በስልጤ ዞን በወያኔ ኢህአዴግ አስተባባሪነት ሊደረግ የነበረው የኦሮሞ ፣ አማራ እና የኮንሶ ትግል ለመቃወም የሚደረግ ሰልፍ ተሰረዘ።
በስልጤ ዞን በሁሉም የወረዳ ከ 100 በላይ አባ ወራዎችን በመቀስቀስ በዋና ከተማዋ ወራቤ በወያኔ ኢህአዴግ አስተባባሪነት ሊደረግ የነበረው የኦሮሞ ፣ አማራ እና የኮንሶ ትግል ለመቃወም የሚደረግ ሰልፍ ተሰረዘ።
ለተከታታይ ቀናት እስከ ዛሬ ከጠዋት ድረስ ቅስቀሳ እየተደረገ የነበረ ሲሆን ሰልፉ በህብረተሰቡ እምቢተኝነት ምክንያት በድጋሚ ላልታወቀ ጊዜ ተራዝሟል በሚል ሰልፉ ተሰርዟል ። የስልጤ ዞን ምሁራን ፣ ወጣቶች ፣ አርሶ አደሮች እና አንዳንድ ሀገር ወዳድ አመራሮች ላደረጋችሁት ሁሉ ላቅ ያለ ክብር ይገባችኋል።
የህዝቡ ጉዳይ ያገባኛል የምትሉ ሁሉ ምስጋናችን ላቅ ያለ ነው። አሁንም ህዝቡ በተቻለው መጠን ከአማራ እና ከኦሮሞ ወገኖቹ ጎን መቆም አለበት! የነፃነት ጥያቄውን አንግቦ መነሳት አለበት ! ድል ለሰፊው ህዝብ !