ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ከእሳትና ጥይት የተረፉት ታሳሪዎች በቂሊንጦ በእንግልትና ስቃይ ውስጥ ናቸው

ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ከእሳትና ጥይት የተረፉት ታሳሪዎች በቂሊንጦ በእንግልትና ስቃይ ውስጥ መሆናቸውን ለቢቢኤን ገለጹ

ቂሊንጦ በደረሰው የእሳትና የጥይት ተኩስ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ መንግስት ባመነው 23 ሰዎች እና ከዚያ በላይ መሞታቸው ይታወቃል፡፡ የተረፉት እስረኞች ወደ ተለያዩ እስር ቤቶች መላካቸው እና የተወሰኑት ደግሞ በቂሊንጦ ታስረው እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡

በአሁኑ ጊዜ በቂሊንጦ የተመደቡት እስረኞች በአንድ ክፍል ተዘግቶ እንደሚውሉ ና በቂ የጸሃይ ብርሃን እንኳን እያገኙ እንዳልሆነ ገልጸዋል፡፡ ለቤተሰብ ጥየቃ ከተፈቀደችው ትንሽ ደቂቃ ውጭ በአንድ ክፍል ተዘግቶባቸው እንደሚውሉና በማእከላዊ እንኳን ለጻሃይ ብርሃን በቀን የሚሰጠው ደቂቃዎች ለነሱ መነፈጉን የታሳሪ ቤተሰቦች አስረድተዋል፡፡

የቆዪ ብርድልብሶች እንዲሁም ክፍሎች ተዘግተው ስለሚውሉ አንዳንዶች የጤና መታወክ ጭምር እያጋጣማቸው መሆኑን እና ከፍተኛ ስጋት ውስጥ መውደቃቸውን ጠቁመዋል፡፡ ማህበረሰቡም የታሳሪዎች የየአያያዝ ሁኔታ እንዲስተካከል ግፊት እንዲያሳድር ሲሉ መልክታቸውን ልከዋል – ቢቢኤን መስከረም 7/2009

