የለውጥ ማዕበል ገፈት ቀማሽ ሳንሆን፣ ተቋዳሽ ለመሆን፣… የመፍትሄው ጅምር ይሄውና! ( ዮሃንስ ሰ. )

አምናና ዘንድሮ፣ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ይበልጥ እየተጋጋለ፣ እየተበላሸና አስፈሪ እየሆነ የመጣው፣ በአጋጣሚ ይመስላችኋል? በየአገሩኮ፣ ተመሳሳይ ትዕይንቶችን እያየን ነው። ግራ እየተጋባን፣ እውነታውን በግልፅ ለማየት ፈርተን፣ ራሳችንን ለማታለል ካልፈለግን በቀር፣ የፖለቲካ ማዕበሉ፣ የአጋጣሚ ጉዳይ አይደለም። አስፈሪነቱ ደግሞ፣ ጭራና ቀንዱ አልያዝ ብሎ፣ ጨርሶ መፍትሄ የሌለው መምሰሉ ነው። ነገሮች ሁሉ ሲምታቱብንና የመፍትሄ ጭላንጭል ሲጠፋብን፣ አብዛኞቻችን፣ ከጭንቀት ለመገላገል፣ አይናችንን እንጨፍናለን። በሰበብ በማመኻኛ፣ ራሳችንን እናታልላለን። የመንግስት ደጋፊም ሆነ ተቃዋሚ፣ ብዙም ልዩነት የለውም። ከእውነታው ለመሸሽ ይሽቀዳደማሉ – አለማቀፋዊው ማዕበል እኛን የማይመለከት ለማስመሰል።
ማዕበሉ የኢትዮጵያ መንግስትን አይነካካም? ማዕበሉ የኢትዮጵያ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎችን አይመለከትም? ብዙዎቹ የመንግስት ደጋፊዎች፣ ይህንን ማሰብ አይፈልጉም። ከግብፅ የሆስኒ ሙባረክ መንግስት፣ ከየመን፣ ከቱኒዚያና ከሌሎች የማዕበሉ ገፈት ቀማሽ መንግስታት ጋር እንዳይመሳሰልባቸው ይፈራሉ። በጥንቃቄ ማሰብ፣ አመፅን እንደማባባስ የሚቆጥሩም አሉ። ብዙዎቹ ተቃዋሚዎችስ? ብዙዎቹ፣ ሊያስቡበት አይፈልጉም። ከግብፅ፣ ከየመን፣ ከቱኒዚያና ከሌሎች አገራት አስፈሪ የትርምስ ማዕበል ጋር እንዳይመሳሰልባቸው ይፈራሉ። እንዲያውም፣ በጥንቃቄ ማሰብ፣ ተቃውሞን እንደማዳከም የሚቆጥሩ አሉ።
ደጋፊዎችና ተቃዋሚዎች፣ በአብዛኛው እንዲህ ከእውነታ መሸሻቸውና ላለማሰብ መንገታገታቸው፣ ትርጉሙ ምንድነው? ያው… አይንን ጨፍኖ እንደ መጠበቅ ወይም አይንን ጨፍኖ እንደ መሮጥ ነው – “የሚሆነውን ነገር እናያለን… ከሆነ በኋላ” እንደማለት።
አንዳንዱ፣ “በአንዳች ተአምር፣ ከማዕበሉ እናመልጥ ይሆናል” ብሎ ይመኛል – ነገር እንዳይደፈርስ በመመኘት። አንዳንዱ ደግሞ፣ “ደፍርሶ አይቀርም፤ በማግስቱ በአንዳች ተዓምር፣ ነገሩ ሁሉ እየጠራ መልክ ይይዝ ይሆናል” ብሎ ይመኛል። በደፈናው ከመመኘት በቀር፣ እውነታውን በጥንቃቄ አስተውሎ፣ የማዕበሉን ምንነት አገናዝቦ፣ የሚያዛልቅ መፍትሄ ለማበጀት፣ አብጠርጥሮና አንጥሮ የሚያስብ ሰው ሲጠፋ፣ ‘አደጋ አለው’።
አብዛኛው ሰው፣ የአገሬው አዝማሚያ አልጥም እያለው፣ በዝምታና በስጋት መሃል ይወዛወዛል – በማዕበሉ እየተንሸራተተ። አብዛኛው “ንቁ ተሳታፊ” ደግሞ፣ በእያንዳንዷ ቁንፅል ወሬ የእለት የእለቷ የብሽሽቅ ጨዋታ ላይ ‘እየተመሰጠ’ ይደናበራል – ወጀቡን እያባባሰ። እንዲያም ሆኖ፣ የብዙዎቹ የጋራ ምኞት ምንድነው? በቃ፣ “በአንዳች ተዓምር ሁሉም ነገር ሰላም ይሆናል” እያሉ፣ በድፍን ምኞት ራሳቸውን ያታልላሉ። እና… ሌሎች በርካታ አገራት፣ ሰላም ያጡት፣ በእርግማን ነው? እዚህም እዚያም ትርምስ የሚፈጠረው፣… እንዲሁ በአጋጣሚ ነው?
የማዕበል ተቋዳሽ – ‘በአጋጣሚ’
ዛሬ፣ በጥቂት አመታት ውስጥ፣ ብዙ አገራት በየተራ የማዕበል ገፈት ቀማሽ ለመሆን እየተዳረጉ የሚገኙት፣ በአጋጣሚ ከሆነ፣ ያስገርማል።
