በአዲስ አበባ የመምህራን እና የወያኔ ፍጥጫ እየተጋጋለ ነው ።

በአዲስ አበባ የመምህራን እና የወያኔ ፍጥጫ እየተጋጋለ ነው።

Minilik Salsawi – mereja.com በአዲስ አበባ የተጀመረው የመምሕራን ስልጠና ተብሎ በወያኔ ባለስልጣናትና ካድሬዎች የተጀመረው ስብሰባ በመድረኩ መሪዎችና በመምህራት መሃከል የተጀመረው ዝምታ እየጠበበ በንትርክና በፍጥጫ እየተጋጋለ መምጣቱን ተሳታፊ መምሕራን ተናግረዋል።

Image may contain: 2 people , crowd and text

በኣዲስ ኣበባ ዩንቨርስቲ ዛሬ ጠዋት በነበረው ስብሰባ ዶ፨ር አብርሃ በተባለ ግለሰብ ዕአንድ የኢኮኖሚ እና የፓለቲካ ማህበረሰብ መመስረትዕ በሚል ርዕስ አሰልቺ በሆነ የአቀራረብ ዘዬ ፕረሰንታቲኦን በመቅረብ ሂደት ላይ ስለ ትምክህተኝነት እና ጠባብነት ዙሪያ ማጠንጠን ሲጀምር ተሰብሳቢ ምሑራን በጭብጨባ ገለፃውን እንዲያቆም ጠየቁ፣ አቅራቢው ልጨርስ እያለ ቢለማመንም ጭብጨባው በመቀጠሉ ሳይጨርስ ለማቆም ተገዷል፥፥ መድረኩን የሚመራው ካሣ ተ፨ብርሃን ዕገለፃው እየተጠናቀቀ ነበር፣ ቸኮላችው፣እንዲያው ዝም ብላችው ነው ዓመላችሁን ያወጣችሁትና ከእናንተ የማይጠበቅ ነገር የፈፀማችሁትዕ በማለት በመናገሩ ምሑራኑ በከፍተኛ ጭብጨባ ተቃውሞአቸውን ደግመዋል።

በኣዲስ ኣበባ በተለያዩ ኣደራሾች እየተካሄደ በሚገኘው ስልጣና\ስብሰባ ላይ በስፋት የኦሮሚያ እና የኣማራ ክልል ጉዳዮችን መነጋገሪያ መሆናቸውም ለወያኔ ሰዎች በፍጹም ሊመቻቸው ኣልቻለም። የሕዝብን ጥያቄ በሻእቢያና በውጪ ሃይላት ላይ ኣትላኩ በማለት በሰሜን ኣዲስ ኣበባ ባለ ኣንድ ኣደራሽ የተነሳው ጥያቄ ኣንድ ሁለት ሲባል እስከ ዘለፋ ኣድጎ የወያኔ ሰዎች ለድብድብ ሲጋበዙ ተስተውሏል።እንደተለመደው የወልቃይት ጥያቄ በክልሎች ስምምነት ይፈታል በሚል ሊያዘናጉ ቢፈልጉም ፌዴራሉ በክልሎች ጉዳይ ኣይገባም በሚል ሽፋን ቢደረግም ሕዝቡን እየገደለ ያለው ግን የፌዴራሉ ጦር ነው ሲሉ ተችተዋል፥የትግራይ ክልል ጠባቦች የማራ ክልል ትምክተኛ ባለስልጣናት ችግር እየፈተሩ ነው የሚል ሰበብ የሚፈጥረው ማእከላዊ መንግስት ነው የሚገደለው ግን ጥያቄዬን መልሱ የሚለው ሕዝብ ነው ምን ኣይነት በዽብና የተሞላ ኣስተዳደር ጉዳዩን እንደሚመራው ያሳያል በማለት ወንጀለኛው የክልሉ ባለስልጣናት ሳይሆኑ የፌዴራል መንግስት ሰዎች ናቸው ሲሉ መምህራኑ በቁጣ ገልጸዋል።