1 Comment on “ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ከእሳትና ጥይት የተረፉት ታሳሪዎች በቂሊንጦ በእንግልትና ስቃይ ውስጥ ናቸው”

  1. “ወያኔ የጥፋት ዘመን” የሚለው የሙሉቀን ተስፋው መጽሐፍ እንዳይሰራጭ ታገደ። ግን ለምን?
    “ወያኔ የጥፋት ዘመን” የሚለዉን የሙሉቀን ተስፋዉ መጽሀፍ በመላ ሀገሪቱ እንዳይሰራጭ እና እንዳይነበብ አግዳዋለች:: ግን ለምን?
    ህዉሀቶች እንዲህ አይነት መጽሀፍ ታትሞ ቢሰራጭ እንደሚያግዱት ገና ከጅምሩ ግምት ሳይሆን ጠንካራ ድምዳሜ ላይ ደርሼ ነበር:: ይሄም የሆነዉ በተለያዬ ወቅት ከበርካታ ወጣቶች ጋር በአማራ ህዝብ ላይ የተሰራዉን የዘር ማጥፋት ወንጀል በመጽሀፍ መልክ ስለማሳተም እየተወያዬን ስለነበረ እና ወያኔም መጽሀፉ ታትሞ ቢወጣ ሊያግደዉ እንደሚችል ሰፊ ትንታኔ ሰርተንበት ስለነበረ ነዉ::
    ታሪኩን ለማሳጠር በመሃል ሙሉቀንን ሳገኘዉ ትክክለኘዉን ስራ የሚሰራዉ ይሄ እሳት የላሰ ወጣት መሆኑን በመረዳቴ ሙሉቀንን ማበረታታትን መረጥሁ:: ሙሉቀንም በፍጥነት ስራዉን ማቀላጠፉን ያዘዉ::
    በጣም በተሳካ ሁኔታም ሞረሽ የጥናቱን ወጭ ሊሸፍን ሲነሳ: የመረጃ ምንጮቹ ኔትወርኮች ደግሞ ተያይዘዉ መፈሰስ ጀመሩ::በተለይም የመላዉ አማራ ህዝብ ድርጀት (መአህድ) እንዲሁም የመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ለብዙ አመታት የደከሙበት የአማራን ህዝብ ፍጅት በመረጃ እየመዘገቡ ያጠራቀሙት የመረጃ ቋት እንደ ኩል ዉሃ ኮለል እያለ ለመነሻነት እና ለመንደርደሪያነት ማገልገል ጀመረ:: በተጨማሪም የሰበአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች የሰበሰቧቸዉ መረጃዎች በአማራ ህዝብ ላይ የደረሰዉን ፍጅት ፍንትዉ አድርገዉ ማሳዬት ጀመሩ::
    ለሃያ አምስት አመታት በአማራ ህዝብ ላይ የዘር ፍጅት ሲፈጸም እና የአማራ ህዝብ ከአባቶቹ ሀገር ከኢትዮጵያ ምድር ያለ እዳዉ ሲሳደድ በርካታ ሚዲያዎች ምንነቱ ግልጽ ባልሆነ ምክንያት አፋቸዉን መለጎም ቢመርጡም ስለ እዉነት ሲሉ ግን ሳይታክቱ መረጃ ይይዙ የነበሩ ግለሰቦች: የፓርቲ አባላት: የፓርቲ አመራሮች : የፖለቲካ ድርጅቶች: የሰበአዊ መብት ተሟጋቾች: ተራ ዜጎች ግን ብዙ ነበሩ::
    እናም እነዚህ ሁሉ ሀይሎች ያጠራቀሙት መረጃ አንዴ ዉሉ ሲገኝ መተርተር ጀመረ::ሙሉቀን በወጣት ጉልበቱ ሳይደክም ወደ ማህበረሰቡ ዉስጥ ጠልቆ ገባ ::ጥናቱ አድካሚ ቢሆንም አመርቂ ስራም በፍጥነት መሰራት ቻለ:: ይሄ ጥናት በተሳካ ሁኔታ ተጠናቆ በመጽሀፍ መልክ ለህትመት መቅረቡ የሙሉቀንን ብርታ እና ትጋት የሚያረጋግጥ ነዉ::
    ከብዙ ወጣቶች ጋር ካለኝ ሰፊ ግንኙነት አንጽር ስገመግመዉ የሙሉቀን አንድ የተለዬ ተሰጥኦ ፈጥኖ ወደ ስራ መግባቱ እና አደጋዎችን ተጋፍጦ ለመስራት ፈቃደኛ መሆኑ ነዉ:: እንዲሁም በዚህ ጥናት ጀርባ ያሉት ሀይላት እና የመረጃ ምንጮች የጥናቱ ዋና የጥንካሬ ምንጭ ናቸዉ:: በጥናቱ ዉስጥ የተጠቀሱት መረጃዎች ማንንም የሚያፈናፍኑ አይደሉም:: ምክንያቱም ጥናቱ ከተጨባጭ ምንጮች እንዲሁም በአካል ጉዳቱ የደረሰባቸዉን በህይወት የተረፉ ተጠቂዎችን ሁሉ በማካተት የተሰራ ስለሆነ ነዉ::
