ይድረስ ለክቡር አቶ ፈቃደ ሸዋቀና (ከፌስቡክ የተገኘ)
ከሰለሞን አባ
ሰላምታየን እንደ “ያ ትውልድ” የፍቅር ደብዳቤ ሳላስረዝም ወደዋናው ጉዳየ ልግባ ።
ክቡርነትዎ ኢሳት የግንቦት ሰባት ልሣን መሆኑን አውቀው በአንዳንድ ነገር ሊያጋድል ይችላል ብለው መጠርጠርዎ መልካም ። ነገር ግን ለፖለቲካል ሰርቫይቫል ተብሎ ድንበር ያልለፈን አካሄድ ደግሞ ሌላው ወገን አይቶ እንደማያልፍ አልጠረጠሩም ። በሌላ በኩል ደግሞ የሌሎች ድርጅቶችንም አቤቱታ አልተመለከቱም ወይንም ሌሎች ድርጅቶችን ለመውቀስ ድፍረቱን ስላጡ ያማራ አክቲቪስቶችን ከነካካሁ ሌሎቹም መልዕክቱ ይደርሳቸዋል ብለው አስበውም ይሆናል ። አለበለዚያማ መኢአድን ያህል ድርጅት ሳያውቁት ብቻ ሳይሆ ሳይከታተሉትም አልቀሩም ። መኢአድ በም/ሕዝብ ግንኙነቱ አቶ ለገሠ ወ/ሀና አማካኝነት ወያኔ አባሎቻችንን ያፍናል ኢሳት ደግሞ ያባሎቻችንን የመታፈን ዜና ያፍናል ብሎናል ። በተደጋጋሚ ለኢሳት መግለጫ ቢልኩም ኢሳት በጓሮ በር አውጥቶ እንደሚጥል በግልፅ ተናግረዋል (ይህ እንግዲህ የዚህ ሦስት ቀን መነጋገሪያችን ሆኖ የሰነበተ ነው) ።
ክቡርነትዎ የራሳቸውን አይሰሩምና ኢሳትን ለማፍረስ የተነሱ የአማራ ነፃ አውጪዎች ብለው ክስ አቅርበዋል ። ለማፍረስ ያሚለውን ሐሜት ሳልፈራ ፤ ሳልሸማቀቅ እንዲሁ ችላ ብየ አልፈውና (ምክኒያቱም ስለሌለ) ኢሳትን መተቸት ሜድያ ይኑረንም አይኑረንም ይቀጥላል ። ኢሳት ከትችት የሚድነው ስነምግባሩን ሲያሳርም እንጅ አማራ ሜድያ ስለያዘ አይደለም ። ሜድያውን ደግሞ በቅርብ ያ ትናንት የግንቦት ሰባት አባሎችን ስድብ (degradation) ተቋቁሞ ለዛሬው ያማራ ልጆች መነቃቃት መሠረት የሆነው ሞረሽ ወገኔ በሬድዮ መልክ በቀናት ውስጥ ይጀምረዋል ። እርሰዎም ይህን ሞረሽ የዐማራ ድምፅ ሬድዮ በመርዳት ወደተሻለ ደረጃ ከፍ እንዲል የበኩለዎን እንደሚያበረክቱ ጥርጥር የለኝም ።
ክቡርነትዎ ኢሳትን ከስሕተቱ እንዲማር መምከር ተገቢ እንደሆነ ያስቀመጡት ድንቅ ሐሳብ በሌሎች በሐሳብ የተለዩዋቸውን “ጭቃ” እና የመሳሰሉ ቃላቶችን በመገብየት የስድብ ናዳ በሚያወርዱ ሰዎች ዘንድ ተቀባይነት የለውም ፤ አልተቀበሉትምም ። (ጭቃ! የሚለውን ኦድዮ ሰምተው ይሆናል) ።
ክቡርነትዎ እርሰዎ አማራነትን ከኢትዮጵያዊነት የሚነጥሉ ሐይሎች ብለው መሠረት የሌለው ክስ አቅርበዋል ። ኢሳት አማራ ብሎ ሊጠራን ያፍርና “ያማራ ክልል ሰው” ብሎ ከኢትዮጵያ ነጥሎ በክልል አጥሮ ሲያስቀምጠን የማይሰቀጥጠው የአንድ የፖለቲካ ድርጅት ድምፅ በምን ሒሳብ ነው ከአማራ ልጆች ጋር ተወዳድሮ አማሮች አማራነትን ከኢትዮጵያዊነት የሚነጥሉ ኢሳት ደግሞ የኢትዮጵያዊነት ዘማሪ ሆኖ የሚቀርበው ??