የኮንሶ ሕዝብን በተመለከተ የተነሳው ጥያቄ የወያኔ ሰዎች በኪራይ ሰብሳቢዎችና በጫካ የመሸጉ ኣንጃዎች ናቸው በሚል ሊሸፋፍኑ ቢሞክሩም ነገሩ ከሮ ክርክር ቢያስነሳም ኣይናቸውን በጨ ኣጥበው ሲከራከሩ ተስተውሏል። የሕዝብን ጥያቄ ለማድበስበስ የምታደርጉት ጥያቄ ዋጋ ያስከፍላቹሃል ሲሉ መምህራኑ ኣጥብቀው ተናግረዋል። የሚዲያዎችን ጉዳይ በተመለከተ የመንግስት ሚዲያዎች የሚያስተላልፉት ሁሉ የሃሰት ፕሮፓጋንዳና እጅግ ርካሽ ሲሆን በዚህ ላይ ሕዝቡ ምንም ኣይነት የፖለቲካ ጉዳዮች ኣማራጭ እንዳያገኝ ለተቃዋሚ ድርጅቶችና ለሲቪክ ማህበራት ዝግ ነው ለሃገሪቱ የሚጠቅሙ ምሁራን ጋዜጠኞች ጦማሪያን ይታሰራሉ ይገደላሉ ይሰደዳሉ ይህ ሁሉላ የመንግስት ስራ ሲሆን ሕዝብ እየተራበ ከፍተኛ በጀት ተመድቦ ከተለያዩ ሃገራት ተቋሚዎች ይታፈናሉ የተለያዩ ኣፋኝ ሌክኖሎጂዎች ተገዝተው የሕዝብን መብት ለመርገጥ ይውላሉ ሲሉ በምሬት ተናግረዋል።

ወያኔ በማእከላዊ የሚፈጽመው ግፍ እና ሰቆቃ በመምህራኑ ተነስቶ ከፍተኛ የሆነ ጭቅጭቅ ፈጥሯል።በማእከላዊ የማሰቃያ ካምፕ ውስጥ መንግስት ከፍተና ወንጀል በዜጎች ላይ ይፈጽማል ያሉት መምህራን ታስረው የወጡትን ዜጎች አንድ በኣንድ ጠቅሰው ኣስቀምጠዋል። ስለ መምህራን የሙያ ፈቃድ ተነስቶ ወያኔ ላይ መምህራኑ ወርደዉበታል። የሙያ ፈቃድን በተመለከተ መምህሩን ለማታለልና ለማጨናነቅ ሆን ተብሎ የታቀደ የፖለቲካ ፊሽካ ሲሆን ወያኔ እኔ ኣውቅላቹዋለው የሚሉ ኣጉል ፈሊጥ በመምህራኑ ተቀባይነት እንዳሌለው ኣስረግጠው የተናገሩ ሲሆን ጠባብ ትምክህተኛ የሚለው የወያኔ ወንጀል የራሱ ስራ እንጂ የዜጎች ስራ ኣይደለም ሲሉ ገልጸዋል መምህራኑ።በኣንዳንድ ኣደራሾች መምህራን ሲሰላቹና ሲያንቀላፉ ተስተውሏል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ስልጠናውን ለመካፈል ከመንግስት ት/ቤት የሄዱ መምህራን በቀን ለአበል 150 ብር ለሻይ ቡና ደግሞ 20 ብር፣ በድምሩ 170 ብር እየተከፈላቸው ስልጠናውን በመውሰድ ላይ ናቸው::የግል ት/ቤት መምህራን ስልጠናው ከሙያቸው ጋር ፈፅሞ የማይገናኝ ከመሆኑም በላይ ለመንግስት ት/ቤቶች መምህራን የሚሰጠው የአበል ክፍያ የማይታሰብላቸው በመሆኑ ስልጠናውን አንካፈልም በማለት ጥለው ወጥተዋል ተብሏል፡፡ “ስልጠናው ባይኖርም ሥራ ላይ መሆናችሁ አይቀርም ነበር፡፡ ስለዚህም አበል ሊከፈላችሁ አይገባም” መባላቸውን የሚናገሩት መምህራኑ፤ ከሥራችን ጋር ፈፅሞ የማይገናኝ ስልጠና ለመውሰድ አዳራሽ ውስጥ ቁጭ ብለን ከምንውል መደበኛ ሥራችንን ብንጀምር ይሻለናል፡፡ ይህ ስልጠና ከመደበኛ ስራችን ውጪ በመሆኑ ተገቢውን የአበል ክፍያ ሊሰጠን ይገባል ብለዋል፡፡ በአንድ ህግና መንግስት በምትተዳደር አገር ላይ ሆነን አንድ አይነት ስልጠና ለመውሰድ እየተጠራን የግል ት/ቤት መምህራን በመሆናችሁ ስልጠናውን የምንሰጣችሁ ያለ አበል ክፍያ ነው መባሉ ህጋዊ ተግባር አይደለም” ሲሉም ተችተዋል፡፡

