የጎባጣ አሽከር አጎንብሶ ይሄዳል (መርሐጥበብ፣ ከባህር ዳር)

መርሐጥበብ
ከባህር ዳር

tigist-satenawnews-6
ዲንቢጧ የሕወአት ተላላኪና የተላላው ደርጅት ብአዴን አባል ገነት ገ/እግዚአብሔር ገ/ኢየሱስ

እኔማ ዘንድሮ በግርምት መሞቴ ነው፡፡ የሰው ልጅ በሚያውቀውም ሆነ በማያውቀው እየገባ መዘባረቁ የግርምቴ መነሻ ነው፡፡ የሻይ ማንኪያ ያህል መረጃ ይዞ ጭልፋ ሙሉ ወግ ማውጋት ምን የሚሉት በሽታ ነው፡፡ ያደቆነ ሰይጣን ሳያቀስ አይለቅም እንዲሉ በትንሽ ነገር ሲነኩ እንደ ቆሌ ዶሮ መርገፍገፉ የሰሞኑ የአገሪቱ ካብኔ ተብየዎች ባህርይ በመሆኑ ከመደነቅ ይልቅ መገረም ነው የዕለት ቀለቤ፡፡

ሰሞኑን የአማራ ክልል ከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ በኃላፊነት የምትመራው ዲንቢጧ የሕወአት ተላላኪና የተላላው ደርጅት ብአዴን አባል ገነት ገ/እግዚአብሔር ገ/ኢየሱስ በምትፈጽመው ድርጊት በመላው አማራ ክልል የሕዝብ ጥላቻ ከማትረፏ በላይ አመኔታ የሌላት ደካማ ፍጡር መሆኗን በምትመራው ተቋምና በተለያዩ መድረኮች ሲነገራት የማትሰማና ከወድቀት የማትማር የባህር ዳር ከተማ ወጣት እያሳደነች የምታሳስርና የምታስገድል እንዲሁም በአማራ ክልል ሕዝብ ስም የምትነግድ ትውልድና ዘመን የማይረሳት ጠላት መሆኗ እየታወቀ የክልሉ መንግስት ቃል አቀባይ ተብየው ንጉሱ ጥላሁን ለክልሉ መንግስት ቃል ማቀበሉን ትቶ ለወ/ሮዋ ጥብቅና መቆሙን በራሱ የማኅበራዊ ድረ ገጽ በለቀቀው መረጃ መታዘብ ችያለሁ፡፡

“የጠሉትን ማስጠላት ምን ያደርጋል“ በሚል ርዕስ የለቀቀው መረጃ “ወ/ሮ ገነት ሙሰኞችን አጥብቃ የምትታገል ምርጥ የሴት አመራር መሆኗን መመስከር እፈልጋለሁ፡፡ ነገር ግን በቢሮው ውስጥ ያሉ መሃንዲሶች በአጭር ጊዜ በሙስና ተዘፍቀው ሃብት በማካበት መኪና መግዛት፣ የቤት ባለቤት መሆን እና የቅንጦት ኑሮ ከማንም የኢትዮጵያ ህዝብ በላይ ለመሆን ሲባል ይህች ሴት የምትጠላውን ኪራይ ሰብሳቢነት ስለሚሰሩ ሴትነቷ ሳይገድባት ትታገላቸዋለች፣ ከስራ ታግዳለች፤ ለአብነት በቅርቡ የኮንትራክተሮችን የደረጃ ማሳደግ ስራ ላይ የተሰማሩ ባለሙያዎች ከአንድ ኮንትራክተር እስከ 20 ሽህ ብር በመቀበል ህጉና መመሪያው የሚጠይቀውን መረጃ ሳያሟሉ ደረጃ የማሳደግ ስራ የሰሩ 4 ባለሙያዎችን ማንም ወንድ ያልደፈራቸውን እሷ ከስራ አግዳቸዋለች ታዲያ ይህችን ሴት ከዚህ በላይ ብትባልም አይገርመኝም ነገር ግን ደሃው የአማራ ህዝብ ነገ እለወጣለሁ እያለ የሚከፍለውን ግብር ሙሰኞች ሲዘርፋት ዝም ብዬ አላይም በማለቷ እንድትሸማቀቅ የሚያደርጉ የፌስ ቡክ ጀግኖች የገባችሁም ያልገባችሁም ከዚች ጀግና ሴት ራስ ላይ ብትወርዱ ጥሩ ነው፡፡ ከሚፃፈው ነገር ስነሳም ወ/ሮ ገነት ተወልዳ ያደገችው ባህር ዳር ቀበሌ 11 ሆኖ ሳለ ሌላ ታርጋ በመስጠት በሴትነት አታሸማቋት ኪራይ ሰብሳቢው ትታገልበት ይህ እውነታ ታሪክ ነው፡፡” የሚል ነው፡፡