አሃ፣ ከሃምሳ ዓመት በፊት፣ ከ30 በላይ የአፍሪካ አገራት፣ በጥቂት አመታት ውስጥ፣ ተራ በተራ ከቅኝ ግዛት የተላቀቁትም፣ በአጋጣሚ በግጥምጥሞሽ ነዋ። ደግሞም፣ ከቅኝ ግዛት መላቀቅ ብቻ አይደለም። ከዛምቢያ እስከ ኬንያ፣ ከካሜሩን እስከ ማዳጋስካር፣ ከሞሪታኒያ እስከ ሶማሊያ፣ ከሴኔጋል እስከ ብሩንዲ… በአብዛኞቹ የአፍሪካ አገራት፣ በዚያን ወቅት፣ ከ50 ዓመት በፊት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች እየተፎካከሩ በርካታ ምርጫዎች ተካሂደዋል። የአፍሪካ አገራት … ታሪክ፣ በጥቂት አመታት ውስጥ … በየተራ ተቀየረ። ከቅኝ ግዛት የወጡ አገራት፣ ከ25 በላይ የአፍሪካ አገራት፣ በአራት አመታት ውስጥ፣ የመድብለ ፓርቲ ስርዓትን በመፍጠር፣ በተመሳሳይ ጊዜ፣ ተመሳሳይ ታሪክ ሰሩ።  “የአጋጣሚ ነገር”!
የማዕበል ገፈት ቀማሽ – ‘በአጋጣሚ’
ከ1950 እስከ 1955 ዓ.ም ድረስ፣ በአብዛኛው እንደ መልካም ጅምር የታየው የለውጥ ማዕበል፣ በዚያው አልዘለቀም። ብዙ ሳይቆይ፣ እንደገና በሌላ ማዕበል ተተክቷል።
አብዛኞቹ የአፍሪካ አገራት…. ከአራት አገራት በስተቀር ሌሎቹ ሁሉ፣… (ማለትም፣ ‘እንደ አጋጣሚ’ ከ40 በላይ የአፍሪካ አገራት ውስጥ)፣ በተመሳሳይ ጊዜ፣ ሃሳባቸውን በተመሳሳይ መንገድ ቀየሩ። የፖለቲካ ፓርቲዎች ፉክክር ወንጀል ነው ብለው ወሰኑ። የአንድ ፓርቲ አገዛዝን አወጁ። እንደ ደርግ፣ የሶሻሊዝም ስርዓት መስርተናል በማለት በኩራት፣ አምባገነንነትን ያወጁ መንግስታት ብዙ ናቸው – ከ30 በላይ የአፍሪካ መንግስታት – ከሊቢያ እስከ አንጎላ፣ ከሲሸልስ እስከ ሴራሊዮን፣ ከአልጄሪያ እስከ ኢትዮጵያ፣ ከኮንጎ እስከ ሶማሊያ… በሶሻሊዝም ማዕበል ተጥለቀለቁ። ለዚያውም፣ ይሄ ሁሉ የሆነው አስር ዓመት በማይሞላ ጊዜ ውስጥ ነው! ይሄም ግጥምጥሞሽ ነው?
በ1960ዎቹ ዓ.ም፣… ገዢ ፓርቲና መንግስት ብቻ አልነበሩም፣ ሶሻሊዝምን ያራገቡት። እንደ ኢህአፓ እና እንደ ኢህአዴግ የመሳሰሉ፣ ብዙዎቹ የአፍሪካ ተቃዋሚዎችና ተዋጊዎችም፣ ‘እንደ አጋጣሚ’፣ ያው… ሶሻሊስቶች ነበሩ። ምን ይሄ ብቻ።
ሌላ የሲሳይ ማዕበል  “በአጋጣሚ”
በ1982 ዓ.ም፣ መንግስት አዲስ ነገር ይዞ መጣ። ሶሻሊስት ያልሆነ ፓርቲ እመሰርታለሁ አለ። መንግስት የሰዎችን ንብረት እየወረሰ፣ ኢኮኖሚውን ሙሉ ለሙሉ ለመቆጣጠር በኩራት ዘመቻ ሲያካሂድ እንዳልነበረ፤ ‘ድንገት’ ተነስቶ፣ የግል ቢዝነስ እንዲስፋፋ እፈቅዳለሁ በማለት አወጀ – “ቅይጥ ኢኮኖሚ”፣ “ገበያ ቀመስ ኢኮኖሚ” የሚል አባባል በረከተ።
በዚያው አመት፣ ኢህአዴግም በረሃ ውስጥ፣ “ለጊዜው ሶሻሊዝምን ለቀቅ አድርጌለሁ” የሚል መግለጫ አሰራጨ። ቅይጥ ኢኮኖሚን እንደሚፈቅድም ገለፀ። “የአንድ ሶሻሊስት ፓርቲ አገዛዝ” የሚል ሃሳቡንም በመቀየር፣ ብዙ ፓርቲዎች የሚሳተፉበት ስርዓትን እመሰርታለሁ አለ።
ደርግ እና ኢህአዴግ ምን ነክቷቸው ነው፣ ድንገት በተመሳሳይ ጊዜ፣ በተመሳሳይ መንገድ ሃሳባቸውን የቀየሩት? ታዲያ፣ ሃሳባቸውን የቀየሩት የአገራችን ፓርቲዎች ብቻ አይደሉም። የአንድ ፓርቲ አገዛዝ ወይም የሶሻሊዝም አምባገነንነት ሰፍኖባቸው የነበሩ ብዙ የአፍሪካ አገራት ውስጥ፣ ‘ድንገት’ ተመሳሳይ ለውጥ የተከሰተው፣ በዚያን ጊዜ ነው – ከ1982 እስከ 1986 ዓ.ም።
ሲኮሩበት የነበረውን የአንድ ፓርቲ አገዛዝ ትተው፣ ብዙ ፓርቲዎች የሚሳተፉበት ስርዓት ለመመስረት ወሰኑ።
