በቦሌ አየር ማረፊያ በሁለት ተጠርጣሪዎች ምክንያት በረራ እንዲዘገይ ተደረገ

Ethiopia Zare (ረቡዕ ሰኔ 9 ቀን 2002 ዓ.ም. June 16, 2010) ባለፈው ሣምንት ማክሰኞ ከአዲስ አበባ ቦሌ አየር ማረፊያ ወደ ቴልሰቪቭ ከምሽቱ 4 ሰዓት ከ35 ላይ ይበር የነበረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ለአርባ አምስት ደቂቃ ያህል እንዲዘገይ ተደረገ። ይህም የሆነው በደህንነት ሰዎች የተጠረጠሩ ሁለት ተሳፋሪዎችን ተጨማሪ ፍተሻ ሲደረግላቸው መሆኑ ታወቀ።