የስየ ሀገር
ጽዮን ግርማ – ከትግራይ
በመኪና ከአቢአዲ የአንድ ሰዓት፤ በእግር ደግሞ ለሦስት ሰዓት የሚያስጉዘውን፣ ዳገታማ፣ ቁልቁለታማ፣ ጠመዝማዛ እና ድንጋያማ መንገድ አቆራርጠን ዳገት ላይ ከሚገኝ አንድ ቤት ደረስን – ቅዳሜ ግንቦት 14 ቀን 2002 ዓ.ም.። የቤቱ ብረት በር ተከፈተልን እና ወደ ውስጥ ዘለቅን። በድንጋይ የተሠራው ቤት ሰፊ ሳሎን አለው። አነስ አነስ ያሉ አራት መኝታ ክፍሎችንም ይዟል። የቤት ዕቃዎቹ አርጅተዋል፤ ሰፊው ግቢ አካባቢው ላይ በስፋት በሚገኘው ቀይ ድንጋይ ታጥሯል።