ወያኔ ተርበትብቷል! የአዲስ አበባ ሕዝብ በቅርብ ጊዜ የወያኔን ግብዓተ መሬት መፈጸሙ አይቀርም!!!

አይ ወያኔ! Muluken Tesfaw

Muluken Tesfaw's Profile Photoነብሰ ገዳዩ ወያኔ ሸዋ ላይ ግብዓተ መሬቱ እንደሚፈጸም ጠንቅቆ ስለሚያውቅ፣ አዲስ አበባ ውስጥ ምንም ዓይነት የተሰበሰበ ሕዝብ እንዳይኖር የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም፡፡ ሆኖም የውሸትና የቅጥፈት አባት ነውና እንደለመደበት አዲስ አበባ ውስጥ መሰብሰብ ይቻላል የሚል ርካሽ ፕሮፓጋንዳውን ለማሰራጨት፣ ትናንትና መስከረም 16 ቀን 2009 ዓ.ም. የደመራ በዓልን ለማክበር በተሰበሰበው ኦርቶዶክሳዊ መሃል በሺሕዎች የሚቆጠር አጋዚና የሲቪል ልብስ የለበሱ ሰላዮችን መድቦ ሲያበቃ፣ ‹‹ደመራው በደመቀና ሰላማዊ በሆነ መልኩ ተከብሯል›› የሚል ቱልቱላውን ሲነፋ ተስተውሏል፡፡ ወያኔ ማለት ይህ ነው! ውሸት፣ ቅጥፈት! ክህደት! አፈና! ግድያ!
ትናንትና ከቀኑ 5 ሰዓት ጀምሮ የአዲስ አበባ ሕዝብ በየቦታው ሲፈተሽ ውሏል፡፡ አጋዚ ሁሉንም መንገዶች ጠርቅሞ በመዝጋቱ ምክንያት ከፍተኛ የሆነ የትራፊክ ችግር የነበረ ሲሆን፣ ሕዝቡ በተለይም ሥራ ላይ የዋለው ሲቪል ሰርቫንት በእግሩ እንዲኳትን ተገዷል፡፡ ወያኔ ተርበትብቷል! በየቤተክርስቲያኑ እየተዘዋወረ ዘማሪያኑንን ሲያስጠነቅቅ እንደነበርም ታውቋል፡፡
ወሮበላው ወያኔ አዲስ አበባ ላይ ምንም ዓይነት ነገር እንዲነሳ አይፈልግም፡፡ ሆኖም የአዲስ አበባ ሕዝብ በቅርብ ጊዜ ውስጥ መነሳቱና የወያኔን ግብዓተ መሬት መፈጸሙ አይቀርም!!! የአዲስ አበባ ሕዝብ ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ጊዜያት በተናጠል እየተነሳ ተመትቷል፡፡ አሁን ግን ብቻውን አይደለም!! የአማራና የኦሮሚያ ክልል ሰፊ ሕዝብ አለለት!
በመሠረቱ አዲስ አበባ ውስጥ ወያኔን ለማንበርከክ ቀላል ነው! ጀግኖቹ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የተከተሉትን ዝርዝርና የማያቋርጥ የትግል ስትራቴጂ መጠቀም፣ የአማራና የኦሮሞ ሕዝብ እየተጠቀመባቸው ያሉ የትግል ስታራቴጂዎችን ከአዲስ አበባ ሁኔታ አንጻር አስተካክሎ መጠቀም፣ ስኬታማውን የቱኒዚያ ሕዝብ የአመጽ ስትራቴጂ ከአዲስ አበባ አንጻር ቃኝቶና ሌሎችን ዘዴዎች ጨምሮ መጠቀም ወዘተ. ይቻላል፡፡ ይህን ሁሉ በቅርቡ የምናየው ይሆናል፡፡
የአዲስ አበባ ሕዝብ ከአማራና ኦሮሞ ሕዝቦች የበለጠ እንደሆነ እንጂ ያነሰ አልተጨቆነም፡፡ ይህ ሕዝብ በ1997 ዓ.ም. ወያኔን አንቅሮ እንደተፋውና ከዚያን ጊዜ ወዲህ በለየለት አፈና ውስጥ የሚኖር ሕዝብ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ስለሆነም ብዙሃኑ አዲስ አበቤ ወያኔ እንዲቀበርና በላዩ ላይ ሙጃ እንዲበቅልበት ይፈልጋል፡፡ 2009 ብዙ ያሳየናል!!!!

