‹‹የባለ አደራ መንግስት መቋቋም አለበት›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት (የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር)

ኢ/ር ይልቃል ጌትነት (የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር)  Addis Admass
የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ላለፉት 3 ወራት በአሜሪካና ካናዳ ባደረጉት
የሥራ ጉብኝት ከየአገራቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር መወያየታቸውን ይገልጻሉ፡፡ ሰሞኑን ወደ
አገራቸው የተመለሱት ኢ/ር ይልቃል ከአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ አለማየሁ አንበሴ ጋር አጭር ቃለ-
ምልልስ አድርገዋል፡፡

የአሜሪካ ጉብኝትዎ አላማ ምን ነበር?
በመጀመሪያ የሄድኩት ወደ ካናዳ ቶሮንቶ ነበር። በዚያ የሰሜን አሜሪካ የስፖርት ፌስቲቫል ይካሄድ ነበር፡፡ በፌስቲቫሉ ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው ሁኔታ ንግግር እንዳደርግ አንድ ማህበር ጋብዞኝ ነው የሄድኩት፡፡ እኔ ከሄድኩ በኋላ በአጠቃላይ በሃገር ውስጥ ያሉ ነገሮች እየተለዋወጡ መጡ። ስለዚህም ለኢትዮጵያውያን፣ ለአሜሪካና ለካናዳ መንግስት ባለስልጣናት እንዲሁም ለተለያዩ የሲቪክ ማህበራትና ለሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፤በኢትዮጵያ እየደረሰ ያለውን የጅምላ እስርና ግድያ እንዲያውቁ አድርገናል፡፡ ለወደፊትም መፍትሄው ምን መሆን እንዳለበት ከሚመለከታቸው አካላት በተለይም የኢህአዴግ ወዳጅ ከሆኑ ከሁለቱ ሃገራት መንግስታት ጋር ለመነጋገር ችለናል፡፡
ውይይታችሁ ምን ላይ ነበር ያተኮረው?
መንግስት ነገሮች ከቁጥጥሩ ውጪ እየወጡበት እንደሆነ በስፋት ተነጋግረናል፡፡ ቀደም ሲል ስንሄድ የምንነጋገረው ስለ ጋዜጠኞች እስር፣ ስለ ፖለቲከኞች እንግልትና እስር ነበር፡፡ አሁን ግን ተቀይሯል፡፡ በቀን ስንት ሰው ሞተ? የሚል ጥያቄና መረጃ ነው የሚሰማው፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ የኢትዮጵያ ሁኔታ አሣሣቢ እየሆነ ነው፡፡ አስቸጋሪ ወደ ሆነ ሁኔታ እየገባን ስለሆነ እነዚህን ነገሮች በስፋት አንስተን ተነጋግረናል፡፡ ለካናዳና ለአሜሪካ መንግስታት በዚህ ጉዳይ ላይ እኔም ዶ/ር መረራም በስፋት አስረድተናል። በካናዳ ከውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሰዎች ጋር ተነጋግሬያለሁ፣ ከሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋርም ተወያይቻለሁ። በአሜሪካ ከውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሰዎችና ከቪዛ ክፍል ሃላፊዎች ጋር ተነጋግሬአለሁ፡፡ በካናዳ የኢትዮጵያ ልማት ተራድኦ ድርጅት ዳይሬክተርንም አነጋግሬያለሁ፡፡ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ቋሚ ሴኔት ጋር ለመነጋገር ችያለሁ፡፡ በኋላም ከዶ/ር መረራ ጋር ሆነን፣አትላንቲክ ካውንስል በሚባል የውይይት አደራጅ ቡድን አማካኝነት የአደባባይ ምሁራን ከሚባሉት እንዲሁም ከአሜሪካ መንግስት የውጭ ጉዳይና ከኮንግረስ የተውጣጡ ሰዎች ሆነው፣ የኢትዮጵያን አጠቃላይ ወቅታዊ ሁኔታና የወደፊት እጣ ፈንታን በተመለከተ ንግግር አድርገናል፡፡ እኔም ዶ/ር መረራም ስለ ጉዳዩ በስፋት አብራርተናል፡፡
የአሜሪካ ባለስልጣናት አሁን ስላለው የሃገሪቱ ጉዳይ ተጨባጭ ዕውቀትና ግንዛቤ አላቸው?
የቁርጠኝነት ጉዳይ ነው እንጂ በቂ ግንዛቤ አላቸው፡፡ ይሄን የሚያውቁበት የተለያዩ መንገዶች አላቸው፡፡ ከኤምባሲው በየቀኑ መረጃ ያገኛሉ፡፡ መድረኩን ልዩ የሚያደርገው በአሜሪካ መንግስት የተለያዩ መዋቅር ውስጥ ሁነኛ ቦታ ያላቸው ሰዎች መገኘታቸውና ሰብሰብ ብለው የኛን ጉዳይ ማዳመጣቸው ሲሆን ይሄም  ጉዳዩ የበለጠ ትኩረት እንዲያገኝ ረድቶታል፡፡ በመድረኩ ላይ ለወደፊት ምን ታስባለችሁ ተብለን ስንጠየቅ፣ የኛ ምላሽ የነበረው አሁን ባለው ሁኔታ ኢህአዴግ ብቻውን የሚፈታው ነገር እንደሌለ፣ ህዝብም በተለያየ ሁኔታ ተቃውሞውን እየገለፀ ያለው ይሄን ችግር ይፍታልን በሚል ሳይሆን ኢህአዴግን ይሁንታ የመንሳት አይነት መሆኑን ጠቁመን፣ ይሄ ደግሞ በቀላሉ የሚታከም ባለመሆኑ፣የባለአደራ መንግስት ተቋቁሞ ለዲሞክራሲ አስፈላጊ የሆነ ተቋማትን ለ1 ዓመት ተኩል ያህል በማስተካከል፣የፖለቲካ ቡድኖች ተወዳድረው ስልጣን የሚይዙበትን መንገድ ማመቻቸት አስፈላጊ መሆኑን ነው፡፡ ከዚህ ውጭ የሚደረግ ጊዜያዊ የጥገና ለውጦች አገሪቱ አሁን ላለችበት ችግር መፍትሄ የሚሰጥ እንዳልሆነ ተናግረናል፡፡ ይሄን ሃሳብ በሚገባ እንዲይዙትም አድርገናል፡፡
የእነሱስ ምላሽ ምን ነበር?
አንድ መገንዘብ ያለብን ነገር፣ የትግሉና የጉዳዩ ባለቤት የኢትዮጵያ ህዝብ ነው፡፡ የእነሡ ድጋፍ ብቻ ነው ሊሆን የሚችለው፡፡ እኛ ችግሩን በሚገባ ነግረናቸዋል፡፡ “ኢህአዴግ የልብ ወዳጃችሁ እንደሆነ እናውቃለን፤ ‹ኢሳያስና አቶ መለስን ከቅኝ ግዛት በኋላ የመጡ የአዲሱ ትውልድ አመራሮች› እያላችሁ ታሞኳሻቸው ነበር፡፡ ነገር ግን አሁን ኤርትራ የት ነው ያለችው? ኢትዮጵያ ምን ደረጃ ላይ ናት? ይሄን ገምግሙ” ብለናቸዋል፡፡ ኢህአዴግ ብቻውን ያለውን ችግር አይፈታውም፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ የራሳችሁንም ጥቅም ልታጡ ትችላላችሁ፡፡ የምትረዱን ለኛ ብቻ ሳይሆን ለራሳችሁም ጥቅም ጭምር ነው ብለን አስረድተናቸዋል፡፡ በእናንተ የተለሳለሰ ፖሊሲ ምክንያት ብዙ ሀገር ፈርሷል፡፡ ኢትዮጵያ በቀጠናው ጠንከር ያለ ታሪክ ያለው ህዝብ  ሀገር ነች፤የአህጉሩ መቀመጫ ነች … የዚህች ሀገር መረጋጋት አቅሙ ለእናንተ ነው፡፡ ችግሮች ተባብሰው ሀገሪቱ ከመፍረሷ በፊት አንድ ነገር አድርጉ ብለን በትኩረት ነግረናቸዋል፡፡ እነሱም ጥያቄ እየጠየቁን በጥሞና ሰምተውናል፡፡