ማዕበሉ በቃ፣ አህጉሪቱን አጥለቀለቀ፡፡ በአራት ዓመታት ውስጥ፣ በ34 የአፍሪካ አገራት፣ በየተራ አዳዲስ የህገመንግስት አዋጆች ተዘጋጅተው ፀድቀዋል። “ተቃዋሚ ፓርቲዎች እንዲቋቋሙ” ለመፍቀድ የህገመንግስት ማሻሻያዎች ታውጀዋል። ይሄም ግጥምጥሞሽ ነው? ከአልጀሪያ እስከ አንጎላ፣ ከቤኒን እስከ ጂቡቲ፣ ከጋና እስከ ታንዛኒያ፣ ከኒጀር እስከ ሞዛምቢክ… በሁሉም አቅጣጫ፣ የምድረ አፍሪካ የፖለቲካ መነጋገሪያዎች ተቀየሩ – “መድብለ ፓርቲ” እና “የገበያ ኢኮኖሚ” የሚሉ ርዕሶች ነገሱ። ኢትዮጵያም የዚሁ አዲስ የሲሳይ ማዕበል ተቋዳሽ ነበረች። ‘የአጋጣሚ ነገር’!
የአጋጣሚ ጉዳይ አይደለም – ራሳችንን አናታልል
የዛሬ 50 ዓመት፣… እዚህም እዚያም፣ የሶሻሊዝምና የአንድ ፓርቲ አገዛዝ በየአገሩ ታወጀ። መንግስታት የየአገራቸውን ኢኮኖሚ ተቆጣጠሩ። የግል ንብረትና ቢዝነስ ተወገዘ። በጥቂት አመታት ውስጥ፣ ከ30 በላይ የአህጉሪቱ አገራት፣ የማዕበሉ ገፈት ቀማሽ ሆነዋል – ኢትዮጵያም አላመለጠችም።
የዛሬ 25 ዓመት ደግሞ፣ እዚህም እዚያም፣ በየአገሩ ብዙ ፓርቲዎችን የሚያስተናግድ ‘ዲሞክራሲ’፣ ቢዝነስ እንዲስፋፋ የሚፈቅድ ‘የገበያ ኢኮኖሚ’… የሚሉ አዋጆች ተበራከቱ። በአራት አመታት ውስጥ፣ ከ30 በላይ አገራት የማዕበሉ ተቋዳሽ ሆነዋል – ኢትዮጵያም ጭምር።
እነዚህ ሁሉ፣ ‘የግጥምጥሞሽ ጉዳይ ናቸው’ የምንል ከሆነ፤ ራሳችንን እስከ ወዲያኛው ድረስ ለማታለል ቆርጠናል ማለት ነው – አይናችንን ጨፍነን ለመቀመጥ፤ ለመሮጥ መርጠናል ማለት።
ይሄውና ዛሬም ሌላ ‘ግጥምጥሞሽ’ እያየን ነው – አዲስ የፖለቲካ ማዕበል በየአገሩ ሲያስገመግምና ሲገለባበጥ እየተመለከትን ነው። ካሁን በፊት እንዳየነው፣ ኢትዮጵያም የግጥምጥሞሹ ተቋዳሽ ወይም ገፈት ቀማሽ መሆኗ ይቀራል?…
ታዲያ፣ ቢያንስ ካሁን በኋላ፣ “ነገሩ ሁሉ የአጋጣሚ ነገር ነው” እያልን ራሳችንን ማታለል አይበቃንም?
ነገርዬው የግጥምጥሞሽ ጉዳይ አይደለም። ዋና ዋና ሃሳቦች፣ የፖለቲካ ሃሳቦችም ጭምር፣ ንብረትን የሚያራቁትና የአንድ ፓርቲ አገዛዝን የሚያስፋፋ ሶሻሊዝም፣ አልያም ነፃ የገበያ ስርዓትን የሚያስፋፋ ‘የመድብለ ፓርቲ’ ሊበራሊዝም፣ እና ሌሎች ሃሳቦች፣ ድንበር የለሽ ናቸው። አንደኛው ወይም ሌላኛው ሃሳብ፣ በአንድ አገር ውስጥ ብቻ ተስፋፍቶ አይቆምም። የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ፣ ወደ ሌሎች አገራትም መዛመቱ አይቀርም። ይሄ የአጋጣሚ ጉዳይ አይደለም። የሰው ዋነኛ ልዩ ተፈጥሮ፣ ማሰብ የሚችል መሆኑ ነውና። እናም፣ አለማቀፋዊ የሃሳብ ለውጥ፣ የለውጥ ማዕበል አንዱ መንስኤ ነው።
ሁለተኛው መንስኤ ደግሞ፣ በአብዛኛው አገር፣ በአብዛኛው ጊዜ፣ ብዙ የኑሮ ቅሬታዎች፣ እሮሮዎችና ተቃውሞዎች መኖራቸው ነው። ከኑሮ ቅሬታና እሮሮ ጋር ደግሞ፣ በደፈናው ለውጥን የመመኘት ስሜት አብሮ ይኖራል። አቤቱታ ማቅረብና ተቃውሞ ማሰማትም እንዲሁ።
በ1960ዎቹ ዓ.ም፣ እንደሌላው ጊዜ፣ በየአገሩ በኑሮ ችግር የተማረሩ ብዙ ሰዎች መኖራቸውና በየአገሩ የተቃውሞ ሰልፎች መበራከታቸው አይገርምም – ለውጥን በመመኘት። ነገር ግን፣ በደፈናው ‘ለውጥ’ን መመኘት፣ መልካም ለውጥን ያስገኛል ማለት አይደለም።
