ጥላሁን በ”ኦፔራ ሐውስ”
ጥላሁን ”የኦፔራ የወርቅ ማንኪያ ነክሶ የተወለደ ነው” ሲሉ ወዳጆቼ ይመሰክሩለታል። በተፈጥሮ ተስረቅራቂ ድምፅ ማግኘቱ፣ መልከ መልካምነቱ፣ በሚያውቁት ሁሉ ዘንድ ተወዳጅ መሆኑ ዕድለኛነቱን ይመሰክራሉ። በተለይም ጎላ ጎላ ያሉ ዓይኖቹን ወዲያና ወዲህ ሲያንከባልላቸው ግርማ ሞገሱን ከፍ ያደርጉለት ነበር። ”ቁልጬ” የሚል የቅጽል ስም አስገኝቶለታል። ተወዳጁ ልዩ ተሰጥዖውን የሚያሳይበት መድረክ ያለብዙ ውጣ ውረድ ማግኘቱ ለዕድለኝነቱ አንዱ ማሳያ ነው።