ለሀገሪቱ ወቅታዊ ችግር መፍትሄው ምንድን ነው ይላሉ?
መፍትሄው አጭርና ግልፅ ነው፡፡ የባለአደራ መንግስት ማቋቋም ብቻ ነው፡፡ ኢህአዴግ አሁን ከባድ የቅቡልነት ችግር አለበት፤ህዝቡ የሚያነሳቸው ጥያቄዎች “ኢህአዴግ በቃን” ወደሚል ተሻግሯል፡፡ ጥገናዊ ለውጦች አድርጌ የህዝብ ይሁንታ አገኛለሁ እያለ ቢሆንም ህዝቡ እስከ ህይወት መስዋዕትነት ድረስ እየከፈለ ያለው መሰረታዊ ለውጥ ስለፈለገ ነው፡፡ ስለዚህ ሀገሪቱን ከቀጣይ ጥፋት ለማዳን የባለአደራ መንግስት መቋቋም አለበት፡፡ ከዚያ ውጪ የሀገሪቱን ሁኔታ ሊያረጋጋ የሚችል ነገር እንደሌለ እኔ በአፅንኦት ነው የምናገረው፡፡
የባለአደራ መንግስት ሲሉ ምን ማለትዎ ነው? ማን ነው የሚያቋቁመው?
ከሀገር ሽማግሌዎች፣ ከሲቪል ተቋማት፣ ከታዋቂ ሰዎች፣ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጣ ነው የሚሆነው፡፡ ባለአደራ ማለት ለጊዜው ስልጣኑ በሚመለከታቸው የፖለቲካ ቡድኖች እስከሚያዝ ድረስ ሀገር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ስለሆነች፣ የጦር ኃይሉ ባለበት ሆኖ የሲቪል አስተዳደሩ በባለአደራው ይተካል ማለት ነው። በ1 ዓመት ተኩል ጊዜ ውስጥ ነፃ ምርጫ ቦርድ፣ የሰብአዊ መብት ተቋማት፣ ነፃ ሚዲያ፣ ነፃ የፖለቲካ ቡድኖች … ይቋቋሙና ሥልጣኑን በምርጫ አሸናፊ ለሆነ ቡድን ያስረክባል ማለት ነው፡፡
ኢህአዴግ ስር ነቀል ህዳሴ አደርጋለሁ፤ ችግሮችንም እፈታለሁ ብሏል፡፡ ይሄንንስ እንዴት ያዩታል?
አሁን ባለው ሁኔታ ሚኒስትር በማባረርና በመሾም የሚለወጥ ነገር የለም፡፡ ጥያቄው መረር ያለ ነው፡፡ ኢህአዴግ በባህሪው የሚታደስ ድርጅት አይደለም፡፡ የመድብለ ፓርቲ ስርአትን በሙሉ ልቡ የተቀበለ ድርጅት ስላልሆነ አይታደስም፡፡ ማዕከላዊነት የበዛበት፣ ተቀናቃኞቹን እንደ ጠላት የሚቆጥር፣ ጠንከር ያሉ ትችቶች የሚያቀርቡ ሚዲያዎችን የዘጋ … ስለሆነ እነዚህ ባህሪያቱ ለመሻሻል እድል አይሰጡትም፡፡ አንድ ስርአት ለመሻሻል ነጻ ሚዲያ፣ የሲቪል ተቋማት፣ ተቀናቃኝ የፖለቲካ ቡድኖች ነፃነት —- መኖር አለበት፡፡ ኢህአዴግ እነዚህ ስለሌሉት፣ተጠያቂነትን አስፍኖ ሊሻሻል የሚችል ድርጅት አይደለም፡፡
በአሁኑ ወቅት የተቃዋሚ ፓርቲዎች ሚና ምን መሆን አለበት?
እንደዚህ ባለ አስቸጋሪ ወቅት ያለውን ነባራዊ ሁኔታ፣ ለአለም ማህበረሰብና ለገዥው ፓርቲ ማሳወቅና መፍትሄውን ማመላከት ይጠበቅባቸዋል። ተቃዋሚዎች ሃሳብ ማፍለቅ አለባቸው፡፡ ህዝብ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች የፍልስፍና እና የአይዲኦሎጂ መልክ አስይዞ፣ ምን መሆን እንዳለበት የማመላከት ኃላፊነትም አለባቸው፡፡

