ትውስታ ለሙዚቃው ቀማሪ (ጌታቸው አበራ)
ጌታቸው አበራ (መጋቢት ፮ ቀን ፪ ሺህ ፪ ዓ.ም./ማርች 2010)
የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ በእሁድ ዕለት ዜናው፣ የእውቁን የሙዚቃ ደራሲና ቀማሪ፣ የኮ/ል ሣህሌ ደጋጎን ዜና እረፍት ሲያሰማን፣ አዘንኩኝ። በትዝታ ወደኋላ በመመለስም የልጅነት ጊዜዬን ማሰላሰል ያዝኩኝ። የሙዚቃ በረከት እየመገቡ ላሳደጉን ለኒያ ታላቅ የሙዚቃ ሰው ያለኝን ከበሬታ ለመግለጽም ይህቺን አጭር ማስታወሻ ለማስተላለፍ ወደድኩ።