ክቡርነትዎ ሙሕር እንደመሆንዎ መጠን አንድ ነገር ተገንዝበዋል ። ይህም አሁን አማራ ነህ ብለው ሲነካኩት የሚሸማቀቅ ሳይሆን እምቢ የሚል ሐይል ለኢሳት አደጋ እንደሆነ “ኢሳትን ሊያፈርሱ” በሚለው ቃል ውስጥ ያለዎትን ስጋት አስቀምጠዋል ። ፈፅሞ ስጋት አይግባዎት !! ባይገርመዎት ኢሳትን ተችተዋል ከተባሉት አንዱ ሄኖክ የሽጥላ በቅርብ ኢሳትን የምንተቸው እንዲያስተካክል እንጅ ለማጥፋት አይደለም በማለት ኢሳትን መርዳት እንዳለብን አመላክቶናል ። ባይሆን የራሳችን ሜድያ ልክ የኦሮሞ ወንድሞቻችን እንዳላቸው ሁሉ እኛም ይኖረናል ። ይህ አማሮች የራሳቸው የሆነን የሬድዮና የቴሌቪዥን ጣቢያ መመስረት ኢሳትን የሚያፈርሰው ከሆነ ግን ተጠያቂ የሚሆን አካል የለም ።
ክቡርነትዎ ኢሳት የማንኛውን ያማራ ድርጅት እንደሚያገል እንዲነገርዎትና ወቀሳ እንደሚያቀርቡ አስተያየት መስጫ ላይ ጥያቄ አቅርበዋል ። ለዚህ መልስ አልለኝ ነገር ግን ስሞታ እንዲነግሩልኝ አለመሆኑ ይታወቅልኝ ። ባይሆን ከእርሶ የሚደበቅ ነገር አይኖረንምና በግልፅ አስቀምጠዋለሁ ። አዴሐን ከግንቦት 7 ቀደም ብሎ ኤርትራ በርሀ የገባው ያማራ ልጆች ድርጅታችን አንዱ የዚህ ደባ ሰለባ ነው ። ኢሳት ኤርትራ ገባሁ ባለበት ወቅት እባካችሁ ከሕዝብ አገናኙን እኛንም አናግሩን ብለው ኢሳቶችን ሲጠይቋቸው ኢሳት እነ ሳልሳይ ወያኔና ሌሎች የጎሣ ሓይሎች ጋር ስራ በዝቶበት ስለነበር ጆሮ አልሰጣቸውም ። በተደጋጋሚ በመደወል ኢሳትን ስለትግላቸው እንዲዘግብላቸው የሚያቀርቡትን ሁሉ አንድም ቀን አቅርበው አያውቁም ። ይህን ድርጅት ኢሳት ከመሬት ተነስቶ ከግንቦት ሰባት ጋር አንድ ሆነ የሚል ዜና ባሰራጨበት ወቅት ድርጅቱ መሠረት የሌለው ወሬ ነው ብሎ መልስ ሰጥቶ ነበር ። ኢሳቶች ይህን ድርጅታችንን በዚያ አቂመውበት ይሆን ?? ካልጋለብኩህስ ተብሎ ቂም ይያዛል ??