እንደ ቃል አቀባዩ ዲስኩር ሙሰኞችን አጥብቃ የምትታገል ምርጥ የሴት አመራር መሆኗን መመስከር እፈልጋለሁ ማለቱ “የጎባጣ አሽከር አጎንብሶ ይሄዳል” የሚለውን አባባል ለጽሁፌ በርዕስነት እንድመርጥ አስገደደኝ፡፡ ለምን ቢሉ ከጌታው ከፍ ብሎ ላለመታየትና ጌታውን ላለማሳጣት ነው የሚለው አባባል ትዝ አለኝ፡፡ የንጉሱ ጠበቃነት በመረጃ ያልተደገፈ ነው፡፡

በሶማሌ አንድ አባባል አለ ልንገራችሁ። አባባሏን የሰመኋት ይህን ጦማር ስሞነጫጭር ነው፡፡ አንዲት ሶማሌ ሴት ነበረች። በሶማሌ ባህል ጋብቻ በግልጽ ካልሆነ አይፈጸምም። አንዲት ሶማሌ ከባህሉ ውጭ በድብቅ የወደደችውን ባል አገባች። ሁለቱ ተጋቢዎች  ከጊዜ በኋላ እንናገራለን በሚል ስምምነት የተጋቢ ቤተሰቦች ሳያውቁ አብረው መኖር እንደጀመሩ ባል በድንገት በመኪና አደጋ ሕይወቱ ያልፋል። ሚስት እንዴት ብላ ታልቅስ፤ ምክንያት አጣች። ‘ባሌ ነበረ’ ብላ ካለቀሰች፣ ሕጋዊ ባል አይደለም፤ ስለዚህ ‘ብልግና ነበር የምትሰሩት፤ መቼ ነው የተጋባችሁት?’ ሊባል ነው። ስለዚህ ልጅቷ ተጨንቃ ዝም አለች። በዚህ አጋጣሚ ከነበራቸው ፍየሎች አንዱ በቀበሮ ተበላና ሞተ የሚባል ወሬ በእረኛው መልዕክት ይደርሳል፡፡ ‘የኛ ፍየል እኮ በቀበሮ ተበላ ይላታል። ሚስቲቱም ምክንያት አግኝታ በዛ አለቀሰች። የልቅሶ ደረጃውን በመገንዘብ ይህን ያዩ አባትም “ልጄ ይሄ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነው!” አላት። ይባላል፡፡ የንጉሱ ወግም ከገነት ትግል ጀርባ ያለውን ድርጊት አለመገንዘቡን ያስታውሳል፡፡

በቅድሚያ ገነት ተብየዋን ግለሰብ በሚገባ አያውቃትም፡፡ የቀን እንጂ የሰው ጀግና እንደሌለውና በአንድ ድርጅት መሰባሰብ የግለሰቦች ማንነት መገለጫ እንደማይሆን እንኳን የመንግስት ቃል አቀባይ በሌላም ሙያ የተሰማራ ይዘነጋዋል የሚል ህሳቤ የለኝም፡፡ የንጉሱ ሀሳብ አላዋቂ ሳሚ … ነው የሆነብኝ፡፡

