃምን የይስሀቅንና የያዕቆብን እምነት በተግባራቹሁ በንግግራችሁ ትመሰክራላችሁ የሚል ግምት ተሰጥቷችሁ ነበር፡፡ በኦሪቱ የሚያምነው የእስራኤል ሕዝብ ቀን ቢጥለውና በጠላቱ ተሽንፎ ቢወረር በዚህ አረመኔ ባህርያችሁ ሰይፋችሁን እንደምታዞሩበት በግልጽ አሳያችሁ፡፡

የውጭ ወራሪዎች እኛን ከፋፍለው ኃይላችን አዳክመው ለመግዛት ሲሉ የተናገሩትን ሴራ ኢትዮጵያውያን አባቶቻችን የተናገሩት አስመስላችሁ የምትናገሩት በዓለም ተበትኖ ባለው ቤተ እስራኤልና በኦርቶዶክስ ተዋህዶ አካል ሁሉ ፊት ሕገ ወጦች መሆናችሁን እንዳጋለጣችሁ ልትገነዘቡ ይገባችኋል፡፡ እናንት አረመኔዎች ለምትናገሩት አረማዊ የቁጣ ቃል ክርስቶስ ትንቢት አናግሮ ራሱ ፈቅዶ ራቁትን የተሰቀለው ክርስቶስ ላደረሱበት ዘለፋ “ሳያዉቁ ነውና ይቅር በላቸው” እንዳለው በኢየሩሳሌም ገዳማት የሚኖሩት መንፈሳውያን አባቶች ክርስቶስ ያለውን ከመድግም በቀር ጴንጤዋ ፓስተር የተናገረችውን አይናገሩትም፡፡

እምነቱና እውቀቱ ያለው ሁሉ “ዓይን ሁሉ ያየዋል፡፡ የወጉት ሁሉ ያዩታል (ራእይ 1፡7) የተባለው የሚፈጸምበትን ቀን በመናፈቅ ያሁኑን አራማዊ ስሕተታችሁን ታዝቦ ያልፋችኋል፡፡ የምትደግሙት ከሆነ ግን ኦሪቱ በሚፈቅደው የእስራኤል ሕግ በደነገገው ቅጣት የእስራኤል መንግሥት በናነተ አረመኔዎች ላይ እርምጃ እንዲወስድ መላ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሕዝብና ይህን የመሰለውን አረመኔ ባህርይ የሚጸየፈውን ሰው ሁሉ በማስተባበር በናንተ ላይ የእስራኤል ሕገ መንግሥት የሚደነግገውን እርምጃ እንዲወስድ ሰላማዊ ሰልፍ እንድናደርግ እንገደዳለን፡፡ ራሳችሁን እንድታውቁ፡ ከገባችሁበት ጉድጓድ እንድትወጡና ደግማችሁ እንዳትሳሳቱ ይረዳችኋልና ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ ታህሳስ 20 /2025 ያቀረቡትን ጦማር ከዚህ በታች ተመልከቱት አንቡት ተማሩት፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ህዝበ ክርስቲያን ከሚያርዱት አረመኔዎች ጋራ ከተሳሰራችሁበት አረማዊ ሰንሰለት አምላከ እስራኤል እንዲያላቅቃችሁ እንጸልይላችኋለን፡፡ የቀሲስ አስተርአየን የመጽህፍ ግምገማ አሁን እየተንጋገርንበት ካለው ጉዳይ ጋር በቀጥታ ተያያዥነት ስላለው በድጋሚ አቅርበንላችኋል። ጽሁፉን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። ጥንትነታዊነት በዘመናዊነት (Antiquity to Modernity) የመጽሐፍ ግምገማ በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