 

30 Comments on “‹‹የባለ አደራ መንግስት መቋቋም አለበት›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት (የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር)”

  1. Mr Yilikal! Make no mistake. We know excellently who you are. You are worse than Lidetu Ayalew. We know who is manipulating you from behind. You are trying in vain to prolong and even make permanent the life of those who bought you. Your suggestion will never be accepted.Never!Never!Never!

    Aboma Mitiku

  2. Mr Yilikal! Make no mistake. We know excellently who you are. You are worse than Lidetu Ayalew. We know who is manipulating you from behind. You are trying in vain to prolong and even make permanent the life of those who bought you. Your suggestion will never be accepted.Never!Never!Never!

    Aboma Mitiku

  3. ኢ/ር ይልቃል ጌትነት pheew. why address him ኢ/ር instead of ‘Ato’?
    I find it very peculiar .
    If he is an engineer,why is he in politics?

    ዶ/ር መረራ and Ato ይልቃል seem to be immune from TPLF punishment. why are so many in TPLF prison for speaking their minds while these two are roaming free? very unusual.

    Man who scratches ass should not bite fingernails.

  4. Engineer ethiopia Wust selamawi tgl malethn akum ena sbseba lay bereket,abuhay sbu. Ena deber tsilun gidel abay tsihayn egnaw engelalen! Mognu desalegnn ena demekechn yemelesn kebr tebaki enketralen ok?

  5. The poor Yilqal I think is a sincere individual but who is deeply naive.
    I doubt if Merera is any different either.

    Both individuals do not seem to be fully aware of two things, at least.

    1. The treacherous nature of Woyane Tigres, the criminal traitors can never be reformed. Dealing with these murderers is like making a truce with a killer cobra.
    The brutes which burned and gunned down innocent prisoners in their custody, are simply beneath humanity. The Tigre killing squad that ordered a grieving mother to sit on her murdered son’s body and started assaulting her received its instructions from the highest authorities in the Woyane regime. Should any Ethiopian political party ever consider any discussion with the Nazis of the day? We leave it to Yilqal’s discretion.

    2. Complete lack of cognizance of the nature of Western governments.
    The countries which the two gentlemen visited are not oblivious to the
    atrocities Woyane TPLF has committed- from effectively helping Eritrea’s secession to the bantustanization of Ethiopia, a recipe to dismantle it.
    USA and Canada have been forefront in supporting a tribal regime of a tiny minority ethnic group representing at best 5% of Ethiopia’s population.
    They know damn well how they have virtually marginalized the preponderant majority of Ethiopians. They know how Tigres have disenfranchised the nation, how they plunder the nation. They are aware of how Tigres have established an apartheid system that has entitled them to appropriate whatever they wanted from annexing lands from Gondar and Wollo to thrusting a Tigre identity on reluctant others.
    In short, the Western nations have historically been on the wrong side of history as far as we are concerned. They have always betrayed us.
    Therefore, the very attempt at negotiating with Woyane, in itself is an affront to our sovereignty and a treasonable act on the part of Semayawi party and Dr, Merera. Keep away. Let Woyane fall by its own weight!!

