በመምህር ዶ/ር ዘበነ ለማ በዛሬው ዕለት ተጠርቶ የነበረው ”ለቅሷዊ ጸሎት” በምዕመናን ድርቅ ተመታ

  • የምዕመናን ቁጥር ከተጠበቀው እጅግ አነስተኛ ነበር
  • ለምዕመናን ቁጥር መመናመን ዋናው ምክንያት ከሳምንት በፊት ደብሩን ረግጠው በነበሩት አባ መላኩ (አቡነ ፋኑኤል) ምንያት ነው የሚሉ ብዙዎች ናቸው
  • መምህር ዘበነ በቅርቡ አገራችን ውስጥ በወያኔ እየተጨፈጨፉ ለሚገኙት ወገኖቻችን የሰጠውን ወያኔን የሚደግፍ እንዲሁም ከወንጌል የወጣ ምላሽ በርካታ ምዕመናንን ማስቆጣቱና ማሳዘኑ እየተነገረ ነው
  • ቆሞስ አባ መዓዛ ክርስቶስ በየነ፣ መምህር አሸናፊ ዱጋ፣ መምህር ዶ/ር ቀሲስ አንዱዓለም፣ ዲያቆን ኃይለጊዮርጊስ ተፈራና ሌሎችም የአገራችንን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክተው ወያኔን የሚያወግዝና የሚኮንን  ጠንካራና ትክክለኛ ትምህርት መስጠታቸው መምህር ዘበነን ብቻ በወያኔ ደጋፊነት ተነጥሎ አንዲታይና እንዲጋለጥ አድርጎታል የሚል አስተያየትም እየተሰጠ ነው
  • ጸጥታ ለማስጠበቅና ለትራፊክ ተጠርተው የነበሩት ፖሊሶች የመጣው ህዝብ ቁጥር አነሰተኛ በመሆኑ ለምን እንደተጠሩ ሳይገረሙ አልቀረም ተብሏል

መምህር ዘበነ ለማ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው እጅግ አፋኝ፣ ጨፍጫፊና ኢሰብዓዊ የወያኔ አገዛ ላይ ምንም ዓይነት ትችት፣ተግሳጽ፣ ተቃውሞና ውግዘት ማድረግ አያስፈልግም “የክርስቲያኖች ተግባር መጸለይ ብቻ ነው” በማለት በሚሰጠው  የተዛባ ስብከት ምክንያት ብዙ ተቃውሞ ሲሰነዘርበት እንደቆየ ይታወቃል። ቁጥራቸው በቀላሉ የማይገመት ምዕመናንን እሱ አሜሪካ ከመምጣቱ በፊት እጅግ ጠንካራ የወያኔ ተቃዋሚ የነበሩ የሱን ስብከት በመስማት ለአገራቸው ተግባራዊ አስተዋፅኦ እንዳያደርጉና በወያኔ ላይ ጠንካራ አቋም እንዳይወዱ አሽመድምዷቸዋል እየተባለ በስፋት ይነገራል። በተለይም በተለያየ ጊዜ ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ውስጥ በወያኔ ላይ የተደረጉትን የተቃውሞ ሰልፎች “ክርስቲያኖች ለዓለማዊ መሪዎች አቤቱታ አናቀርብም እኛ ወደ ሰማይ ብቻ ነው የምንጮኽው” እያለ አወደ ምህረት ላይ ቆም በማጥላላቱ በርካታ ምዕመናንና ካህናት ሲቃወሙት ኖረዋል።

