‹‹ለዲያስፖራው የተመደበው …››
ከጆኒ፣ ዋሽንግቶን ዲሲ
በቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ዘመነ መንግሥትት በደሴ ከተማ በአስር እልቅና የፖሊስ አባል ሆኖ ሲሰራ ነበር፡፡ በወቅቱ ከባለስላጣናት ጋር በአገልጋይነትና በወሬ አቀባይነትም ያገለግል ስለነበር ከህዝቡ በጉቦኛነቱ የሚቀርበውን አቤቱታ ሁሉ የመቋቋም ሃይል ነበረውና ማንም ሊነካውና ሊጋፋው ወይም ከጉቦ ሊያላቅቀው አልፈረም፡፡ በወቅቱ የክፍለ ሃገሩ የትራፊክ ጽ/ቤት ሃላፊ የነበሩት በተደጋጋሚ ስለቀረበበት አቤቱታ ምላሽ ሲሰጡ ‹‹ምን አድርግ ነው የምትሉኝ? እውነት መሰላችሁ እንዴ ሃላፊ መባሌ እውነተኛው ሹም እኮ እሱ ነው›› ብለው ለአባሎቻቸው ምላሽ ሰጥተው የሰውዬው ነገር በተነሳ ቁጥር ይሄም አባባል አብሮ ይነሳል፡፡
ታደለ ይመር ይባላል
ይቺን ያነበበና በወቅቱ በደሴ ክፍለ ሃገር የነበረ ማንም ሰው ይህን ሰው ያውቀዋል፡፡
ጃንሆይ ከስላጣን ወርደው ደርግ ቦታውን ሲረከብም የፖሊስ አባልና ትርፊክ ክፍል ስለነበርም ከመቅጽበት ተወርውሮ በወቅቱ ከነበሩት የለውጥ ሃዋሪያዎች ጋር እጅና ጓንቲ በመሆን ሚስጥር ወጥቶ ቅሌት ሳይከተል ወደ ናዝሬት ተዛውሮ በትራፊክነት ማገልገሉን ቀጠለ፡፡ለናዝሬት አዲስ በመሆኑን ከደሴ ወደ ናዝሬትም ሲዛወር በታታሪነት የተዛወረና በናዝሬት ያለውን የተሽከርካሪዎችና የአሽከርካሪዎች ስርአት አልበኝነት ለማስተካከል የተመደበ መሆኑን አውርቶ በማስወራት አሁንም እንደገና በናዝሬት ካሉት የወያኔ አባላት ጋር ቡና ጠጪ፤ ወሬ አመላላሽ፤ ሰዎችን በተለያየ ስም ጠቋሚ በመሆንና አዲስ ገብ በሆነበት ከተማ ናዝሬት ከቆዩት ነዋሪዎች የበለጠ ሆኖ ሽር ጉድ አለ፡፡
ታደለ ይመር ይባላል
በናዝሬት የነበሩትን የወያኔ አባላት ቁርስ ምሳ እራት እየጋበዘና የማያውቁትን ውስኪና ጥሬ ስጋ ጋር አገናኝቶ ሱሰኛ በማድረግ ተፈላጊ ሆነ፡፡ ገንዘብ አይቸግረው እያንዳንዱን አሽከርካሪ በተለይም በክፍለ ሃገር አውቶቡስ ጣቢያና በከተማው መውጫና መግቢያ ላይ እየቆመ የክስ ሰነድ እያወጣ ሰነዱንና ጉቦውን አብሮ ወደ ኪሱ እየከተተ በዚያው ደሞ ወያኔዎችን እየጋበዘ የሚነካው ጠፋ፡፡ አሁንም እንደደሴው ተፈሪና እጅ አስነሺ ደጅ ተጠኚ አማላጅ ሆነ፡፡
በናዝሬትም በዚያን ወቅ የነበሩ ይሄን ሲያነቡ ያውቁታል፡፡ማንነቱን በሚገባ ይለዩታል፡
