ወጣት በለጠ ንብረቱ ቸኮለ እድሜው 17 የሕወሓት ቅጥረኞች በጥይት ገድለውታል ። አሁን ውጤት ሲመጣ ሁሉንም የትምህርት አይነት “A” አስመዝግቦል ።

ወጣት በለጠ ንብረቱ ቸኮለ እድሜው 17 ፣ የ2008 ዓም የአስረኛ ክፍል ማትሪክ ተፈታኝ ነበር።
ወረታ ላይ በተደረገው የአማራ ተጋድሎ ሳቢያ የሕወሓት ቅጥረኞች በጥይት ገድለውታል ። አሁን ውጤት ሲመጣ ሁሉንም የትምህርት አይነት “A” አስመዝግቦ ኖሯል ።
ይሄን እጅግ የሚያኮራ ውጤት መጣ… ባለውጤቱ ወንድማችን በለጠ ግን የለም ። አማራ በመሆኑ በለጋነቱ ተቀጠፈ ። ያማል!!
የግድያውን ትዕዛዝ የሰጡት የፎገራ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አሰሜ ፈረደ እና የወረታ ከተማ የፀጥታ ኃላፊ ተዋበ ጌጡ የተባሉ የህወሓት ቅጥረኞች ሰሲሆኑ ግድያውን የፈፀመው ግለሰብ ደግሞ በወረታ ከተማ ቀበሌ 01 ልዮ ስሙ እስቴ በር በሚባል ቦታ ኗሪ የሆነው አቶ ውቤ መለሰ መሆኑን አረጋግጠናል፡፡