ትምህርት-ነክ ቃሎች
ከዲባቶ መስፍን አረጋ
ይህ ጦማር (article) በትምህርት-ነክ ቃሎች ላይ የሚያተኩር ነው። ጦማር ማለት ጥናታዊ ፅሁፍ እንደማለት ሲሆን ቃሉ የተገኘውም ከግእዝ ነው። በዚህ ጦማር ውስጥ ስለተካተቱትና ስለሌሎች በሺህ የሚቆጠሩ አያሌ አዳዲስ ሰገላዊ ቃላቶች (scientific words) አመሰራረት በሰፊው ለመረዳት “ሰገላዊ አማርኛ” (አማሮምኛ) በሚል ርዕስ በቅርቡ ያሳተምኩትን መጽሃፍ መመልከት ያስፈልጋል።
ሰገል ማለት በግእዝ ጥበብ ማለት ነው “ሰብአ ሰገል” እንዲሉ “የጥበብ ሰዎች” ለማለት ሲፈልጉ። ይህም ቃል ሳይንስ የሚለውን የባእድ ቃል የተካልናል። ከዚህም ሰገለኛ (scientist)፣ ሰገላዊ (scientific) የሚሉትን ቃሎች እናገኛለን። ስለዚህም “ሰገላዊ አማርኛ” ማለት “ሳይንሳዊ አማርኛ” (Scientific Amharic) ማለት ይሆናል። “አሞሮምኛ” ማለት ደግሞ አማርኛንን ኦሮምኛን በማጣመር የፈጠርኩት ቃል ነው — ሰገላዊ አማርኛን በመጻፍ ቋንቋችን ሰገላዊ፣ ማለትም ሳይንሳዊ፣ ለማድረግ የኦሮምኛን ቋንቋ በሰፊው ተጠቅሜበታለሁ — ለኦሮምኛ ቋንቋ ምስጋና ይግባውና። ለመቀጠል እዚህ ላይ ይጫኑ…