ከአንድ ዓመት በፊት በሊቢያ በሰማዕትነት ላለፉት ኢትዮጵያውያን ዋሽንግተን ውስጥ ተካሂዶ በነበረው የጸሎት ዝግጅት ላይ ወያኔን የሚያወግዙ ጠንካራ የሃይማኖት አባቶች በአቡነ መቃሪዎጽስ መሪነት ባካሄዱት ዝግጅት ላይ “ከመንግሥት ያጋጨኛል” በማለት ሌላ የግሉ ዝግጅት ማድረጉ አይዘነጋም። መምህር ዘበነ ለማ እንደለመደው  በዛሬውም ዕለት ቴምፕል ሂልስ፣ ሜሪላንድ በሚገኘው ቤተክርስቲያን ውስጥ የጠራው የለቅሶና የጸሎት ዝግጅት በቅርቡ አገራችን ውስጥ በወያኔ ለተጨፈጨፉት ወገኖች እንጸልያለን የሚል ስም የተሰጠው ሲሆን ወያኔን በማያስቀይም ሁኔታ እጅግ በተለሳለሰ ሁኔታ የተካሄደ እንደነበር ተገልጾልናል።

ኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ጊዜ ወያኔ ንጹሃን ዜጎችን እንደ ከብት አያረደ ባለበት ጊዜ መፍትሄው ነፍሰ ገዳዩ ከድርጊቱ እንዲታቀብ ማስገደድ መሆኑና ህዝብ የህይወት ዋጋ እየከፈለባቸው ላሉት ጥያቄዎች ተገቢውን መልስ መስጠት መሆኑ እየታወቀና መፍትሄውም በሰው እጅ (በወያኔ አጅ) የሚገኝን ነገር “መቅሰፍት”፣ “መዓት” ወይም “የፈጣሪ ቁጣ”  አንደወረደ አስመስሎ ሁኔታውን አጣሞና ኣወላግዶ ለምዕመናን  የተሳሳተና የተንሸዋረረ ትምህርት እየሰጠ ነው። መምህር ዘበነ ይህንን በማድረግ  ህዝብ ያነሳቸው የህልውና ጥያቄዎች እንዳይመለሱ እንዲሁም በማለቅ ላይ ያለው ህዝብ ዝም ብሎ እንዲታረድና ለወያኔ ሰጥ ለጥ ብሎ እንዲገዛ በተዘዋዋሪ መንገድ እያመቻቸ መሆኑን መረዳት አያዳግትም።

በዛሬው ዕለት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ምዕመናን ይመጣሉ ተብሎ ተጠብቆ የነበረ ቢሆንም እጅግ አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ካህናትና ምዕመናን ብቻ መገኘታቸው መምህር ዘበነ ለማ በወቅታዊው የአገራችን ሁኔታ ላይ ከህዝብ ጎን ከመቆም ይልቅ ከወያኔ ጎን በመቆሙ ምክንያት ነው በማለት የቤተክርስቲያን ጉዳይን እግር በእግር የሚከታተሉ ምዕመናን እየተናገሩ ነው። በዛሬው የመምህር ዘበነ ዝግጅት ላይ ይመጣሉ ተብለው ለነበሩ ምዕመናን የትራፊክ መጨናነቅን ለማስወገድ ከቤተክርስቲያኑ ሂሳብ ወጭ በማድረግ ተቀጥረው የነበሩ ፖሊሶች የመጣው ተሳታፊ እጅግ አነስተኛ ስለነበር ምንም ሳይደክሙ በዕረፍት ነው ያሳለፉት የሚል አስተያየትም ተሰጥቷል። (እንደውም አንዳንድ ቀልደኞች ፖሊሶቹ እጅግ ብዙ ወንጀል በሚፈጸምበት የፕሪንስ ጆርጅ ወረዳ ውስጥ ሲደክሙ የሚውሉ ስለሆነ የተጨማሪ ሰዓት ክፍያ ተደርጎላቸው አንድ ቀን አርፈው መዋላቸው መልካም ስራ ነው የሚሉም ተደምጠዋል። የተደረገው የጸሎትና የሐዘን መግለጫ ሁኔታም በመምህር ዘበነ ለማ የተመራ ሲሆን አካሄዱ ያልተለመደና አንዳንዶችን ግራ ያጋቡ እንግዳ ሁኔታዎችም የታዩበት ነበር  ።