ግለሰቡ በቢሮው ውስጥ ያሉ መሃንዲሶች በአጭር ጊዜ በሙስና ተዘፍቀው ሃብት በማካበት መኪና መግዛት፣ የቤት ባለቤት መሆንና የቅንጦት ኑሮ እየኖሩ ያሉትን ጾታዋ ሳይገድባት ትታገላለች ያለው ሀሳብ ጅምላ አስተያየት በመሆኑ ብዙም ባልቀበለውም ድክመቱንና ሀቁን ጉዳይ ለማሳየት እሻለሁ፡፡ አቶ ንጉሱ ቆርጦ ቀጥል አመለካከትህ ብዙም ርቀት አያስጉዝህም፡፡ የአማራ ክልል አመራር ስሙ በተነሳ ቁጥር የምትሰነዝረው አስተያየት ለስልጣንህ ማቆያ የምትጠቀምበት ስትራቴጂ እንደሆነ ማስረጃ መጥቀስ አያስፈልግም፡፡ የጎንደር ቅዳሜ ገበያ በእሳት ሲጋይ ሰሜን ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ላይ ሆነህ በቪኦኤ የአማረኛ ቋንቋ ሬዲዮ ጣቢያ የሰጠኸው መግለጫ ተጠቃሽ ነው፡፡ በሌለህበትና በማታውቀው ጉዳይ መዘባረቅ በክራሞት የተላበስከው የሙያ ካባ ስለሆነ ብዙም  አይደንቀኝም፡፡ ዛሬ ደግሞ ስለ ግለሰቧ የሰጠኸው አስተያየት ብዕሬን ከወረቀት ጋር እንዳዋድድ አስገደድከኝ፡፡ ምክንያቱም ነገ ደግሞ ሌላ ላለማለትህ ዕምነት ስላጣሁብህ ነው፡፡

በእኛ አገር የጋዜጠኝነት ሙያ  የአንድ ወገን መረጃ ዜና እየሆነ አገር ማመስ ከተጀመረ ሩብ ዓመት እንዳለፈው ላንተ መንገር ለቀባሪው ማርዳት ነው የሚሆንብኝ፡፡ ሴትየዋ ብቻ የነገረችህን ተቀብለህ በቢሮው ውስጥ ያሉ መሃንዲሶች ኪራይ ሰብሳቢዎች ናቸው ማለትህ አዘንኩልህ ይህ ቀን እንዲህ ሆኖ የሚቀር መስሎህ ሁሉንም መሃንዲሶች በኪራይ ሰብሳቢዎች ቅርጫት ማስቀመጥህ ዘንግተኸው እንደሆነ እንጃ እንጂ የኮንስትራክሽን ዘርፉን የሚመራውም ኃላፊ መሃንዲስ ነው፡፡ ዳሩ ከመንግስት ቃል አቀባይ ምን ይጠበቃል፡፡

አቶ ንጉሱ ከሰጠኸው አስተያየት ተነስቼ ለአብነት ብለህ ያቀረብከው ሀሳብ “ጅል አይሙት እንዲያጫውት” የሚያሰኝ ነው፡፡ ቢሮው የኮንትራክተሮችን የደረጃ ማሳደግ ስራ ላይ የተሰማሩ ባለሙያዎች ከአንድ ኮንትራክተር እስከ 20 ሺህ ብር በመቀበል ህጉና መመሪያው የሚጠይቀውን መረጃ ሳያሟሉ ደረጃ የማሳደግ ሥራ የሰሩ 4 ባለሙያዎችን ማንም ወንድ ያልደፈራቸውን እሷ ከስራ አግዳቸዋለች ያልከው ጉዳይ ጫፍ ይዘህ መሮጥህን ያሳያል፡፡ በቅድሚያ ምነው ዛሬ ይህን ሀሳብ ይዘህ ወጣህ ጃል? ከነገረ ቀደም በዚህ ዘርፍ ከሥራ የታገደ አይደለም አራት አንድም ባለሙያ የለም፡፡ በሥራ ተቋራጮች የደረጃ ማሳደግ ተግባር ከመመሪያ ውጭ ተደራድረዋል በሚል ተብለው የተጠረጠሩ በተለያየ የሥራ መደብና ደረጃ የሚገኙ ባለሙያዎች ከነበሩበት የሥራ መደብ አንተ እንዳወራኸው ታግደው ሳይሆን በሌላ የሥራ መደብ ተዛውረው እየሠሩ እንዳሉና እስካሁንም የተጠረጠሩበት ጉዳይ አስካሁን ዳር ሳይደርስ ባለሙያዎችም በተመደቡበት የሥራ መደብ እያገለገሉ እንደሚገኙ ልብ ትለው ይገባል፡፡

