ብራቮ! አበራ ለማ (የትዝታ ቅምሻ)

ስሜነህ ታምራት ከስዊድን

ከአዲስ አበባ ተነስተን ወደ ወሊሶ በሎንቺና ስጓዝ ነበር፤ ለመጀመሪያ ጊዜ አበራ ለማን ያገኘሁት። እናም “ኩል ወይስ ጥላሸት” የሚል መጽሐፍ በገፀበረከት አበረከተልኝ። “የማን መጽሐፍ ነው?” አልኩት፤ “እኔ የሞካከርኳት መጽሐፌ ናት” አለኝ – ለስለስ ባለ አንደበት። አመስግኜ ተቀበልኩት።