ምንም እንኳ እንደ መምህር ዘበነ ለማ ያሉት ሀቁን ጨፍልቀው ከነፈሰ ገዳዮች ጋር አብረው ቢሰለፉም ማህጸኗ የማይነጥፈው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ያፈራቻቸው በርካታ እወነተኛ መምህራን አሏት። ከነዚህም መካካል መምህር ዶ/ር ቀሲስ አንዱዓለም “አባቶችህ የሰሩትን የቀድሞውን የድንበር ምልክት አታፍርስ” እንዲሁም ዲያቆን ኃይለጊዮርጊስ ተፈራ “የደሙ ድምፅ” በሚል ርዕስ ወቅታዊው የአገራችንን ጉዳይ  አስመልክተው የሰጧቸውን ትምህርቶች አቅርበንላችኋል።

       መምህር ዶ/ር ቀሲስ አንዱዓለም “አባቶችህ የሰሩትን የቀደመውን የድንበር ምልክት አታፍርስ”

ዲያቆን ኃይለጊዮርጊስ ተፈራ “የደሙ ድምፅ”

 

https://youtu.be/exbWPyv41H0

 

 

 

 

30 Comments on “በመምህር ዶ/ር ዘበነ ለማ በዛሬው ዕለት ተጠርቶ የነበረው ”ለቅሷዊ ጸሎት” በምዕመናን ድርቅ ተመታ”

  1. why talking about Zeben so much. OUr people and country is in serious problem. You are wasting your as well everybody’s time on a subject of self interest. If you have a kind of complex towards Zeben try to solve it personally.

  2. sorry I’m confused what is the problem praying please don’t make every thing impossible prayer change everything don’t make things difficult by false news GOD bless my beloved ETHIOPIA ????

  3. Begebachu ema weyane new Amharahun Oromohu ,Bet Kirstiyanen atefalew belo yemetaw tadia zare weyanen begeletse mekawem weyes asemeselo malef ,Zare betekirstianem Eyechohech new Kahenat Menekosat Deyakonat mehemenu ,Zare,kes wayem Diyakon hono lemeketer Bezer ,Gubo bemekefel behonebet Agere,Yemela yeAger gudayun poletica Yemil Ye Weyane Tarega yemiletefu geleseboch Weyane weyem Atalayoch mehonachu enekewn legna,Ye Ethiopia Guday yagebanal lemenelew Ethiopian Kereto yetegnawem yewchi ziega Yeredachewal.Lemanegnahum Egzihabeher yeferedewen Sew Ayesherewem .

  4. Zebene america min yiseral weyane asadot newu endayibal yeweyane degafi newu .lemastemar endayibal bahunu seat ersu ethio geter wust newu mastemar yelebet.leloch eko weyane ethio wust endayinoru asaduachewu newu

  5. ኢትዩጵያ አሁን የሚያስፈልጋት ጸሎት ብቻ ሳይሆን ሥራም ጭምር ነው። ጸሎቱም ቢሆን መምህር ዘበነ እንደሚያደርገው ያለ ከወንጌል የራቀ “ለመሪዎች ተገዙ፣ተጨፍጨፉ” ሳይሆን ገዥዎችን አውግዞ ህዝቡ እራሱን ነጻ እንዲያወጣ ማበረታታት ነው። ከመምህር ዘበነ በስተቀር ሌሎች በዚህ ዜና ላይ እንዳሉት መምህር አንዱአለም፣ ዲያቆን ኃይለጊዪርጊስና ሌሎችም ትክክለኛ ወንጌል እይውሰበኩ ነው። እኔ መምህር ዘበነ በትምህርቱ ከማደንቃቸው አንዷ ስሆን ለሱ የምለጠው ምክር ትምህርትህን አስተካክል በወያኔ ለሚያልቀው ህዝብ ተቆርቋሪነት አሳይ እንዲሁም አገርን በጎሳ ከፋፍለው የሚጨፈጭፉትን ወያኔዎች አውግዛቸው ወኔው ይኑርህ ክርስትና እኮ ዋጋ ያስከፍላል በተለይ መምህር ሂነው ማማ ላይ ከወጣህ።