በስልጠናው ለመካፈል ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ገልፀው ከስልጠናው አዳራሽ ከወጡት መምህራን መካከል ያነጋገርናቸው ስማቸው እንዳይገለፅ የፈለጉ መምህር፤ “የስልጠናው ዋንኛ አጀንዳ ሆኖ የቀረበው የፌደራሊዝም ጉዳይ ከመምህርነት ሙያ ጋር ፈፅሞ የማይገናኝና ለመምህራኑ አቅም ግንባታም ሆነ ክህሎት ማሣደጊያ አንዳችም ፋይዳ የሌለው ፖለቲካ ነው፡፡ ለአመታት በመምህራኑ ውስጥ ሲነሳ የቆየውን የፈቃድ አሰጣጥ ጉዳይ አጀንዳ አድርገው ያቀረቡትም ይህንኑ ፓለቲካዊ ይዘት ያለውን የፌደራሊዝም ጉዳይ ለመሸፈን እንዲረዳ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡ስልጠናውን ለመካፈል ከመንግስት ት/ቤት የሄዱ መምህራን በቀን ለአበል 150 ብር ለሻይ ቡና ደግሞ 20 ብር፣ በድምሩ 170 ብር እየተከፈላቸው ስልጠናውን በመውሰድ ላይ ሲሆኑ በከተማዋ የሚገኙ አብዛኛዎቹ የግል ት/ቤት መምህራን ስልጠናውን ለመካፈል ፍቃደኛ ሳይሆኑ በመቅረታቸው ተበትነዋል፡፡ መምህራኑ ይህንኑ ጥያቄአቸውን በተደጋጋሚ ቢያቀርቡም ምላሽ አለማግኘታቸውንና በትናንትናው ዕለትም ተመሳሳይ ጥያቄ ያቀረቡ መምህራን ስልጠናውን ባለመካፈል ውሳኔያቸው የፀኑ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡#ምንሊክሳልሳዊ

12 Comments on “በአዲስ አበባ የመምህራን እና የወያኔ ፍጥጫ እየተጋጋለ ነው ።”

  1. የህዝብ ጥያቄ ስልጣን በአንድ አንስተኛ ጠባብ እጅ ስለወደቀ እኩል ተካፍለን አገራችን በጋራ እናስተዳድር ነው። የ 100 ሚሊዮን ህዝብ አገር በጥቂቶች መተዳደር ይብቃ። የአደራ መንግስት ሁሉንም ያካተተ ይቋቋም ነው ያለው ህዝቡ። ጥገና ሳይሆን ለውጥ። ሰው መቀያየር ሳይሆን የስርዐት ለውጥ። አባ ድላን አንስቶ ተሾመ ቶጋን መተካት ሳይሆን ምሁራንን የአገር ሽማግሌዎችን ተቃዋሚዎችን ያካተተ የአደራ መንግስት በአስቸኳይ ይቋቋም ነው ጥያቄው መልሱም እሱ ብቻ ነው። ወያኔ መሽቶብሃል ቶሎ ፍጠን ሳትበላ።