መልካም ለውጥን የሚያስገኝ፣ ትክክለኛ አስተሳሰብን ማዳበርና፣ ጠቃሚ የመፍትሄ ሃሳብን መያዝ ያስፈልጋል። ግን ያኔ ምን ዋጋ አለው? አለምን፣ ከዚያም አፍሪካን አጥለቅልቆ የነበረው የአእምሮ ማዕበል፣ በአብዛኛው በጭፍን የሶሻሊዝም አስተሳሰብና፣ በመጥፎ የሶሻሊዝም ሃሳብ የተሞላ ማዕበል ነው። በዚህም ምክንያት፣ የያኔው የለውጥ ማዕበል፣ የአፍሪካ አገራትን ወደ ባሰ ቀውስ የሚያስገባ ክፉ ማዕበል ሆኖ አረፈው የአፈና፣ የድህነት፣ የግድያ ማዕበል። በ1980ዎቹ ዓ.ምም እንዲሁ፣ የኑሮ ችግሮች ሰማይ ደርሰው ነበር – በየአገሩ፣ የተቃውሞ ድምፆች የተበራከቱበት። ደግነቱ፣ በዚያ ወቅት፣ አለምንና አፍሪካን እያጥለቀለቀ የነበረ አዲስ የአእምሮ ማዕበል፣ በአመዛኙ ፈካ ያለ የሊበራሊዝም አስተሳሰብና፣ ከዚሁ የሚመነጩ ጥሩ ሃሳቦችን የያዘ ማዕበል ነው። በዚህም ምክንያት፣ በርካታ የአፍሪካ አገራት፣ የዚሁ ቅዱስ ማዕበል ተቋዳሽ ሆነዋል።
ታዲያ፣ በየጊዜው የተለያዩ የለውጥ ማዕበሎች ሲፈጠሩ፣ ገፈት ቀማሽ ከመሆን ማምለጥ አይቻልም፤ ወይም ተቋዳሽ ሳንሆን ሊያመልጠን አይችልም ማለት አይደለም።
የአፍሪካ አገራትን የሚያሰቃይ፣ የአንድ ፓርቲ የሶሻሊዝም አገዛዝ፣ በ1960ዎቹ በየአቅጣጫው እንደ ማዕበል ብዙዎችን ቢያጥለቀልቅም፣ በአስተዋይነትና በፅናት፣ “የተሻለ መፍትሄ” ለማበጀት የሞከሩ አገራት አሉ። አዎ ጥቂት ናቸው። ግን፣ ተሳክቶላቸዋል – ሞሮኮ፣ ሞሪሸስ፣ ቦትስዋና።
ለአፍሪካ አገራት የመሻሻል እድል የሚሰጥ ሌላ የለውጥ ማዕበል በ1980ዎቹ ዓ.ም ሲፈጠርም፣ ብዙ አገራትን ቢያዳርስም፣ በዚሁ እድል በፍጥነት ለመጠቀምና ውጤታማ ለመሆን ከመጣር ይልቅ፣ ከለውጥ ለመሸሽ ሲንገታገቱ ወይም በዘፈቀደ ሲደናበሩ፣ ፈጠነም ዘገየም፣ ለብጥብጥና ለእልቂት የተዳረጉ አገራት አሉ – እነ ኮንጎ ወዲያውኑ፣ እነ ሊቢያ ደግሞ የኋላ ኋላ ለጥፋት ተዳርገዋል።
ምን ለማለት ፈልጌ ነው?
በ1960ዎቹ ዓ.ም፣ የወቅቱ የኢትዮጵያ መንግስት፣ የአለምን ሁኔታ አገናዝቦና የአገሬውን ችግር አስተውሎ፣ በአንድ በኩል ክፉ የሶሻሊዝም ማዕበልን ለመቋቋም የሚያስችል፣ በሌላ በኩል ደግሞ የኑሮ ችግርን የሚያቃልል፣ ትክክለኛና ጠቃሚ የመፍትሄ ሃሳብ ቢያበጅ ኖሮ… ብላችሁ አስቡ። ኢትዮጵያውያን ከብዙ ስቃይ ይድኑ ነበር። ሰላሳ ዓመታት በከንቱ አይባክኑም ነበር። በኑሮ፣ አሁን ካለንበት ደረጃ፣ አስር እጥፍ ከፍ ለማለት የሚያስችል የለውጥ እድል በተገኘ ነበር።
በ1980ዎቹ ዓ.ም ደግሞ፣ ዘረኝነትና የብሄር ብሄረሰብ ተወላጅነት የፖለቲካ መቆመሪያ እንዳይሆን የሚረዳ፣ የኑሮ ችግርን ለማቃለል ብቻ ሳይሆን ለወደፊትም ለብልፅግና የሚበጅ፣ በአጠቃላይ ለስልጣኔ የሚያግዝ የፖለቲካ ማዕበል በአለማቀፍ ደረጃ እየተስፋፋ መቆየቱን ቀደም ብሎ መገንዘብ ቢቻል ኖሮና፣ እንደ ታይዋንና እንደ ደቡብ ኮሪያ ባንፈጥን እንኳ፣ የቻይናን ለውጥ በማየት ከ1970ዎቹ አጋማሽ ጀምሮ፣ ወደ ገበያ ኢኮኖሚ፣ ከዚያም ወደ ሊበራል ዲሞክራሲ የለውጥ እንቅስቃሴ ማድረግ ቢቻል ኖሮ ብላችሁ አስቡት። ኢትዮጵያውያን በስንትና ስንት እጥፍ የመሻሻል ድንቅ የለውጥ እድል ባገኙ ነበር።
እነዚህ ሁሉ፣ ተመልሰው የማይለወጡ፣ የድሮ ታሪኮች ናቸው። ነገር ግን፣ ዛሬና ነፈ የለውጥ ማዕበሎችን ሲከሰት፣ በጭፍን ተደብቆ ከመጠበቅ ወይም በጭፍን ከመንደርደር ይልቅ፣ እያንዳንዱን ማዕበል በማገናዘብ፣ የአገሬውንም የኑሮ ችግር በማስተዋል፣ እያንዳንዱን ለውጥ፣ መልካም ለውጥ እንዲሆን የማድረግ ምርጫ አለን።
አዎ የምርጫ ጉዳይ ነው። የማሰብ እና ያለማሰብ፣ መፍትሄ የማበጀትና የመሸሽ ወይም በዘፈቀደ የመደናበር ምርጫ ነው። ይሄ ነው፣ የመፍትሄው ጅምር! ማስተዋል፣ ማገናዘብና ማሰብ መጀመር፣ መፍትሄ ማበጀት እንደሚያስፈልግ ማወቅና ራሳችንን ሳናታልል በቅንነት መመርመር፣ በትጋት ማሰብ!

