ቻይና የዓለም በሽታ (ከአደፍርስ ተሰማ)
በሰባቱ የአለም ክፍሎች ስር በመስደድ ዓለምን የሚመዘብሩት ቻይናዊያኑ አሁን ላለውና መልኩን ለውጦ ሊመጣ ላለው የአለም የፓለቲካ መዋቅር የተስቦ በሽታ ናቸው። አንድ ነጥብ አምስት ቢሊዮን ህዝብ የታጎረባት ቻይና ዛሬ በአንድ እጅ ማጭድና መዶሻ በሌላው እጃችው የአሜሪካ ዶላር በመያዝ አለም አቀፍ ምዝበራቸውን ቀጥለውታል። አለቅጥ የተዋቀረው የስለላ መዋቅራቸው ሰውን መተናፈሻ አሳጥቶታል። ቻይና ስብዕና የጎደላት ሰውና እንስሳት ጭምር የሚሰቃዩባት ሃገር ናት። ለሌላው ማዘን የሚባለ ነገር በቋንቋቸው የለም። ሰውን ከእንስሳ ለይተው አያዩም። ታዲያ እንደዚህ ያሉትን አረመኔዎች ነው ወያኔ ወደ ሃገራችን አስገብቶ አለቃ አርጎ በህዝባችን ላይ ያቆመብን። በኢትዮጵያ አሳሪና ገራፊ ናቸው። የሚስሩት መንገድ፤ የሚያቆሙት ሃውልት፤ ባጠቃላይ እጃቸው የነካው ሁሉ ውሎ ሳያድር ይፈራርሳል። ከቻይና ተመርቶ ወደ ሶስተኛው ዓለም የሚላኩ ቁሳቁሶች ሁሉ ያለጥራት የተሰሩ በመሆናቸው ለምዕራቡ ከሚላኩት የሽቀጥ አይነቶች በጥራት በጣም ዝቅ ያሉ ስለሚሆኑ አገልግሎታቸው ጊዜአዊ ነው። ባጭሩ ሶስተኛው ዓለም የህንድና የቻይና መጫወቻ ሆኖአል።
ለምሳሌ ያህል በፓናማ የሆነውን ልጥቀስ አንድ (glycerin) አምራች የሆነ የቻይና ኩባኒያ ግልስሪን ነው በማለት diethylene glycol ፓናማ ውስጥ ለሚገኝ ኩባንያ ይሸጣል። ይህ ፓናማዊ ኩባኒያም ግልስርን ያገኘ መስሎት ከጉንፋን መድሃኒት ጋር በመደባለቅ መድሃኒቱን ለሃገሩ መንግስት ይሸጣል። መንግስትም መድሃኒቱን ለሆስፒታል ያከፋፍላል። ይህኑ መድሃኒት የወሰዱ ሁሉ ታመው ከዚህ አለም በሞት ይለያሉ። ምርመራውም glycerin ሳይሆን diethylene glycol ከጉንፋን መድሃኒቱ ጋር እንደተደባለቀ ይደረስበታል። ሌላም ብዙ ጉድ አለ…የጥርስ መፋቂያ፤ የጥርስ ሳሙና፤ የተለያዪ የሰውና የከብት መድሃኒቶች ተበከለው ተገኘተዋል። በሃገራችን ከቻይና የተሰራ መድሃኒት ውጠውና ተወግተው ህይወታቸው ያለፈውን መቃብር ይቁጠረው። ነገራችን ሁሉ የሚያቆመው ታሞ ነበር ሞት ብቻ እየተባለ ነውና። የሚያሳዝነው ነገር ግን የህንድ ኩባኒያዎችም ከቻይና አለመሻላቸው ነው። በኢትዮጵያ እልፍ ሽቀጥ የሚገባው ከእነዚህ ሁለት ሃገሮች ነው። ዛሬ ወያኔ አቶ ስዪም መስፍንን በቻይና መዲና ያስቀመጠው ከቻይና ጋር ያለውን መተሳስር ጥብቀት ያመለክታል። ቻይናም ሆነ ህንድ ለኢትዮጵያ አይጠቅሙም። ሁለቱ ሃገሮች ዘራፊዎች ናቸው።
ፓለቲከኞች ልበ-ቢሶች ናቸው። የቻይና ጉርብትና ለማንም አይጠቅምም። እንደ ሃገራችን የሽንኮራ አገዳ ጣዕሙ እስኪያልቅ ብቻ መጦ መትፋት ነው የእነዚህ ሃገሮች ፍቅር ለአፍሪቃ ህልውና። ዛሬ በሃገራችን በእርሻ ስም ለዘመናት የቆየ ደን የሚመነጥሩት ለጤፍ ማሳ አይደለም። የእራሳቸውን ኪስ ለመሙላት ለማመቻቸት እንጂ። የሰው መራብና መራቆት ደንታቸው አይደለም። በራሳቸው ሃገር ረሃብና የሰብዓዊ መብቶች ጭቆና የነበረና አሁንም ያለ ነው።
አሁን አደጉ ከነፉ የሚባልላቸው ቻይና እና ህንድ በቱኒዚያ እንደተነሳው ያለ የህዝብ አመጽ ተቀጣጥሎ እንደሚጠብሳቸው ከአሁኑ የሚያመላክቱ መሰረታዊ ነገሮች አሉ። ወያኔም እነዚህን ሰመ ጠበብቶች እያመጣ በህዝባችን ላይ አለቃ አርጎ መሾሙን ቢያቆም ይሻለዋል። እንዴት ሰው በሃገሩ በቻይና ይገረፋል? ይህ አሳፋሪ ተግባር ነው። ባጭሩ ቻይና የዓለም በሽታ ናት። ዛሬ በሱዳን፤ በአልጀርስና በኢትዮጵያ የሚያደርጉት የበጎ አድራጎት ስራ አይደለም ምዝበራ እንጂ። ለሚመዘብሩት ህዝብም ሆነ ለቆሙበት ምድር ምንም ጥንቃቄ የማያረጉ አሳሞች ናችው። አንባቢ በዚህች አጭር ጹሁፍ የምለው ባይዋጠው ለማወራረጃ ያህል ዋቤ የማረገው ጊዜን ነው። ቀን ሁሉን ያሳያልና ሰንበተን እንይ።