የኢሕአዴግ የተሀድሶ ተምሳሌት የኢንደስትሪ ሚንስትር አህመድ አብተው የሙስናው ንገሥ !!

አህመድ አብተው የተባለው በሙስና የበሰበሰ ሰው ወሎ ዩንቨርሲቲ ስለመታደስ ሲያወራ ምሽት ዜና ላይ ሰማሁት። አቶ አህመድ የዐማራ ክልል የገጠር መንገዶች ኃላፊ ሆኖ ሲሰራ የተገኘባት የሙስና ወንጀል እስካሁን ይገርመኛል።

የዐማራ ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ኦዲተሮችን (በ2004 ዓ.ም ይመስለኛል) የኦዲት ባለሙያዎችን ወደ ገጠር መንገድ ዋና መሥሪያ ቤት ላከ። ወያኔ ተፈጻሚ ያልሆን ሁሉንም የገጠር ቀበሌ በመንገድ ማገናኘት በሚል እርዳታና ብድር ከዓለም ባንክ የሰበሰበበት ወቅትም ነበር።
የሆነው ሆኖ የኦዲት ባለሙያዎቹ የክልሉ ገጠር መንገድ የተከራያቸው እና ውድ የኪራይ ዋጋ የሚወጣባቸው ሁለት የመንገድ መደምደሚያ ቡልዶዘር መኪናዎች ይገኛሉ፤ ኦዶተሮቹ ፋይሉን ሲመረምሩ የአቶ አህመድ አብተው ሆነው ተገኙ።
ጉዱ በዚህ ቢያበቃ ጥሩ ነበር፤ ለመሥሪያ ቤቱ በእርዳታ ከመጡት ቡልዶዘሮች ሁለቱ ይጠፋሉ። ፋይል ሲገላበጥ ሊብሬያቸው በአቶ አህመድ ስም መግባታቸውን አሳየ። አቶ አህመድ በስሙ ያደረገውን የሕዝብ ሀብት መልሶ በውድ ዋጋ ኃላፊ ሆኖ በሚሰራበት መሥሪያ ቤት እያከራየ ቸክ እራሱ እየጻፈ ይበላል።
ኦዲተሮች ሪፓርት አደረጉ። የክልሉ ምክር ቤት ጉድ አለ። ከዚያም በአስተዳደር ውሳኔ ይሰጠው ተብሎ “አፉ” ተባለ። በኋላም አቶ ኃይለማርያም የኢንደስትሪ ሚንስትር አድርጎ አሳደገው። እዚያ ሂዶ ምን ፋብሪካ በስሙ እንዳደረገ እግዜር ይወቅ።
ይህ ግለሰብ የሀይቅ ሀይቅን አደጋ ላይ የሚጥል ፕሮጀክትም ተፈጻሚ በማድረግ ይታወቃል።

የኢሕአዴግ የተሀድሶ ተምሳሌት አህመድ አብተው!!Muluken Tesfaw

3 Comments on “የኢሕአዴግ የተሀድሶ ተምሳሌት የኢንደስትሪ ሚንስትር አህመድ አብተው የሙስናው ንገሥ !!”

  1. do not lie,he is hard worker but we know you bs he is moslim;no more ortodox power,

  2. ከወያኔና ፡ በኢሕሃደግ ስም ከሰበሰባቸው ውሾቹ ውስጥ ፡ በማጭበርበር ያልተካነ ይገኛል ብዬስ አልጠረጥርም። ተጋዳዩን ጳጳስ ጨምሮ!

  3. ይህ ሰው ቀላል አይምሰላችሁ በሃይቅ የውሃ አካባቢ ለልማት ብሎም አጥሪ ኢንቨስተሮች ጋር በመተባበር የሰራው ደባና በገንዘብ እያስጠፋ ያለውን ይህ ታሪካዎ ቦታ እንድበከልና እንድጠፋ ዋነኛው ቀንደኛ የወያኔ ቀውስ ፈጣሪው አህመድ አብተው ለቀጣዩ ትውልድ ጥቅም እንዳይሰጥ በደም የተጨማለቀ ነው፡፡
    ይህ ሰው የወሎን ዩንቨርሲቲ ስለመታደስ ሊነግረን አይደለም እንደውም አህመድ አብተው ዪንቨርሲቲውን ከሚያዳከሙት ቀንደኛው የብአዴንና ከወያኔ ጋር በማበር አማራን የሚጠላ ፣የሚገድል፣የሚያሳፍን ይባስ ብሎ በአንዳንድ አካባቢዎች በጎ አድራጊ የወሎ ተወላጆች ትምህርት ቤት ለመስራት ጥያቄ ሲያቀርቡ አህመድ አብተው ባማራቸው ካድሬዎቹ በወያኔ ሪሞት ኮንትሮል የሚንቀሳቀሱ ጸር ሰው ጸር ኢትዮጵያዊያን በተለይ ከ40 አመታት በላይ በወያኔ የተገደሉት አማራዎች ቁጥር ሰንት ነው ትውልድ ማወቅና ለቀጣዩ ተተኪ ትውልድ እንወቀው አህመድ አብተው ግን የባንዳ ልጅ መሆኑ ይታወቅ
    ሰይድ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*