6 Comments on “የለውጥ ማዕበል ገፈት ቀማሽ ሳንሆን፣ ተቋዳሽ ለመሆን፣… የመፍትሄው ጅምር ይሄውና! ( ዮሃንስ ሰ. )”

  1. We have two questions that need to be answered to solve the problem.
    1) Equality for all the peoples, and power should be delivered to the Ethiopian people, and no more TPLF Rulling.
    2) It is required to stop dividing the people ethnically, and use geographic similarities and economic similarities. It is required to respect individual rights and to stop grabbing their property such as land and others. And to stop socialistic full to take individual property.
    If the current Rulling party is willing to do such things, they will save themselves from further problem, and they save the people from the things that may happen. At the eleventh hour, they have still the chance, but 2009 EC is the last year. Time to think.

  2. There is however, no historical parallel between Woyane Tigre regime and any country, anywhere in the World. I have yet to find a single country in the world that has ever been ruled by traitors and mercenaries.There is not a single example of a Woyane-like government in the world. Woyanes helped Eritrea break away. They also gave a large swathe of Ethiopian land to the Sudan. Where on earth has similar acts of high treason committed except in Ethiopia. Where on earth are such traitors allowed to seize state power and continue with their unfinished business of destroying a country?

    Woyanes are beyond redemption. Their acts of treason aside, they have committed a spate of genocides across the nation sometimes by proxy. They have virtually disenfranchised the entire non-Tigrean population of 95% for a quarter of a century.
    These unlettered and moronic outfit have done untold and unspeakable crimes against Ethiopia and its people. We should not brook Woyanes for a day longer if we can. Bringing them to justice, is the first step in taking ownership of our country.

  3. የአማራን ህዝብ በጠላትነት ሲፈርጁና ለማጥፋትም ሲወስኑ ስለአማራ ህዝብ ታላቅነትና ሀያልነት ግን አንዳችም እውቅና አልነበራቸውም፣ ዛሬም የላቸውም፡፡ ከአማራ፣ ኦሮሞ፣ ጉራጌ፣ ሀድያ፣ ከምባታ፣ ሲዳማ፣ እፋር፣ ወላይታና ከሌሎችም ህዝቦች ጋር ግን የሚያገናኛቸው ምንም እንደሌለ ለዘመናት በተግባር የሚያሳዩ ናቸው፡፡ የኢትዮጲያ ህዝብ ከውጪ ጠላት ጋር ሲዋጋ የኖረ እኮ በነሱ ምክንያት ነው፡፡ ተራ ሽፍታ የነበር ዮሀንስ ከእንግሊዝ ጋር በመሆን ነው እነሱን እየመራ አምጥቶ አፄ ቲዎድሮስን አስገድሎ፣ በሺህ የሚቆጠር ኢትዮጲያዊንን አሰውቶ፣ ከታሪከ ጀምሮ የተጠራቀመን የሀገርን ቅርስና ንብረት አዘርፎና መቅደላን ለሶስት ሳምንታት ያህል በእሳት አጋይቶ ለዚህ ውለታው ምላሽ የሚሆን እንግሊዞች ንጉስ ያደረጉት፡፡ ንግስናውም ከ1881 እስከ 1889 ለ8 አመት ብቻ ነው፡፡

    ወያኔንም ከትግራይ ተራራ ጀምረው ሲረዱ ኖረው ከስልጣን ላይ ያወጧቸውና እስከአሁኗ ደቂቃ ድረስ አየረዷቸው ያሉ እንግሊዞችች ሲሆኑ በወያኔ ዘር ማጠፋት ተግባር ላይም በእርዳ ሰጪ፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ በጎ እድራጊት፣ የተባበሩት መንግስታትና ሌላም በሚል ስያሜ በተለይም እንግሊዝና አሜሪካ ከወያኔ ጋር ምስጢራዊ ግንኙነት ፈጥረው በጋራ የሰሩት ወንጀል ነው፡፡ ጣሊያን ኢትዮጲያን በወረረ ጊዜ ባንዳዎችና ለዚያ ሁሉ ሰቆቃ ቅድሚያ ፈፃሚዎች የነዚህ የትግሬ ወያኔዎች አባቶችና አያቶች ናቸው፡፡ ከተራ ሽፍታነት አንስቶ እንግሊዝ ለ8 አመት ብቻ ንጉስ ያደረገችው የባንዳ የአፄ ዮሀንስ የልጅ ልጅም ነበር ጣሊያኖችን እየመራ አዲስ አበባ ያደረሳቸው፡፡ ዘረ ባንዳ ምን ጊዜም ባንዳ ይባልል ይህ ነው፡፡

    ከዚያም በፊት በእነዚህ ትግሬዎች ማለትም የየመን ባሪያዎች አማካኝነት ነው የውጪ ሀይል ቦታና እርዳታ እያገኜ ኢትዮጲያ ስትወረርና አማራ፣ ኦሮሞ፣ ጉራጌ፣ ሀድያ፣ ከምባታ፣ ሲዳማ፣ ወላይታ፣ አፋርና ሁሉም ዜጋ በጋራ አድዋንና ማይጨውን ጨምሮ የጋራን ጠላት በጋራ ሲያሰወጣና ወደር የሌለው መስዋዕት በነሱ ምክንያት ሲከፍል የኖረ፡፡ በደርግ ዘመን በነዚህ ባንዳዎቸ ምክንያት ስንት ዜጋ እንዳለቀ፣ ንብረት እንደወደመና ኢኮኖሚው እንደደቀቀ የሚታወቅ ነው፡፡ የሚገርመው ግን እንደነዚህ አይነት የሀገር ጠላቶች ስልጣል መያዝ ብቻ ሳይሆን በጥፋት ለመቀጠል ያመቻቸው ዘንድ አንድ ሆኖ የኖረን ህዝብ በተለያየ መንገድ ለመከፋፈልና ለማጋጨት መሞከርና ለጊዜውም ቢሆን ሊሳካላቸው መቻል ነው፡፡