በሁለተኛ ደረጃ ዳግማዊ መ.ዐ.ሕ.ድ. የታላቁን መሪያችንን ፕሮፌሰር አስራት ፈለግ ተከትሎ የወጣው ድርጅታችን ወራትን ቢያስቆጥርም የጎሣ ሐይሎችን በባትሪ ፈልጎ የሚያቀርበው ፤ አማርኛን የሚጠሉትን ደግሞ በእንግሊዝኛ ለውይይት የሚጋብዘው ኢሳት ሊያናግራቸው ፈቃደኛ አይደለም ። እነርሱም አይለምኑትም (ቆራጦች ናቸዋ! ሲፈልግ በራሱ ይምጣ) ። መሪውን አናቅም በማለት ማስተባበል ውሐ አያነሳም ። ምክኒያቱም የድርጅቱ ድሕረ ገጽ ላይ ሊገናኟቸው ስለሚችሉ ። ሲጀመር የአንድን ድርጅት አመራር አፈላልጎ ማግኘት የጋዜጠኛ ስራ ሲሆን ለኢሳት ደግሞ በዘመነ ኢንተርኔት በጣም ቀላሉ ነው ። እባክዎን ሂደው እንዳይወቅሱ ። ይሄን እርሰዎ ስለጠየቁ ብየ እንጅ ላማራ ልጆች ኢሳትን እንዲሸመግሉ አይደለም የጻፍኩት ። እባክዎን ስሞትልዎ ።
ከምላጭ የሰላው ወጣቱ የአማራ ትውልድ ሳይሽመደመድ ፤ ሳይሳቀቅ ፤ ያለምንም ይሉኝታ መሰናክል ሆነው የሚገቡ ሐይሎችን እያገለለ ትግሉን ጥግ ያደርሰዋል ። ዕድሜና ጤና ይስጠን ብቻ ። እርሰዎን ያህል የሐገር ሐብት ትምክህተኛ አማራ ተብለው ከአዲሳባ ዩኒቨርስቲ የተባረሩበት አማራ መሆን መጭውን ትውልድ (የእኔን ትውልድ ጨምሮ) ሊያሸማቅቅ ከቶውኑ አንፈቅድለትም ።
ክቡርነትዎ ኢሳትን እየወቀስኩ አለመሆኑ ይታወቅልኝ ። ስለኢሳት ላውጋ ያልኩ እንደሆን ቀኑ ባጠረኝ ። ባንድ ወቅት በሞረሽ ላይ ከዘመተው የኢሳቱ ሊቀመንበር ጀምሬ እስከ ዛሬዋ ዕለት ያልሉ ስሕተቶችን ለመጻፍም አልተነሳሁም ። ባይሆን ዋናው ቁም ነገር እርሰዎ የጻፉትን እንደመደፋፈሪያ አድርገው የስድብ ናዳ የሚያወርዱትን ለማስገንዘብ ነው ።
ክቡርነትዎ ባሉበት ሰላምን እመኝለዎታለሁ ። ሰላም ውለው ይግቡ ።
yehe sewye betam mesere sew new !!
tsre Amara lik ende DRr entone kkk
minalebet Amarawin lekek beyaregen
G7 min yahil bekeflew new ?
ፈቃደ ሸዋቀና አማራ አይደለሁም ብሎ በኢሳት ተናግሯል።
ለዚህ ጽሃፊ ጥያቄ አልኝ።በጎንደርና በጎጃም የሚካሄደው ሕዝባዊ እምቢተኝነት ተጠቅልሎ ለአማራ ብቻ የሚሰጠው ለምንድን ነው ? ? ? ይሄ ወያኔ በቀደደው ቦይ መፍሰስ አይሆንም ወይ ? ? ? ከአማራው ጋር በጎንደርና በጎጃም የሚኖሩ አገዎች፥ቅማንቶች፥ሽናሻዎች፥ትግሬዎች፥ሌሎችም፥ሌሎችም እያሉ ጠቅሎ የአማራ ተጋድሎ ብሎ ማሳነስ ወደምን ያደርሳል ? ? With all due respect for all Amhara people please lets burry any thing and every thing that came with venomous and wicked woyane such as ክልል፥ዘር፥ቋንቋ፥ሃይማኖት ተኮር identification. በተለይ ክልል የሚለው ቃል ከፈጣሪው ከመለስ ጋር መቀበር አለበት።
how many amhara live in tgrea ==0=so why tgrea are in amhara land in gojjan agew and amhara 99/0mixed race there is no amhara there is no agew we are mixed amhara
iBAKACHIHU ISU YE ESAT POLITICAL ANALIST
FEDADE SHOAKENA GUREGNA YE SHABIA TELALAKI
IWQINA FELAGI ATTENETION SEEKER .
ዱሮም የአማራን ሕዝብ ክብርና አንድነት ሲነሳ ሆዳቸውን የሚቆርጣቸው በጣም በጣም ብዙ ብዙ ናቸወና ምንም ሣትሸማቀቁ የሞረሽ ወገኔን አላማ ከግብ አድርሱት ሁላችንም ከጎናችሁ ነን እንኳን ሬድዮ ጣቢያ ለምን ቴሌቭዥን ጣቢያ አይከፈትም!!