7 Comments on “ወያኔ ተርበትብቷል! የአዲስ አበባ ሕዝብ በቅርብ ጊዜ የወያኔን ግብዓተ መሬት መፈጸሙ አይቀርም!!!”

  1. x ende xornet = war

    Awe Ahun gebay! Leka tgrie woyanie aster mamonna kedern yabarere ende etio-sumaliena afar letefenaqelu tgriewoch genzeb alaqerblet slalu new.
    Enkuan le amara le lielam ymiterf agazi endalew betenagere bemagstu sumalie, afar, lielochum dresuly tgrie be amara tefeje sil merietun woyanie yewosedebet ye afar meriwoch ena yezer fjit yetgrie woyanie yaderesebet ye etiopia sumalie meriwoch sayterfachew yeber erdata sexuna yeslxan edmieyachewn arazemu. Qxfetun yeteredu ye oromo meriwoch genzeb balemsxetachew keslxan woredu. Mnalbat genzeb yemisexu yihonal yetekuachew.

  2. Ya tigere ket salbada ka Addis Ababa atabarowachew. Kulekwale salamebalu ketachew are yelawem labed yamachale. Feta hew gen frog new memaselut,kenterachew bizum aydelem.

  3. 1. ጥበቃ ዋና መምሪያ: መኮንን (ወዲ ኮበል) ይህ የVIP ጥበቃን ጨምሮ አየር መንገድንም ይቆጣጠራል
    2. ክንፈ ማሰልጠኛ: ታደለ ፀጋዬ ዳይሬክተር፤ ዶ/ር ሀሽም ተውፊቅ ም/ዳይሬክተርና የአስተዳደርና ፋይናንስ ኃላፊ
    3. የቴክኒክ መረጃ: ማዕሾ ( ማዕሾ ከአምስቱ የጌታቸው ምክትሎች አንዱ ነው) የሚመራው ቢሆንም ጌታቸው በቀጥታ ይቆጣጠረዋል
    4. የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ ዋና መምሪያ: ገ/ዮሃንስ ተክሉ ዋና ዳይሬክተር
    5. የውጭ መረጃ ዋና መምሪያ: ሀደራ ( ሀደራው ሌላው ከአምስቱ የጌታቸው ምክሎች አንዱ ነው) ይመራው የነበረ ሲሆን አሁን ገና ቋሚ ሰው አልተተካም። ልዑል ታፈረ ምክትል ነው።
    6. የውስጥ ደህንነት ጥበቃ ዋና መምሪያ: አማኑኤል ኪሮስ ዋና ዳይሬክተር ሲሆን ደርበው ደመላሽ ምክትሉ ነው
    7. ፀረ ሽብር መምሪያ: ተስፋዬ ዑርጌ ኃላፊ ሲሆን (አግ7፣ ኦነግ፣ አልሸባብ ወዘተ.) ሲሆኑ ምንም እንኳን የራሱ ዋና ክፍል ቢኖረውም አርበኞች ግንቦት-7 ን የመምሪያው ኃላፊ በቀጥታ ይከታተላል።