    ከሌላ አፍሪካ ጋር ሲነፃፀር ኢትዮጲያ ብዙ ህዝብ ያላት ነገር ግን ጥቂት ብሄረሰቦች ያሏት ነች፡፡ ሱዳን 35 ሚሊዮን ህዝብ ሲሆን 407 ብሄረሰብ ያለው ነው፡፡ ኬንያ 72፣ ኡጋንዳ 62፣ ትንሿ ኤርትራ 9፣ ታንዛኒያ 130፣ ሞዛምቢክ 120፣ ዲ ኮጆንጎ 708፣ ናይጀሪያ 550፣ ካሜሩን 250፣ ግሀና 103፣ ግብፅ የተለያዩ ኑቢያንና ቤጃ ብሄረሰቦች፣ በርበር፣ በጣም ብዙ የሆኑ ብሄሮችና የሰው ዘሮች ቱርክን ጨምሮ ከመላው መካከለኛው ምስራቅ የመጡና በአጠቃላይ በመላው አለም በሚገኙ ሀገሮች ብዙ ቁጥር ያለው ብሄረሰብና የሰው ዘር በየሀገራቱ ይገኛል፡፡ በኢንዶነዚያ 1700 በሄረሰቦችና ሁሉም የሰው ዘር ይገኛል፡፡ ትንሽ የሆነች ፊሊፒንስ ከ120 ብሄረሰቦች በላይና የተለያዩ የሰው ዘሮች ይገኛሉ፡፡ በአውሮፓና በአሜሪካ ከተሞች የሚታየው ህዝብ ሁሉንም የሰው ዘርና ብሄረሰብ የሚወክል ሲሆን ቋንቋ ሌላ ሳይሆን መግባቢያ መሳሪያ እንደመሆኑ መጠን በአንድ ቋንቋ እየተግባባ በሰላም ይኖራል፡፡

    ከኛ ጋ ያሉት የየመን ባሪያ ዲያብሎሰ ትግረዎች ግን 99.9 በመቶ የሚሆነውን አንድነታችንንና ተመሳሳይነታችንን ለማጥፋት ሲሉ 0.1 በመቶ በሚሆን ልዩነት ላይ ሙሉ በሙሉ በማተኮር ሀዝባችንን ለመከፋፈልና ሀገራችንን አየዘረፉ ለማጥፋት በግልፅና በስውር በርትተው እየሰሩ 25 አመታትን አስቆጥረዋል፡፡ ይህ የአረመኔነት ባህሪያቸው ግን ከአሁ በኋላ አብቅቶለታል፡፡ ትግሬ የሚለውን ስም ከየት እንዳገኙት፣ ማን፣ ለምንና መች እንደሰጣቸው የመን ሀገር ባሪያ በነበሩበት ዘመን ስለመሆኑ ከዚያ ሄዳቸሁ እውነቱን እወቁ፡፡ ትግሬ የሚል ቃል በጥንታዊ የኢትዮጲያ ቋንቋ ግዕዝ ውስጥ አንድም ቦታ ላይ አታገኙም፡፡ ምክንያቱም በዚያን ወቅት ኢትዮጲያ ውስጥ አልነበሩም፡፡ አማራን ግን አምሀራ እያለ ነው ግዕዝ ከጥንት ጀምረሮ ያለማቋረጥ የሚያውቀውና የሚጠራውም፡፡

    ዘረ ባንዳ የኢትዮጲያ ጠላት ወያኔ ትግሬ አማራን የመጥላት አቅምም ሆነ መብት የሚኖረው ሆኖ እያለ ነገር ግን ይህን ጥላቻውን በአማራ ህዝብ ላይ ለመፈፀም መነሳቱ ግን በኋላ ላይ ራስን ማጥፋት እንደሆነ አለመረዳትና የአማራ ህዝብ ማንና ምን እንደሆነ ጠንቅቆ አለማወቅ ነው፡፡ የአማራን ህዝብ ለማጥፋት ጣሊያንም ሞክሮ አልሳካለት አንዳለስ እንዴት የጣሊያን ባንዳ ወላጆቻቸው እያስጠነቀቁ እንዳልነገሯቸው ግን አሁንም ወያኔ ትግሬ እሱነቱ ባንዳነትና ጥፋት ብቻ አንደሆነ የሚያመለክት ነው፡፡

    በእርግጥ ታሪክ የማይረሳውና ሰቆቃ የሆነ ጥፋት በአማራ ህዝብ ላይ ለ25 አመታት ለመፈፀምና ለማስፈፀምም ችለዋል፡፡ የተፈፀመው ወንጀል ሁሉም ተመዝግቦ የተቀመጠ ሲሆን ገና አንዱም በትክክል ያልወጣ ነገር ግን በቅርቡ የሚወጣና እነ የውሸት ዶክተር ነን ባይ ወያኔ ትግሬዎችን ከነዘር ማንዘራቸውና የውጪ ተባባሪዎቻቸው መቀመቅ የሚከት ነው፡፡ ከተከዜ ምላሸ በጎንደር፣ የአባይ ወንዝ ኢትዮጲያን ለቆ እሰከሚወጣ ድረስ ያለው ግዛት በጎጃም፣ በሸዋና ወሎ እንዲሁም በመላው ኢትዮጲያ የሚኖርን ታላቅና ሀያል የሆነ ጥንታዊ የአማራን ህዝብ የአንበጣውና የቁልቋሉ ትግራይ ባንዳዎች ለመጥላት ቢችሉም ነገር ግን መሬቱን እየሰረቁ በመውሰድ ለመጉዳትና እሱንም ለማጥፋት በዘመቻ መልክ መሞከራቸው በይቅርታ የሚታለፍ ሳይሆን በእጥፍ ከነወለዱ በነሱ ላይ በቂም በቀል የሚመለስ የለየለት ወንጀል ነው፡፡ በአሁኑም ሰአት በመኸር የስራና ምርት ወቅት በጎንደርና ጎጃም ግልፅ የሆነ ጦርነት በአማራ ህዝብ ላይ ከፍተው ህዝብን እየጨፈጨፉና ንብረትን እያወደሙ አንደሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡

    የተከዜ፣ የአባይ፣ የጣና፣ የሰሜን ተራሮች፣ የከፍተኛው ቦታ፣ የዝናምና የወንዝ መሬት፣ መልካም መልክአ ምድርና ተስማሚ አየር ያለው ሰራተኛ፣ አምራችና ጥምታዊ አማራን ለማጥፋት ወያኔ ትግሬ በተፈጥሮ ከተረገመ ትግራ ተነስቶ መሞከር ጥፋቱ በነሱ ላይ ሳይሆን በራሱ በአማራ ህዝብ ላይ ስለመሆኑ የታመነበት ነው፡፡ በመሆኑም ለራሱ ለመሆን የማይችል ለሌላ ለመሆን አይችልምና አማራ ኢትዮጲያን ጨምሮ ለሌላ ለመሆን ሲል በቅድሚያ ለራሱ መሆን አለበት፡፡ ይህም የሚጀምር የወያኔን ማንኛውንም ጣልቃ ገብነትና ተፅኖ ከአማራ ህዝብነ ቦታ ላይ ሙሉ በሙሉ መደምሰስና ማሰወገድ ሲሆን ወልቃይት፣ ቃፍታ ሁመራ፣ ጠገዴ፣ ጠለምትና ራያን ማስመለስ የመጀመሪያውና ዋነኛው ተግባር ነው፡፡

    ወያኔ ኩሁሉ ከሁሉ የሚፈራውና የሚጠላው እና ይህንም በማወቅ ያለማቋረጥ ከ25 አመታት ሲሰራበት የኖረ ወንጀል አንዱን ከሌላው የማጋጨት ሴራ ሁሉም ኢትያጲዊያን በአንድነት በመነሳት ሙሉ በሙሉ ሊያጋልጡትና ሊቃወሙት የሚገባ ሲሆን ይህም ከአን ጀምሮ በጋራ መተግበር ያለበት ነው፡፡ እየለ ሁሉንም ሲያጠቃ የኖረን ዘራፊ ወያኔ ትግሬ በመተባበር ከምድረ ገፅ ማጥፋት ይገባል፡፡ ህዝብ ከተባበረበት ገና ሳይነኩት በፍራቻ ነው እንደ ጉም ተበትኖ የሚጠፋ፡፡ በጋራ ጠላት ላይ የህዝብ መተባበር በጣም ወሳኝ ነው፡፡ አማራ፣ ኦሮሞ፣ ጉራጌ፣ አፋር፣ ሀድያ፣ ከምባታ፣ ሲዳማ፣ ወላይታ(ከነሱ የወጣውን ወያኔን ትግሬ የሚያይ አንድ አይን ብቻ ሳይሆን ግማሽ ልብ፣ ግማሽ ጭንቅላትና ግማሽ ስውነት ብቻ ያለው የሚመስልን የወያኔ ተላላኪ ውሻ ጠቅላይ ሚኒስተር ወላይታወች ቢያጠፉት መልካም ነበር)< ጋምቤላና ሌሎችም በመተባበር የጋራ ጠላታቸው የሆነን ወያኔ ትግሬ በከባድ አድማና ማቀብ ጭምር በተለያየ መንገድ በሱ ላይ መነሳትና ጥቃት ማደረስ አለባቸው፡፡

    ከአሁ በኋላ ግን ወያኔ ትግሬ በአማራ ህዝብና መሬት ላይ እንዳለፈው 25 አመታት እሱ ሙሉ በሙሉ የሚያገባውና የሚዘርፍ በፍፁም አይሆንም፡፡ በብአዴን ስም የተደራጁ የወያኔ ትግሬ ቅጥረኛና ተላላኪ በአማራ ህዝብ ላይ ዋነኛ ጠላቶች የሆኑትም እንድ በአንድ አየተጋለጡና እየተዋረዱ እንደ አረም እየተመነጠሩ የሚጣሉ ቆሻሾች ናቸው፡፡ ራስ ደጀን ተራራንና አካባቢውን በይቅርታ እንደመለሱ ሁሉ ከህዝብ በተዘረፈ የሚንቀሳቀስን ሁሉ ዳሸን ቢራና ዳሸን ባንክን ጨምሮ መመለስ አለባቸው፡፡ ይህ ሳይሆን ቀርቶ ግን ከአሁ በኋላ አንድም ባልዲ ውሃ በነፃ የማያገኝና ዳሸን ቢራን በውድ አየሸጠ ትርፍ የሚያካብት አይደለም፡፡