በናዝሬት ለጥቂት ወራት ከሰራና አገልግሎቱን ለወያኔ ክህደቱን በህዝብ ላይ ካከናወነ በኋላ እራሴን ለማሻሻልና የተሸለ አገልግሎት ለሃገሬም ለወያኔም ለመስጠት እንድችል ወደ አዲስ አበባ ተዛውሬ የህግ ትምህርት እንድታተል ይፈቀድልኝ ብሎ ባመለኬው መሰረት ክፍሉ ሲጠየቅም የሱ ወደ አዲስ አበባ መሄድ ለክፍሉም ለአሽከርካሪዎችም እፎይታ ስለሚሆን ያለተቃውሞ የጠየቀው ተፈቅዶለት የህግ ትምህርት በዲፕሎማ ደረጃ መከታተል ጀመረ፡፡ እዛም እንዳለ እቅድ አለውና ማመለክቻ አስገብቶ የደም ብዛትና ስኳርም ስላለብኝ ከፖሊስ አባልነት እንድገለል ይፈቀድልኝ ብሎ አመልክቶ አሁንም ተፈቀደለት፡ ወዲያውም የሲቪል አባል ሆኖ ከሰዎች በመጠጋት የነገረፈጂነት ስራ ለመስራት በመጠየቅ ጥንሽ ትንሽ ስራ እየሰራ ሳለ አንዲት እመቤት ከባለቤታቸው ጋር በገጠማቸው አለመግባባት ፍርድ ቤት ሲቆሙ ይሀተው ግለሰብ የጥብቅና ስራውን እሱ ያዘ፡፡ መልከ ቀና ነውና በተለይ ወሬ ስለሚያውቅና እራሱን ሰማየ ሰማያት ጥግ አውጥቶ ስለ ራሱ ማውራት ስለሚያውቅ ከኒህ ሴት ወይዘሮ ጋር ቀስ በቀስ ከነገረፈጂነት ወደ ቤተኛነት፤ቀስ ብሎም ወደ አልጋ ደባልነት ተረማምዶ ስራውን ቀጠለ፡፡ አሁን ሁለት ስራ አለው፡፡ አንዱ በፍርድ ቤት የቆመበትን ጉዳይ መከታተል፤ በሌላ በኩል ደሞ ከኒህ ሴት ጋር ያለውን ግንኙነት አጠናክሮ ሙሉ ውክልና ለማግኘትና በንብረት ሃብታቸው ለማዘዝ ነበር፡፡ ሁለቱንም አሳካ፡፡ የፍርድ ቤቱ ጉዳይ ለሴትዮዋ ባመዘነ መልኩ ሲፈረድ፤ እሱም ሙሉ በሙሉ ከነገረፈጂነትና ውክልናም አልፎ ወደትዳር ጓደኛነት ተረማምዶ ህጋዊ የጋብቻ የሰማንያ ጋበቻ ተፈራረመ›› አሁን ሁሉ በጁ ሁሉ በደጁ ሆነ፡፡ በፍርድ ቤቱ ውሳኔ መሰረት ለሴትየዮዋ የደረሰውን አነስተኛ ሆቴል ያዝበት ይቀጥር ያሰናብት ገቢውን ይቆጣጠርና ንብረትነቱን ያረጋግጥ ጀመር፡፡ይህችን አናሳ ሆቴል ሰበብ አድርጎም በአዲስ አበባ ነጋዴዎች ምክር ቤት በአባልነት ተመዘገበ፡፡ በገባ ሰሞን ምክር ቤቱ ዓመታዊ ስብሰባውን ሲያደርግ እሱም በአባልነቱ እንደመንኛውም አባል ተጠርቶ ተሳተፈ፡፡
በዚህ ስብሰባ ላይ እነማን ወደ አመራር እንደሚመረጡ አስቀድሞ ገምቶና የንግዱን ህብረተሰብ ስሜትም በማስላት የይመረጣሉ ካላቸው ጋር ተጠግቶ ለምርጫው ሰዉን በማግባባት እንዲመረጡ ማድረጉን ያዘና ወዳጅንትንም አብሮ ገዛ፡፡በምርጫው ማግስት ወዲያው ከተመራጮቹ ጋር ቤተኛ ሆኖ ቡና አጣጭና አማካሪ፤ የህግ ባለሙያነቱንም መከታ በማድረግ የንግዱ ህብረተሰብ የግልግል ኮሚቴ አባል ሆኖ በተመራጮቹ ተመደበ፡፡ የግልግል ኮሚቴ አባላትም የመጀመርያ ስብሰባቸውን ሲያደርጉና ሰብሳቢና ጸሃፊ ሲመርጡ በወሬ አዋቂነቱና በምርጫም ወቅት ባሳየው ሁኔታ አንዳንዶቹን አባላትም እኔ ነኝ ስማችሁን የሰጠሁላችሁ እያለ በጸሃፊነት ለመመረጥ በቃ፡፡ይሄ ደሞ ከምክር ቤቱ አመራሮች ጋር የበለጠ እያገናኘው አቀራረበው፡፡