  2. በ2009 መምህራን እና ተማሪዎች የትግሉ ባለቤት ይሆናሉ

    የኦሮሞና የአማራ ተማሪዎች ጥንቃቄ አድርጉ በዙ ሸፍጥ አለና

  3. በባህርዳር ዩኒቨርስቲ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በመካሄድ ላይ ባለው የመምህራን ውይይት ወቅት የታሰሩት ወጣቶች እጣ ፋንታ እንዲነገራቸው መምህራን ዑኡታ ሲያቀርቡ፣ ስልጠና እየተሰጣቸው ነው የሚል ምላሽ በመሰጠቱ መምህራን ተቃውሞአቸውን ገልጸው ነበር።1 ሺ 500 በላይ ወጣቶች በቤንሻንጉል ጉሙዝ ጫካ ውስጥ ታስረው ስቃይ እየደረሰባቸው ቀኑን ሙሉ ድንጋይ በመፍለጥ እየተቀጡ መሆኑን፣ ብዙዎች በበሽታ፣ በርሃብ እና በህመም ህይወታቸው እያለፈ መሆኑን፣ በእስር ቤቱ ታስሮ ያመለጠ አንድ የቀድሞ ወታደር በ09/2016 ገልጿል።

    በአማራ ክልል የተካሄዱ ህዝባዊ ንቅናቄዎችን ተከትሎ ከታሰሩት ከ1 ሺ700 እስከ 2 ሺ የሚደረሱ ወጣቶች ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ በሚገኝ ጫካ ውስጥ ታስረው ቀኑን ሙሉ ድንጋይ በመፍለጥ እየተቀጡ መሆኑን፣ ብዙዎች በበሽታ፣ በርሃብ እና በህመም ህይወታቸው እያለፈ መሆኑን፣ በእስር ቤቱ ታስሮ ያመለጠ አንድ የቀድሞ ወታደር ገልጿል። በጠባቂ ጓደኞቹ ድጋፍ ያመለጠው ይህ የቀድሞ ወታደር፣ በወጣቶች ላይ የሚደርሰውን ስቃይ ከተመለከተ በሁዋላ፣ ስርዓቱን ማገልገሉ በእጅጉ ቆጭቶታል።ጠባቂ ወታደሮች ስለ እስረኞቹ ምንም እንደማያውቁ ፣ እርስ በርስ እንደማይነጋጋሩና ከውጭ ካለው ማህበረሰብ ጋር በፈጽሙ እንደማይገናኙ የገለጸው ወጣቱ፣ በውትድርና ውስጥ እያለ በሚያውቃቸው ሰዎች እርዳታ መጥፋቱንና ህይወቱን ማትረፉን ተናግሯል።እነዚህን እስረኞች ከሞት ለመታገድ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሊረባረብ እንደሚገባ ወጣቱ ገልጿል።

  4. Do you know when i begin to believe the government? When they allow opposition media to reach the public. Let the people hear left and right and decide. Allowing only one media to propagate government propoganda is a proof that the government is hiding something from the people. Go to neighbouring country like kenya there are hundreds of channels. Ethiopian government is really very backward in 21st century.

  5. It seems everything is moving in the right direction for Ethiopia and Ethiopians because now every single Ethiopian knows who Woyane is. Every Ethiopian knows now Woyane is liar, murderer, treacherous, terrorist, and criminal. Woyanes are completely hopeless and beyond any type of redemption. Woyane’s have already outlived their pathetic life and they must be made to disappear from our lives.