  6. በጣም የሚያሳዝን ጉዳይ ነው። በእግዚአብሔር ቤት ከምእመናን ይሰጠው የነበረውን ክብር ጥሎ አሁን አገሪቷን ደም ከሚቀቡ አረመኔዎች ጋር መሆኑ በግልፅ እንደሚያስታውቅበት ቢገባው ጥሩ ነው ። ከእነ መምህር ዳንኤል እውንትን መማር ያስፈልጋል እዚህ አገር ሆኖ የሽንገላ ስብከት በቃን እግዚአብሔርን ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን ። ለእውነትና ለሀይማኖታችን የቆሙት ፀሎት ሀገራችንን ይጠብቅልን።

  7. በእግዚአብሔር ቤት በብልጠት አምታቶ አለባብሶ መስበክ ይቅር ፍልስፍና ሳይሆን እውነት የምነገርበት የተጎዳውን የጎዳውን ተለይቶ የምፀለይለት ነው። መማር ማለት መፍራት ማለት አይደለም እኛ በቤቴክርስቲያን እምንት እያጣን ከእምነታችን እየተስጏጎልን ነው እና እውነት የሚታይበት ቀን እሩቅ አይደለም

  8. why don’t you protestants and anti Ethio-orthodox christian elements impose off your hands from our church and its servants who are daily busy with the apostolic mission of their mother church which Dr. Zebene is an active part of it ??? !!! Pls leave alone Dr. Zebene, he is one of the sons of the godly sons of the church who is dedicated to the spreading of gospel. We know very well that it is the protestants who are capitalizing on the situation to defame and attack the name of our son , Dr. Zebene. Ultimately their scheme is to attack out mother church Ethiopian orthodox and its biblical teaching. We Ethiopian orthodox believers have long got wise to your diabolic people of protestants. Hand off , it is none of your business to meddle in the matter of our country and our belief. in the first place,i do not recognize the protestants as Ethiopian and this leads me to conclude that it is none of your business to meddle both in our country affair and church too. May God Almighty and the Holy Son of God the father and of Saint Mary rebuke the diabolic spirit that is dwelling in you protestants that is spreading hatred and gossip against our church and its servants !!! Amen

  9. መምህር ዘበነ እስቲ እዛው አብራችሁ አንድ ደብር የምታገለግሉትን መምህር አሸናፊን እንዲሁም አጠገብህ ያሉትን አባ መአዛን እንዲሁም መምህር አንዱ አለምንና ዲያቆን ሐየለጊዮርጊስ በቅርቡ አገራችን ውስጥ በወያኔ የደረሰውን ጭፍጨፋ አስመልክተው ተሰጧቸውን ትምህርቶች አዳምጣቸው። እንደሚመስለኝ ያንተ ችግር የምታዳምጠው እራስህንና አጨብጫቢዎችህን ብቻ ነው። የተማርክ ሰው ነህ እስቲ ሌሎችንም አዳምጥና ትምህርት ውሰድ። ወያኔን አውግዘው እንጅ እድሜ አትለምንለት። እግዚያብሔር የማስተማሩን ክህሎት የሰጠህ ቤተክርስቲያንን እንድታገለግል አንጅ ገዥዎችን እንድታገለግል አይድርል።

  10. የዘበነ ቡችሎች በፀሎት ሥም ማጭበርበር አይቻልም፡እንደመጥምቁ ዮሐንስ ንጉሥ ሄርድስን ገስጾ ሕይወቱን ለእምነቱ የሰዋ የእምነት አባቶች ነው የሚያስፈልጉን ማቴ14 ይነበብ፡፡
    አገራችንን አግዚአብሔር ሠላም ያድርግልን፡፡

  11. Yetazebew it is true a prayer is needed but if you know your history Abune Petros died not praying but while denouncing Italians the grand father of weyanes!

  12. Tesfaye Mekoya stay out of this, we heard you changed your tune on weyane keep on that but insulting the people who are against weyane on the open by using Ginamo doesn’t work.