  6. ኢንጅነር ይልቃል አገሪቱ ላለችበት ቀውስ ብቸኛ አማራጭ የሚለውን `የአደራ መንግስት መቋቋም` አጀንዳ ደግፈን አገሪቱ ከቀውስ መውጣት አለባት። ይህ ሳይሆን ቀርቶ ወያኔን በጥይት እናስወግዳለን ብለን ጦርነት ውስጥ ከገባን መተላለቅና አገር መፍረስ ይመጣል። አርቀን ማየት ይኖርብናል ይልቃልን እንደ ወያኔ ደጋፊ መፈረጅም ትክክል አይደለም።

    ይልቃልን ከልደቱ ጋር ማወዳደርም ትክክል አይደለም። ሁለቱም ወጣቶችና የሚያዋጣውን መንገድ የሚያዩ ባለራዕይ መሆናቸው ቢያመሳስላቸውም ኢንጅነር ይልቃል አሁን ላለንበት ቀውስ የሰላም ለውጥ የሚመጣበትን መንገድ ጠቋሚ ስለሆነ ልንደግፈው ይገባል። አሁን አገር ቤት ያሉት ተቃዋሚዎች የአደራ መንግስት ለማቋቋም የአገር ሽማግሌዎችንና ታዋቂ ግለሰቦችን መምረጥና ይህንን ኮሚቴ ለማቋቋም ስራ መጀመር ያለባቸው ጊዜ ነው። የወያኔ እውቅና መጠበቅ አያስፈልግም።

  7. ኣገር መምራት የሚችሉት እውቀት ያላችው ስወች ቢሆን ኣይከፍም ደንቆሮወችማ 25 አመት ኣስተዳዲረው መጨረሻው አሁን የምናየው ነው የሆነው!!!

  8. አክሊሉ ስዩም
    You make it sound as if Ethiopians are incapable of identifying the nature of their enemy.
    Do you trust woyane to agree with this proposal?
    Woyane has no intention of giving up power.

  9. Ke inzih seawoch izih US yalenew
    we know better about the fact on
    the ground. Indiet huno neaw EPRDF
    silxanun saylk sile Mengist silxan
    yemiyaweraw. Neaw weys Ye diaspora
    kededa yewedal bilo neaw ?

  10. ” Animal Mitiku. says: September 11, 2016 at 1:20 am

    Mr Yilikal! Make no mistake. We know excellently who you are. You are worse than Lidetu Ayalew. We know who is manipulating you from behind. You are trying in vain to prolong and even make permanent the life of those who bought you. Your suggestion will never be accepted.Never!Never!Never!

    Aboma Mitiku ”

    I see you think Yiliqal is bought by TPLF or its masters CIA ?

    CIA has by the way thousands of Ethiopian agents it bought at home and abroad.

    That the CIA (CIA = NAZI, white supremacist, jewish & catholic) is recruiting Ethiopian journalists and college professors means that it desperately wants to control the narrative about Ethiopia’s recent history and to prevent the larger Ethiopian public from knowing the truth.

    We should assume that that is one of CIA’s considerations regarding the protest movements that now threaten to overthrow a USA puppet regime that allowed the CIA to control what Ethiopians are thought in history in colleges. CIA is scared of the backlash of extremely destructive USA foreign policy towards Ethiopia and is in a damage control mood.

    We should start talking about the infestation of Ethiopian journalism and academia with CIA agents.

    And we should no longer tolerate CIA agent journalists and intellectuals to dumb down Ethiopian audiences by telling a false and pro-USA narrative about our recent history.