ታደለ ይመር ይባላል
አሁንም በዚህ ወቅት በአካባቢው የነበሩ ይህን ሲያነቡ ማንነቱን ይለዩታል፡፡
ብዙም ሳይቆይ ያቺን ሆቴል ሰበብ በማድረግ ‹‹የአነስተኛ ሆቴሎች ማሕበር›› በሚል ለማቋቋም በጠየቀውና በተለይም በመርካቲ አካባቢ ያሉት አነስተኛ ሆቴሎች አባላት እንዲሆኑን እንዲመዘገቡ መሳርያ ይሆናል በሚል ሃሳቡን አቅርቦ የመጀመርያውን ስብሰባ ጠርቶ ብዙም ሳይቆይ ማህበሩን አዋቅሮ የአመራሮች ምርጫ አካሂዶ እራሱ በሊቀመንበርነት አስመረጠ››፡፡ ይሄ ደግሞ ውሎ አደረና የአነስተኛ ሆቴሎች የሚለውን ደፋ ቀና ብሎ፤ ወጥቶ ወርዶ፤ አባላቱን አሰባስቦና አቤት በሉ ብሎ፤ የሆቴል ሰራተኛች ማህበር ብሎ አሰየመው፤ ወዲያው ቀድሞ የነበረውን የሆቴል ቤቶች ማህበርን ገፍቶ ወደ ዳር ካስወጣ በኋላ ለመጠቅለልና አመራሩን በእጁ ለማስገባት ዳረጎት ማቅረቢያ መንገድ ማመቻቸት ያዘ፡፡
ወዲያው ነው በንግድ ምክር ቤት ባለው ተቀባይነትና ድጋፍ በየቦታው ብቅ ጥልቅ እያለ በመታየቱ ለአማራው የዚያን ጊዜው ብአዴን አባል ሆነ፤ አልፎም በአዲስ አበባ የመኖርያ አካባቢው ተጠሪም ሆነ፡፡ ይሄ ደም የበለጠ ጥቅም አስገኘለት፡፡
ከኤርትራ ጋር በተደረገው ጦርነት ወቅትም በነጋዴው ህብረተሰብ አመራርና በጥቂት የንግዱ ሕብረተሰብ አባላት መሃል ተፈጥሮ በነበረው አለመግባባት የተነሳ በግል ተነሳሽነት የንግዱ ሕብረተሰብ እርዳታ አሰባሳቢ ኮሚቴ ሲፈጠር አሱም እንደ አንደች የማሕበር መሪ በኮሚቴው ውስጥ ተካተተና ማን ይቻለው፡፡
ቀን ቀን በግል ተነሳሽነት ከተቋቋመው ኮሚቴ ጋር አለ ማታታ ደሞ ቀን የሆነውን ሁሉ ወስዶ ለንግድ ምክር ቤት አባላት በማቅረብ በመሃላቸው መግባባት እንዳይኖርና ልዩነቱ እንዲቀጥል በማድረግ የሁለቱም ወገን ተጠቃሚ ሆነ፡፡
በግል የተነሳሳው የእርዳታ ኮሚቴ የተለያያ የእርዳታ ማሰባሰቢያ ተግባራት እየቀደ ከንግዱ ሕብረተሰብ እርዳታ ያሰባስብ ስለነበር በታቀደው የሎተሪ ሽያጭ ላይ ለአሸናፊ ሊሰጥ በእሱ በኩል የተገኘውን ባሕላዊ ወንበርና ጠረጴዛ ዘስከመጨረሻው ገቢ ሳያደርግ ይልቅስ ወደቤቱ ወስዶት በዚያው ቀርቷል፡፡ለምን እንዴት እሱ እጅ እንደገባ ግን የታወቀ ጉዳይ የለም፡፡
ታደለ ይመር ይባላል