ሬድዮ ጣብያ ፖሊስ ጣብያ
ምን ሊበጃት ለኢትዮጵያ?
ኢሣት እንደሆነ የሻዕብያ!
ነቄ ብለናል በሚያዝያ።
It will,most effective, reach most people if amara radio is heard in mobile phone as fm.
Amara le amaraw tegadlo hulunm yadergal, ye gojam agew be tgrie woyanie sletebedele kamara gar tegadlo yadergal. Gn tgrie amaranna agewn yigelal enj kamara gar alwegenem. Amara tegalo mibalw akababiw amara teblo slemitaweqna gnbar qedem anqesaqashu amara slehone new. Qelel bale meseyem alebet
Yedil atebiya arbegna endate endemifelke yetaweke newe.Please,let us not be
thankless,having such monster infront of we get bitter in petty issues.Patience and tolerance are a way forward.
ሞረሽ ማለት ያረጁና የፈጁ ሀሳቦችን ይዞ እራሱን ገራ ገብቶት ሰው ገራ ለማጋባት የተፈጠረ የጥቂት ጠባቦች ጥርቅም ነው.
ይህ ጽሁፍ ከፍተኛ ምሬት አዘል መሆኑ በቀጥታ ከተሰነዘሩት ትችቶች ይልቅ ከበስተዃላው ያዘለውን ጉዳይ መመሩ ተገቢ መስሎ ታዬኝ፣፣እውን ኢሳት ላይ ያን ያክል ማማረር ተአማንነት ይኖረዋል? ኢሳት ደካማ ጎኖች አይኖሩትም አልልም፣፣ሚዛናዊነት ይኑረን ካልን እስካሁን ድረስ እንደ እሳት ወያኔን የተፋለመ ፓርቲ ወይም ሚዲያ አልተፈጠረም፣ብዬ በልበሙሉነት ልመሰክር እችላለሁ፣፣ምናልባት ቅንጅትስ? ሊባል ይችል ይሆናል፣፣የቅንጅት በጣም ላጭር ጊዜ ብቻ ነው፣፣
ጸሀፊው ለምን በጣም ተማረሩ? ኢሳት እርሳቸውን በፈልጉት መጠን አላገለገላቸውም ይሆናል፣ ይህ ደግሞ ሌሎች በሚልዮን የሚቆጠሩት የሚያገኙትን ድጋፍ ዘሮ ሊያስቀር የሚገባ አይመስለኝም፣፣ለዚህ ሁሉ ምስክሩ እያንዳንዱ ህዝብ እንጂ የህዝብ ተወካይ ነኝ ብሎ እራሱን ሹሞ የሚቀርብ ግለስብ ሊሆን አይገባም፣፣ እንደሚታወቀው ወያኔ ኢሳትን ዋነኛ ጠላቱ በማድረግ ለማጥፋት እጅግ ደክሟል፣ የሞክራቸው ብዙ ዜዴዎች ከሽፈውበታል፣፣ይህም ማሌት ተስፋ ቆርጦ ጥረቱን ያቆማል ማለት አይደለም፣፣ምናልባትም እሾህን በእሾህ የማሉትን ዜዴ ለመጠቀምም ይሞክር ይሆናል፣፣በማይረባ ልዩነት ማንም ሰው በዚህ ወጥመድ ውስጥ ባይገባ ደስ ይለኛል፣፣ ተጨማሪ ሚዽዲያ መክፈት ቢያስፈልግ እንኳ ሀገር የማይክደውን የኢሳትን አገልግሎት ሳያጥላሉ፣ አዲስ ለመክፈት ስላሰቡት ሚዲያ እስፈላጊት በሚገባ ማስረዳትና ድጋፍ ሲገኝ ዕቅዱን ተግባራዊ ማድረግ ብቻ ተግቢ የሚሆነው፣፣ መወነጃጀል የሚጠቅመው ወያኔን ብቻ ነው፣፣ ደጋግመን እናስብበት፣፣
thanks man you said it all
DD
Dr Birhanu sathon atikerim ,, kkkkkkkkkkkk
Abich
tewen bakih kk
Esat ye shabya ena ye G7 aynina joro new
bene comediyan entina tiret yetemeserete kkk
mognihen babur tabeya felig !
Firing from work for their being amara is a big crime