ለኢሳት ሥርጭት የተደረገው የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁ ተገለጸ

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ሰኔ 29 ቀን 2002 ዓ.ም. July 06, 2010)፦ በጥቂት ሀገር ወዳዶች የጋራ ጥረትና ስብስብ ተቋቁሞ በኢትዮጵያና በሌሎች የዓለም ክፍሎች መሠራጨት የጀመረውን የኢትዮጵያ ሳይተላይት ቴሌቪዥን ጣቢያ ለመርዳት በስዊድን መዲና ስቶክሆልም ከተማ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት መደረጉ ተገለጸ።