መለስ ዜናዊ ከሥልጣን ይወገድ!

በሰሜን አፍሪካ፣ በመካከለኛው ምሥራቅና በኢትዮጵያ ሰፍኖ የቆዬውን አምባገነናዊ ሥርዓት ልዩነትና ተመሳሳይነት ከግምት ውስጥ በማስገባት፤

ብዙ ደም መፋሰስ ሳያስከትል በቱኒሲያ የተካሄደውን የመንግሥት ለውጥ፣ በግብፅ፣ ዮርዳኖስና ሱዳን እየተካሄደ ያለውን ህዝባዊ አመፅ አርአያነት በመከተል፤

በሀገራችን ዴሞክራሲያዊ ለውጥ እንዲመጣ የምንታገል በመላው ዓለም የምንገኝ ኢትዮጵያውያን ጥር 30 ቀን 2011 በተካሄደው ዓለም አቀፍ ስብሰባ የሚከተለውን ውሳኔ አሳልፈናል፡፡

1. በቱኒሲያ፣ ግብፅ፣ የመንና ሱዳን የተቀጣጠለውን ዴሞክራሲያዊ ትግል ከልብ እንደግፋለን።
2. ጨካኙና አረመኔው መለስ ዜናዊ በአስቸኳይ ከሥልጣን ተወግዶ ኢኮኖሚውን በማረጋጋት ነፃ ምርጫ ለማካሄድ ሁኔታዎችን የሚያመቻች ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ የሽግግር መንግሥት እንዲቋቋም እናሳስባለን።
3. ሁሉም የኢትዮጵያ የሲቪልና ፖለቲካ ድርጅቶች አምባገነናዊውን የመለስ ዜናዊ ሥርዓት ለመገርሰስ ይቻል ዘንድ ህብረት እንዲፈጥሩ እንጠይቃለን።
4. በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ የሚካሄደውን ዴሞክራሲያዊ ለውጥ እንድደግፉ ጥሪ እናቀርባለን።
5. የጦር ሠራዊትና ፖሊስ አባላት ከቱኒሲያና ግብፅ የጦር ሃይሎች ልምድ በመቅሰም የአምባገነኑን የመለሰ ዜናዊ ትዕዛዝ አሻፈረኝ በማለት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ጉዳት ከማድረስ እንዲቆጠብ እንጠያቃለን።
6. የኢትዮጵያ ህዝብ በየሠፈሩ የሠላምና የመረጋጋት ኮሚቴ በማዋቀር ህግና ሥርዓት እንዲያስከብር እያሳሰብን በምንም መልኩ የመለስ ዜናዊ ከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ ሰለባ እንዳይሆን እናስገነዝባለን።
7. በየካቲት 7 ቀን 2011 (እአአ) በዋሽንግተን ዲሲ የተጠራውን ሠላማዊ ሠልፍ በሙሉ ልብ እንደግፋለን። በመላው ዓለም የሚገኙ ዲሞክራሲያዊ ሃይሎች መለስ ዜናዊንና ግብረአበሮቹን በመቃወም ተመሳሳይ ሰልፍ እንዲያደርጉ እናሳስባለን።

አምባገነኑ መለስ ዜናዊ ከሥልጣን ይወገድ!

ነፃነትና ዲሞክራሲ ለኢትዮጵያ ህዝብ!