    7.1. የአርበኞች ግንቦት-7 ዋና ክፍል ኃላፊ ሸዊት በላይ ነው [ይህንን ጽሁፍ በመመርመር ጽህፍ እንደሚበዛበት፤ ዛሬ ሰክሮ እንደሚያድር እገምታለሁ]
    8. የክትትል መምሪያ ኃላፊ: አፅብሃ ግደይ
    9. የፀረ ስለላ መምሪያ ኃላፊ: ነብዩ ዳኘ
    10. የኦፕሬሽን መምሪያ ኃላፊ: ቢኒያም ማሙሸት
    11. የአስተዳደርና ፋይናንስ መምሪያ ኃላፊ: ፍቅሩ በቀለ
    12. የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ክትትል ኃላፊ: አብይ ኃይሉ [እጅግ ከሚያሳዝንኝ ነገሮች አንዱ የዚህ ክፍል ሥራ ነው። ዩኒቨርስቲዎችና ኮሌጆችን መማሪያዎች ሳይሆን እስር ቤቶች ያደረጓቸው የዚህ ክፍል ሠራተኛች ናቸው። የዚህ ክፍል ሠራተኞች የሚሠሩት ደባ ለተከታተለ 32 ዩኒቨርስቲ ሳይሆን 32 እስር ቤቶች እንደተገነቡ ይገባዋል]
    13. የፖለቲካ ፓርቲዎች ክትትል ዋና ክፍል ኃላፊ: አመለወርቅ ገ/ሃዋሪያ (አቶ)፤ ይስሃቅ ይህደጎ ም/ኃላፊ [ይህ ክፍል ፈቃድ ተሰጧቸው የሚንቀሳቀሱትን ተቃዋሚ ፓርቲዎችን በጠላትነት ፈርጆ ሊያጠፋቸው ሌት ተቀን ይሠራል]
    14. የኢኮኖሚ ደህንነት መምሪያ ኃላፊ: መድህኔ ታደሰ ኃላፊ፤ ፍቃዱ መረሳ ም/ኃላፊ
    15. ጥናት መምሪያ ኃላፊ: በላይ አሰፋ ሲሆን አሁን ለምን እንደሆነ ባልገባኝ ሁኔታ እየፈረሰ ያለ መምሪያ ነው
    16. የክልሎች ማስተባበሪያ መምሪያ ኃላፊ: ግርማ ተገኝ ሲሆን 9 ን ክልሎችና አዲስ አበባንም ይመራል:: ከእነዚህ መካከል፦
    16.1. የአማራ ክልል ኃላፊ: እንግዳው አበባው
    16.2. የደቡብ ክልል: እዮብ ተወልደ
    16.3. ኦሮሚያ ክልል: አዲሱ በዳዳ ያስተባብራሉ
    17. የአዲስ አበባ ደህንነት ዋና ክፍል: ጎሃ አፅብሃ ገ/ሂወት ሲሆን 10ሩን ክ/ከተማዎች ያስተባብራል
    17.1. አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ: ጋሻው አበበ ኃላፊ
    17.2. ቦሌ ክ/ከተማ ኃላፊ: ምስጋናው አየለ:
    17.3. ን/ላፍቶ ክ/ከተማ ኃላፊ: ሲሳይ ገ/ፃዲቅ ኃላፊ
    17.4. ልደታ ክ/ከተማ ኃላፊ: አሸናፊ ነጋሽ ኃላፊ
    17.5. ኮልፌ ክ/ከተማ ኃላፊ: ሀይሉ ታደሰ ኃላፊ
    17.6. ቂርቆስ ክ/ከተማ ኃላፊ የሺጥላ ካሳ ኃላፊ
    17.7. አራዳ ክ/ከተማ ኃላፊ: ሀጎስ ሀለፎም ኃላፊ
    17.8. የካ ክ/ከተማ ኃላፊ: ክፍሎም በየነ ኃላፊ
    17.9. ጉለሌክ /ከተማ ኃላፊ: ሳሙኤል ታፈሰ ኃላፊ
    17.10. አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ኃላፊ: አዲስ አለነ ናቸው::

    © satenaw

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*