    ከላይ እንደተቀስኩትም ወያኔዎችን እንዲህ አይነት ጥናት ሊያስደነግጣቸዉ ብቻ ሳይሆን ሊያፍኑት እንደሚችሉም ሰፊ ትንታኔ ሰርተንበት ነበር::ምክንያቱም ይሄ መጽሀፍ አንድ ሰፊ ቁጥር ያለዉን የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ለይተዉ እንዴት የዘር ማጥፋት ኢላማ እንዳደረጉት በጥልቀት
    ያጋልጣቸዋል እና ነዉ:: እናም መጽሀፉ እንዳይሰራጭ ሊያግዱት ቢነሱ ምንም የሚያስገርም ነገር አይኖርም::
    እኔ እንዳስተዋልኩት በርካት ኢትዮጵያዊ ስለ ወያኔ የዘር ማጥፋት ወንጀል በቂ መረጃ የለዉም::ወይም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ላይ የዘር ማጥፋት በኢትዮጵያ እየተደረገ ነዉ ሲባል ነገሩ ቀልድ የሚመስለዉ እና በጀርባዉ የተኛ ብዙ ዜጋ አለ:: የሙሉቀን መጽሀፍ እንግዲህ ይሄን ሁሉ በጀርባዉ ለጥ ያለ ህዝብ የሚያነቃ ነዉ:: ወያኔዎች ደግሞ የንቃተ ህሊናን ሚስጥር በደንብ ያዉቁታል::ህዝብ ንቃተ ህሊናዉ ከፍ ካለ ምን ሊያመጣ እንደሚችል በደንብ ያዉቃሉ::
    በእኔ አረዳድ ይሄ መጽሀፍ የአማራ ህዝብ ጉዳይ ብቻ አይደለም::በእኔ አረዳድ ይሄ መጽሀፍ የኢትዮጵያ ህዝብ ጉዳይ እና ታሪክ ነዉ::አማራ ህዝብ ላይ የደረሰ የዘር ማጥፋት ወንጀል ሁሉም ኢትዮጵያዊ ላይ የደረሰ የዘር ማጥፋት ወንጀል ነዉ ብዬ አምናለሁ::ስለዚህ ሁሉም ኢትዮጵያዊ መጽሀፉን ሲያነበዉ በጣም ልቡ እንደሚሰበር የሚያጠራጥር ነገር አይመስለኝም::ሌላዉ ቀርቶ ከወንጀል ህሊና ንጹህ የሆኑ የህዉሃት አባላት ይሄን መጽሀፍ ቢያነቡት አንድ ጥያቄ መጠዬቃቸዉ አይቀርም:: እንዲህ የሚል:- “ግን የአማራ ህዝብ ምን ስለ በደለን ነዉ ይሄን ሁሉ ወንጀል የፈጸምንበት?” ሲሉ::
    ይሄ መጽሀፍ ወደፊት በምትመሰረተዋ ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ዉስጥ እንዴት የየአንዳንዱ ዜጋ ህይወት እንዲሁም የየአንዳንዱ ማህበረሰብ ህልዉና በጥንቃቄ ሊጠበቅ እንደሚገባዉ ብዙ ትምህርት የሚሰጥ ስለሆነ ኢትዮጵያዉያን ሁሉ መጽሀፉን ታነቡት ዘንድ እጋብዛችኋለሁ:: በቀጣይም ሰፊ ምርምር ሊሰራበት የሚችል ዘርፍ ስለሆነ ምሁራን የመነሻ የመረጃ ምንጭ ልታደርጉት ትችላላችሁ::
    ለማኛዉም ወያኔ ከሰይጣናዊ ስህተቱ ዛሬም አይማርም::አማሮቹን ማንም አለም ሳይሰማ ሀያ አምስት አመት ሙሉ ከምድረ ገጽ ዘራቸዉን አጠፋቸዋለሁ ብሎ እንደዳከረዉ ሁሉ አሁን ደግሞ ስለአማሮቹ ጥፋት የሚያብራራዉን መጽሀፍ አፍኖ ከመሰራጨት ሊያስቀረዉ እየዳከረ ነዉ::
    ያላወቀዉ ነገር ግን ይሄ ትዉልድ በእዉቀት የታጠቀ እና የነቃ ነዉ:: ምንንም ነገር ማፈን አይቻልም:: እግዚአብሄርም ወንጀለኞችን የሚያጋልጡ እንደ ሙሉቀን አይነት ብላቴናዎችን ከትዉልዱ መሃከል አብዝቶ ማስነሳቱን አይተዉም::
    በእዉነቱ ነገሮችን በደንብ ቀረብ ብሎ ለመረመረ እና ላስተዋለ በኢትዮጵያ ምድር የክፋት : የዘረኝነት እና የልዩነት ምንጭ ወያኔ ብቻ ነዉ:: እናም የልዩነት መንፈስን የሚያራግበዉ እርኩስ መንፈስ ይቃጠል ዘንድ የእግዚአብሄር ፈቃዱ ይሆን ዘንድ የዘወትር ጸሎቴ ነዉ::

    ኢትዮጵያንም እግዚአብሄር ይባርካት ! በፍቅር መንፈስም ህዝቧን ይጎብኘዉ !

    September 17,

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*