“ወዳጄ” አለ አጎቴ ታየር ወዳጄ ንጉሱ የወግህን ብዕር አልወደድኩትም፡፡ በደብዛዛ አመለካከት የወጣ ሀሳብ ከማደናቆር ውጭ ሌላ ፋይዳ የለውም፡፡ ታዲያ ይህችን ሴት ከዚህ በላይ ብትባልም አይገርመኝም ያልከው ነገር አልገባኝም ለምን አትነግረንም ቃል አቀባይነትህን ዘነጋኸው፡፡

ደሃው የአማራ ህዝብ ነገ እለወጣለሁ እያለ የሚከፍለውን ግብር ሙሰኞች ሲዘርፋት ዝም ብዬ አላይም በማለቷ እንድትሸማቀቅ የሚያደርጉ የፌስ ቡክ ጀግኖች የገባችሁም ያልገባችሁም ከዚች ጀግና ሴት ራስ ላይ ብትወርዱ ጥሩ ነው ያልከው ጉዳይ እጅግ አስጋራሚና እስስታም ባህርይን የሚያንፀባርቅ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡ ርካሽ ተወዳጅነት የሚፈጥረው ስሜት በመሆኑ አልተቀየምኩህም፡፡ ግለሰቧ ልውደድህ ብትልህስ በምን ቀልቧ ትወዳሃለች ጊዜውንና ቦታውን ማየት ነው እንጂ፡፡

ካቀረብከው ሀሳብ ሌላው ያስገረመኝ ጉዳይ “…ከሚፃፈው ነገር ስነሳም ወ/ሮ ገነት ተወልዳ ያደገችው ባህር ዳር ቀበሌ 11 ሆኖ ሳለ ሌላ ታርጋ በመስጠት በሴትነት አታሸማቋት ኪራይ ሰብሳቢው ትታገልበት ይህ እውነታ ታሪክ ነው፡፡” ያልከው ነው፡፡ ይህ ሀሳብ ጤንነትህን ሁሉ እንድጠራጠር ነው ያደረገረኸው

በቅድሚያ ምነው ስሟን ብቻ ጠርተህ ተውካት? ብዕርህ የፍርሃት ቀለም ለምን ይተፋል? ሌላው ትውልድ በማን ይገለጻል? በወላጅ ወይስ በቦታ? ደግሞም የግለሰቧን የትውልድ ቦታ ለማወቅ የግል ማኅደሯ ከሚገኝበት ተቋም ፈትሽ፡፡ እያሸማቀቃት እያለው ጾታዋ ሳይሆን ተግባሯ ነውና በመጀመሪያ ኪራይ ሰብሳቢነት ከመታገሏ በፊት ራሷን ከኪራይ ሰብሳቢነት ታጽዳ ያኔ የቃል አቀባይነትህ ተግባር ትፈጽማለህ፡፡ ዘመዴ ጫፍ ይዘህ አትባዝን- አበቃሁ፡፡

 

6 Comments on “የጎባጣ አሽከር አጎንብሶ ይሄዳል (መርሐጥበብ፣ ከባህር ዳር)”

  1. የህዝብ ጥያቄ ስልጣን በአንድ አንስተኛ ጠባብ እጅ ስለወደቀ እኩል ተካፍለን አገራችን በጋራ እናስተዳድር ነው። የ 100 ሚሊዮን ህዝብ አገር በጥቂቶች መተዳደር ይብቃ። የአደራ መንግስት ሁሉንም ያካተተ ይቋቋም ነው ያለው ህዝቡ። ጥገና ሳይሆን ለውጥ። ሰው መቀያየር ሳይሆን የስርዐት ለውጥ። አባ ድላን አንስቶ ተሾመ ቶጋን መተካት ሳይሆን ምሁራንን የአገር ሽማግሌዎችን ተቃዋሚዎችን ያካተተ የአደራ መንግስት በአስቸኳይ ይቋቋም ነው ጥያቄው መልሱም እሱ ብቻ ነው።
    20 ሚሊዮን ብር ብቻ?
    ታሪኩ እንዲህ ነው፡፡