    ህዝቡ ከ2009 ጀምሮ አንድም ጠርሙስ ወይም ብርጥቆ ዳሸንና ቅዱስ ጊዮርጊስ በወያኔ ቁጥጥር ስር ያሉትን ላለመጠጣት የወሰነና በምትኩ ደግሞ ጠላን፣ ጠጅን፣ ብርዝንና የፍራፍሬ ጭማቂወችን ራሱ እያመረተ በመገልገል ስራ ፍጥሮ ትርፉን ለራሱ ለማድረግ ህዝቡ ቃል ግብቷል፡፡ ዳሸን ቢራ ወይ በአማራ ህዝብ በሀብትነት መያዝ አለበት፡፡ ወይም ለቆ መውጣት እንጂ ቢራ ማለት ውሃ ሲሆን ይህን ያህል ውሃ በነፃ እየዘረፈና ቢራን በውደ እየሸጠ ነገር ግነ ለትግራይ ግብር መክፈል ብቻ ሳይሆን ባለሀብቶችም ትግሬዎች ሆነው መቀጠል አይችልም፡፡ በሌሎችም የወያኔ ትግሬዎች የኢኮኖሚ ዘርፍ አውታሮች ላይ የዚህ አይነት የማቀብ ስራ መሰራት አለበት፡፡ የሚጠላውንና ለማጥፋት የሚታገለውን የአማራን ህዝብ ለመመዝበር፣ መበዝበዝና ለመዝረፍ እንዲሁም ቦታውን ለመውሰድ እንዴት ይቻለዋል ይህ በጥላቻ የተሞላና በወንጀል የተጨማለቀ የትግሬ ባንዳ ዘር ሁሉ፡፡

    የወያኔን ማንኛውንም ጣልቃ ገብነትና ተፅኖ ከአማራ ህዝብና ቦታ ላይ ሙሉ በሙሉ መደምሰስና ማሰወገድ ግድ የሚል ሲሆን ወልቃይት፣ ቃፍታ ሁመራ፣ ጠገዴ፣ ጠለምትና ራያን ማስመለስ የመጀመሪያውና ዋነኛው ተግባር ነው፡፡ በመጨረሻ ላይ ሁኔታው በዚህ መልክ እንደሚቋጭ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ይህም ይሆን ዘንድ እንደ እሳተ ገሞራ ፈንድቶ በታላቅ ሀይልና ወኔ ሁሉም በአንደነትና በቆራጥነት ለመብቱ፣ ሀብቱ፣ ንብረቱ፣ ማንነቱና ህልውናው ቆርጦ የተነሳና ማንኛውንም መስዋዕት ለመክፈን ያለማወላወል የወሰነ ነው፡፡

  4. ያልተነካ ግልግል ያዉቃል ተብሉዋል እኮ ፡ እኛ የምንለዉ ሁሉም ሰዉ በአንድ አይን ያለአድልኦ መታየት አለበት ፡ ሰዉ በሀገሩ እንደዚግነቱ አገሬ ብሎ ዘና ብሎ ሲኖር ቀጥሎ ባለዉ ስለዲሞክራሲ ኢኮነሚ ማህበራዊ ኑሮ መነጋገር ይቻላል ፡ እንዲሁም ሰዉ በጎሳ በሐይማኖቱ ብሎም በማንነቱ ሳይሸማቀቅ ሠርቶና ዉሎ ሢገባ በዘር በጎሳየ ምን ይደርስብኝ ይሆን ብሎ ሳይጨነቅ አንዱ ጎሳ በወዳጅ ሌላዉ በጠላትነት እየተፈረጄ እንዴትስ ምን አይነትስ ኑሮ እንኑር ። አንድ ወንድሜ የለዉጥ ማዕበል ብሎ ከላይ እንዳሠፈረዉ ቢሆን ጥሩ ነገር ነበር ፡ ነገር ግን ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ማለትም በሕወሀት ዘመን ሁሉንም ልጆችዋ በእኩል አይን አታይም ።

    እንዲያዉም የሚገርመዉ ነገር በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ አገራችን ዉስጥ ከቀን ወደቀን እየሆነ ያለዉ ነገር በጣም አሥፈሪ እየሆነ መጥቶአል ። ይኸዉም በስርአቱ በበጎ አይን ከታየ የሚሮጠዉ ለቅንጦት ነዉ ፡ ለገዥዉ መደብ አይን በበጎ ካልታየም ጥቅሙ ይቅርና ሕልዉናዉም አደጋ ላይ ናት ።
    ይህን አይነት የህይወት ዉጣ ዉረድ ለ25አመታት የከፈለ አሁንም በከፋና በባሰ መልኩ በቀጣይነት እየከፈለ የሚገኝ ዜጋ አለ እንደሚታወቀዉ ማለት ነዉ ። ነገሩ በአንድ ህብረተሰብ ብቻ አላቆመም ሁሉን ኢትዮጵያዉይ ወገናችን እንደሰደድ እየለበለቡት ይገኛሉ ። ታዲያ አሁን የምንመከረዉ ወያኔ ህዝቡን ጨርሶ መሬቱን ለብቻዉ ተቆጣጥሮ ይኑር ማለት ነዉን ። በራሴ ምንም እነሱ ቢከፉም የባሰ ጥፋት እንዳያደርሱ ተሻሽለዉ ወይም ተዳክመዉ በሥልት ይወገዳሉ የሚል እምነት ነበረኝ ፡ ነገር ግን እየቆየ ሢታዩ እንዲያዉም አገሪቱን ከመሸጥ ከመለወጥ አልፈዉ ህዝቡንም ከምድረገፅ ለማጥፋት ይኸዉና እንደሚታየዉ ይጣደፉ ጄመር ።

    እንግዲህ ሁለት አማራጮች አሉን ይመስለኛል ፡ አንድ እንደሢሪና እንደሊቢያ እየተዋጉ መጣልና መዉደቅ ፡ አሊያም ዝም ብሎ በወያኔ እየታረዱ ማለቅ ።

  5. Neither the point, nor the purpose of your article is clear.It Seems you have some confusion on the current Ethiopian issue. I am glad” arat mekeraker” has to put it in details for people who think the same way.

  6. Qexayun lemanbeb megbabiya:
    sweers= xafacoch, color = qelem, correct = tkkl, monday = seño

    kahun behuala mdr kef, semay zq bil tglu biyans woyanien kemedemses ayansm, sibeza demo yekulnet ager adisun etiopiya memesret new.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*