  13. Anonymous you are funny, first of if you are talking about God you shouldn’t write it as”god” second you can hold Zenebe on your back and be at his service, that is what is left of you guys around him to do. Who cares about what you think? Jumping to behind the issue using the protestants is the game you learned from none other that Mr.Z, get over it but don’t try to make every one who is the Z is plente. No we are concerned Ethiopian Tewahido church followers. Don’t his behind the curtain and take the big stick out of your eyes.

  14. It is so depressing to see the road Ethiopians are going now which is downhill!!! In the old times, only the prayer helped us GOD to send st George to our country to help us fight the Italians. Minilikye took the Ark of the Covenant with him to the war right after a long prayer at the church. This tells me that our faith in God is decreasing and we are more dependent on people. If we don’t change our attitude and depend on God as we always have, the end will be unpleasant.

  15. By the way
    I was a smoker and alcoholic until I found Memhir Zebenes preaching on you tube and started to watch it everyday. He turned my life around and for the last seven years I’ve been free of everything and a servant of God. Not only me but also so many of my friends. So please leave him alone!!!

  16. We ask M Zebene to stand with the truth and to for our country not for personal interst you guys.That change is coming for you and ur friend what about the truth think about it if you loyal person ,for me Its about talking reallity and very important.

  17. just to give you guys some reminder, every church has a law to accept anybody for wedding and funeral services. Abune Fanuel went to the church only to celebrate a wedding of one member of that church. Nothing more, nothing less. Stop talking about anybody. It concerns me how you guys get along with each other if we remove weyane and we take the power. Shame shame shame!!!

  18. zebane Lema. He wayne kadra. long time he was ethiopia 15 years ago he was said ( waywalat america ) americ yemenore mate yowerdbatal.way do not he back ethiopia. he has mission. wayna send him usa he divide despora. his job change the drication

  19. መምህር ዲያቆን ኃይለጊዮርጊስ እግዚያብሔር ይስጥልን እጅግ ጠቃሚ የሆነ የተብራራ ትምህርት ስለሰጡን። እኔ በዘበነ መሙለጭለጭና “መንግስትን ልቦና ይስጥልን” ማላዘን ካዝኑት አንዱ ነኝ። ነፍሰ ገዳይን በልመናና በተማጽኖ ማስቆም ቢቻል ኖሮ ዓለም አሁን ካለችበት የተበላሸ ሁኔታ እጅግ የተሻለች በሆነች ነበር። የኢትዮጵያ ሕዝብ 25 ዓመት ሙሉ ወያኔዎችን ለመነ ተማጽነ ከአሁንም በኋላ ልመናውና እዬዬው እንዲቀጥል ነው የመምህር ዘበነ ዓላማ? እነ መምህር ኃይለጊዮርጊስ ዓይነት “አካፋን አካፋ፣ ዶማን ዶማ” የሚል ቆራጥ የወንጌል መምህር ያስፈልጉናል። መመህር ዘበነ እባክህ አንተም የኛው ወገን ነህና ተግሳጻችንና ተቃውሞአችን ተቀበልና ተመለስ። ከተሳሳቱበት መመለስ ወንጀል አይደለምና። እንደውም የአዋቂነት፣ የመማርና የመብሰል ማረጋገጫው የህዝብን ቅሬታና ምክር መቀበል ነው።

  20. እውነቱን አይተው ለህዝቡ የማይናገሩ እንደ ጉዱ ዘበነ ከወያኔ ጋር በሰው ደም የሰከሩ በሰው ስጋ የጠገቡ እንጁ ሌላ ምን ይባላል።

  21. አቤት ሁሉም አንደ ጉግት ይጮሀል፣ የሚያዳምጥ የለም አቤት የክፈተችን ብዛቱ ከአስመሳይ ብዛቱ ከቄስ እና ከህዝብ።
    የድንግል ማርያም ልጅ እየሱስ ክርስቶስ እባክፈ ጠፈተን እንዳንቀር እባክህ የመጨረሻውን እድል ስጠንና ልባችንን አገናኝልን። በምፃትህ ጊዜ ምን ይዘን ከአንተ ፈት እንቀርባለን??????????????

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*