በዚያን ጊዜ በኮሚቴው ውስጥና በንግድ ምክር ቤት አካባቢ የነበሩ መቼም ያውቁታል፡፡
በኋላም ብአዴን በአዲስ አበባ አጠቃላይ ስብሰባ ሲያደርግ ይሄ ሰው በአባልነቱና የሆቴል ቤቶች ማህበርም ሰብሳቢ በመሆኑ ለተሰብሳቢዎች ምግብና መጥ እንዲያቀርብ ሃላፊነት ተሰጥቶት ሳለ፤ጥቅሙን ለራሱ ለማድረግ በማሰብ ደረጃውን ያልጠበቀና ዋጋውም የናረ ሳንድዊች ሊባል የማይገባው ምሳ በማቅረቡና ለአንድ አምቦ ውሃም 5 ብር ሰነድ በማቅረቡ በወቅቱ ሰብሳቢ በህላዊ ዮሴፍ በስብሰባው መሃል ላይ በአደባባየይ አዳራሽ መሃል አቁሞ ምን ያህል የውርደትና ራስወዳድነት ተግባር እንደፈጸመ፤ ፓርቲው ሲያምነው ለግል ጥቀቅሙ ሲል ክህደት የፈጸመና አባላትን ባቀረበው ጽዳት በጎደለው ምግብ አባላትን ለበሽታ የደረገ›› ብሎ ሲያወርድበት ግለሰቡ ባለበት የደም ብዛት እራሱን ስቶ በሸክም ከስብሰባው ወጥቶ ተወሰደ፡፡ ከዚያ በኋላ ወደ ድርጅቱ አልተመለሰም ነበር፡፡
ከምርጫ 97 በኋላ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች በተለያየ ሰበብ አበረዋቸው የነበሩትን አባላት ለመጠናከር ባሉት እቅዳቸው ከያሉበት ሲሰበስቡና መልሰው ሲያስገቡዋቸው ታደለ ይመርም ተመልሶ ገባ፡፡
አሁንስ
አሁንማ ሁላችንም እናውቀዋለን
ታደለ ይመር ይባላል
አሁን ደሞ እንደሰማሁት የኢየሩሳሌም ድርጅት የጠቅላላ ጉባኤ ሰብሳቢ ሆኖ አለ፡፡ እስካሁን በገንዘብ ላይ እጁ ይግባ አይግባ የታወቀ ባይኖርም ለመንግስት ግን ታማኝ አገልጋይነቱንና ደጋፊነቱን እያረጋገጠ ነው፡፡ ባለፈው ገና ምርጫው ሳያልቅ ምርጫው ምን ያህል ነጻና ዴሞክራሲያዊ ሕዝብም የልቡን የተናገረበት እንደሆነ በመንግስት መገናኛ መግለጫ ለመስጠት አንድም ሰው አልቀደመውም፡፡ ያን መሰረት ባደረገ ደግሞ አሁን ዲያስፖራውን ለማነጋገርና ከመንግሥት ጋር እንዲቆም፤ተቃውሞውን እንዲተው በተቋቋመው ኮሚቴ ውስጥ ተመሳሳዩን ይስሃቅ አብዱላሂን ሊቀመንበር፤እራሱን ጸሃፊ አድርጎ አሰይሞ ሽር ጉድ እያለ ነው፡
አሁን ሌላው ስራው የቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ አከፋፋይ ሆኖ እየሰራ የሼር ባለቤትም ነኝ እያለ ነው ምን ያህል እውነት መሆኑን ፋብሪካውና እራሱ ናቸው የሚያውቁት፡፡
ይህ ነው ክፍል አንድ የዚህ ሰው ማንነትና፤ዲያስፖራው የተመደበበትን ቀላማጅ ሊያውቀውና ሊጠነቀቅ ይገባል፡፡ ‹‹ፃአ መንፈስ ርኩስ ነው ማለት ያለብን››
መቼም አብረን ነበርንና ታስታውሰኛለህ
ይቀጥላል፡፡