ከተለየኸን … ደህና ሁን!

ኩችዬ – ሚያዝያ 12 ቀን 2001 ዓ.ም. (April 20, 2009) [email protected]

ለጥላሁን ገሠሠ ሙዚቃ ሙት መሆኔን ሀገር ያውቃል። የእርሱ ሙዚቃ ዳግም ላይሰማ ይታገዳል ያሉኝ ይመስል ከሰሞኑ መልሼ መልሼ የማዳምጠው እሱኑ ብቻ ነበር።