  6. ወያኒ የትግሪ ነጻ አውጭ ኢትዮፒያን ዶቃ አመድ ለማድረግ እኮ እንጂ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ያዘጋጀው እንደ ዩኒቨርስቲ ተማሪ የአገር ተረካቢ ተደርገው አልተማሩም ለአምሃራው ሊላ ታሪክ ለኦሮሞው ሊላ ታሪክ ለትግሪው ሊላ ታሪክ…….እየተነገረ በዩኒቨርስቲ በዘር ተከፋፍለው መች ስለ አገር ጉዳይ ያስባሉ እንደ ተማረ ሳይሆን እንደ እንሥሣ እየተባሉ ነው ያሉት ስለዚህ በተለይ አምሃራውን እና ኦሮሞውን ወራሪና ተወራሪ ጡት ቆራጭና ተቆራጭ በሚል ኦሮሞው የተማረው ታሪክ ከአምሃራው ጋር የማይገጥም ነው ኦሮሞው እንዲት አምሃራ ኦሮሞን እንደወረረ ሚሊሊክ ጡት እንደቆረጠ አታውቁም በማለት የሚጨቃጨቁ ብዙዎች ናቸው ለምን ቆረጠ ሲባሉ ክርስቲያን እያለ በማለት ሲመልሱ ክርስትና ታዲያ በኢትዮፒያ የመጣው የጀመረው በሚሊሊክ ዘመን አይደለም ኦሮሞ ከአምሃራጋር በኢትዮፒያ መኖር የጀመረውም በሚሊሊክ ዘመን አይደለም ስለዚህ የትኛው ታሪክ ነው በሚል ብዙዎች ይቃረናሉ እውነተኛ ታሪክ ከሆነ ታሪክ ታሪክ ነው ለምን የአንድ አገር ህዝቦች ውስጥ አገር ተረካቢዎች ከሆኑ የተለያየ ታሪክ ለምን ይነገራቸዋል እዚህ ላይ አምሃራና ኦሮሞ ብዙ ሲራ ስለተሰራባቸው መጠንቀቅ ያስፈልጋል እንደ እንሥሣ እንዳያስቡ እንደ ሰውና እንደ ሙሁር ማድረግ ጥሩነው በሪ ወለደ ታሪክ የሚያስተምራቸው እንደ እንሥሣ የሚያስቡ በማጋጨት ስለሆነ ህይወታቸው የሚረዝመው የተማረ ህዝብ በመወያየት እውነተኛ ተሪክን መሰረት በማድረግ መሆን አለበት

  7. ወያኔ በአማራ ከዘመተ ሰንትአለ ዘርን በማጥፋት መድሃኒት በመስጠት፣መርዝ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ አማራውን ሰገድለ አሁንም በኮንሶ የሚኖሩ ሃገራቸው የሆነው የአማራ ተወሊጅ በማሳደድና በመጨፍጨፍ በአተት (አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት) በወያኔ የተፈጠረና ብሎም በእንጀራው ውስጥ (ጀሶ፣ሰጋቱራ፣አፈር፣ዳቦ ውስጥም መርዝ በጨመር ብሎም ብጣሪ፣) በእያቀረቡበት በግድ አማራ በኢትዮጵያ ውስጥ መጥፋት አለበት ይህንም እንድሰራ የብአዴን ጽ/ቤት በገንዝብ በሆዳቸው ለወያኔ ያደሩ የባንዳ ልጆችን በማሰማራት
    አማራው ገድለው ወያኔ ሉበሇጽግ ስንት አማራዎችን ገደለ?
    አማር

  8. ሲጀመር መምህራኑ ለምን። ወደ ስብሰባው ይሄዳሉ ለዚያች 150 + 20 ለሻይ ለምትሰጠዋ ብር ነው? 170 ብሯ ሌላ የበለጠ ራስ ምታት ገዝቶ መምጣት እኮ ነው ትርፉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*