    አዲስ አበባ ቄራ አካባቢ አንድ ቤት ለሽያጪ ወጥቷል፡፡ እድሜው በ18 እና 20 መካከል የሆነ ልጅ የመጀመሪያ ቤት ገዢ ሆኖ ከቦታው ይገኛል፡፡ ሻጪዎችም ከእድሜን ልጅነት፣ ከሀገሪቱ ሁኔታና ከዋጋው ውድነት አንፃር ለመቀለድ በማሰብ ከቤቱ ዋጋ በእጥፍ ጨምረው 20 ሚሊዮን ብር ነው ይሉታል፡፡ ለመሳቅና ልጁንም በማስደንገጥ ለማባረር አስበው እንደ ቀልድ ያደረጉት የ20 ሚሊዮን ብር ጨዋታ ግን ቁም ነገር ሆነና ቤቱን ልየው፣ ዋጋ ቀንሱ ወይም ሌሎችን በዚህ ወቅት መጠየቅ የሚገባቸውን ሳይጠይቅ ኑ እንፈራረም አለና አስደነገጣቸው፡፡ ለማመን ባለመቻላቸውና እየቀለደባቸው አንደሆነም ገምተው ለመቆጣት እየቃጣቸው እያሉ የ2 ሚሊዮን ብር ቼክ አወጣና የመፈራረሚያ ቅድሚያ ክፍያ አሳያቸው፡፡ እነሱም ያልጠበቁትን ግብይት እንዳደረጉ በመረዳት ካቀዱት ዋጋ በእጥፍ አትርፈው ቤቱን 20 አመት ለማይሞላ ልጅ በ20 ሚሊዮን ብር ሸጡ፡፡

    ይህም ብቸኛው ክስተት ሳይሆን በስፋትና በጥልቀት በየዘርፉ በየቀኑ የሚፈፅሙት ወንጀል ነው፡፡

    ትልቁ ጥያቄ ግን ይህ ልጅ ማን ነው የሚለው ብቻ ሳይሆን የማን ልጅና ዘመድ ነው የሚለው ነው፡፡ ልጁ ሕውሓት ነው፡፡ ወላጆቹና ዘመዶቹም ያው ሕውሓቶች ሲሆኑ አነማን ናቸው የሚለው ግን መጣራት ቢኖርበትም ሁሉም በዚህ አይነት ወንጀል ተሰማርተው ስለሚገኙ ሁሉም ናቸው ብሎ በሀዘን ማለፍ ሳይሆን በነሱ እየተበደለ ያለ ህዝብ በውስጡ ሰላም አግኝቶ፣ አንድነትን ፈጥሮና በጋራ ተነስቶ ሊያስወግዳቸው ይገባል፡፡ ወንጀላቸው ብዛቱ፣ አይነቱና ይዘቱ በየቀኑ አዲስና ህዝብ ሊቋቋመው የማይችል ሆኗል፡፡

    • Sinebeb: x ende xornet =war.

      Mentyoch welede ya belay zeleqe.
      Negarit temeta awajm xedeqe.
      Bebilawa taredo agazi wedeqe.
      Nexa mewcaw menged blhat
      taweqe.
      Amara woyanien mawdemiya
      mesariya taxeqe.
      Kegdih abeqa agazi aleqe deqeqe.
      woyanie agazi yimeta kemr.
      Tewesno adrual tegelo endiqeber.
      Lewore negari and enkua sayqer.
      Xfatu yebeza yemayalq bineger.
      Ziegochn fejtual amekayito bezer.
      Amara atmarew mretalbown xor.

      • Sinebeb: x ende xornet = war.

        Amarawechun endayseru yabarerch tgrie meqxerua gubzna tebal.
        Ke amara letgrie woyanie yemisebeseb genzeb saysheraref gebi endihon mexarua gbzna aydelem.
        Tera tgrie kemeriet ansto yalkllua be amara qulf xqm meshom new mesna.
        Welqait, xegedie, humeran ke amara qemto wede tgrai mewsed new musna, wonjel xelatnet. Amara sayhon amara asmeslo
        b.a.d.n teblo yetgrie woyanie telalaki huno tgrie woyanien yizo Amaran megdel, maser, seqoqa mefexem, mezrefna mafenaqel new talaqu msna, wonjel.
        Yihn eyefexemq slemusna le menager moralm hone hgawinet fexmo yelehm.

  2. we Ethiopians hate people’s who stand for the truth that is not a new thing in fact you can know the one that people hate is innocent because the only weapon they got is TALKING!!! and that is for you too.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*