  11. @adanech
    አዳነች ስጋትሽ ይገባኛል። ወያኔ አሁን የሚደራደረው ለእራሱ ሲል ነው። አሁን ማንቁርቱን ተይዟል። የዘረፈውን ለመብላትና በሰላም ለመኖር በእርቅ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ሰጥቶ በመቀበል ክመደራደር ውጭ ምርጫ እንደሌለው ተገንዝቧል። ይህንንም ለመረዳት ነባር አመራሮች ከሚሰጡት መግለጫቸው መገንዘብ ይቻላል። ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ይታይባቸዋል።

    የሰላም መደራደር ካልተደረገ ግን ተያይዞ ማለቅና አገርን ማውደም አይቀርም፣ ወያኔ የመደረደር እድል ካልሰጠነው በጣም ራስ ወዳድ ስለሆነ አንዲት ጥይት እስክትቀረው ድረስ አደጋ ማድረሱ አይቀርም። በመቶ ሽህ የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ሰውተን ነጻ መውጣት ይሻለናል ወይንስ በድርድር የሁላችንም የሆነች አገር ማትረፍ? ወያኔ ወታደሩን እንደያዘ መደረደር አደገኛ ነው የሚለውን አቋምሽን እኔም እጋራለሁ ግን ይህን ጥያቄ ለነ ኢንጅነር ይልቃል አቅርበን የአደራ መንግስትን ወያኔ በፈለገ ጊዜ በወታደር ኃይሉ እንደማያሰወግደው ምን ዋስትና ይሰጣል የሚለውን ጥያቄ መልስ ለማግኘት እንጣር።

  12. aboma…then why don’t you tell us what you know about young yilkal..we simply can’t trust your accusations without evidence…so this goes to all conspirators in future please give us evidence ….evidence…

  13. It is not difficult to guess what the ferenjis want when they see the nearing of the collapse of their puppet. They for example want that what they have done in Ethiopia the last 25 years and earlier (actually a horrible crime) to be viewed as something positive in post-TPLF era. For that reason, among others, they rather dont want Ethiopian patriots to replace TPLF, they prefer either tribalists or those who are not that much opposed to tribalism. That is why Meiad and Andinet were not invited to that meeting few weeks ago and why they want TPLF included in a transition government. All their efforts are to minimize the role of Ethiopian patriots as much as possible. The ferenjis hope also that that way, that means by minimizing the role of patriotic Ethiopians, they will be able to reduce the backlash against their horrible crimes in Ethiopia in the past 25 years as sponsors of TPLF.

    As someone said here:
    ” ከሁሉም በላይ ደግሞ ቅድሚያ የመቀመጫዬን እንዳለችው ዝንጀሮ የድርድሩ ዋና አላማ ቅድሚያ የኢትዮጵያን አንድነትና ህልውና አስጠብቆ ኢትዮጵያን እንደ ዩጎዝላቭያ ሶማሊያ ኢራቅ ሊቢያ ሶርያ ከመፈራረስና ከሌላ ቀጣይ የእርስ በርስ ጦርነት የሚታደግና ይህች ታሪካዊ ሀገር እንደ ሀገር መቀጠል የምትችልበትን መፍትሄ የሚያመጣ መሆን አለበት፡፡ዋናው አትኩሮት ሊሰጠው የሚገባው ኢትዮጵያን ማዳን ላይ መሆን አለበት፡፡ ”

    our interest is of course to ensure the continued existence of the historical African country.

    To ensure the ancient African country’s survival what needed is to abolish tribalism, killilism, §39 and ban writing tribal name on IDs, something Rwanda did after the experience of the genocide. The tribal names Hutu and Tutsi were introduced by Germans as divide and rule tactic during colonialism and were kept after independence.

  14. What do we really value most? Ether the ruling party or the people of Ethiopia barely live a life. Life is only meaningful in the absence of fear and animosity, with harmony,mutual respect, triquelity, personal and social responsibility.
    Accountable politicians (parties) and democratic political order is essentual.
    Obviously,the Ethiopian people believe, the current political practice in breach of the trust of the people has become wildly corrupt and selfish.
    More over the ruling party promised so many times to take measures correcting the wrong practices. A Penney of promise is not fulfilled. Rather the problems kept rolling up. Ether deliberate or negligence is self destructive. That is what we are seeing right now.
    Ether moving out Tegray orgin or inviting the Somalian region for help is childish tactic of disinformation. Pls do not undermine and degrade the intellegence of the Ethiopian people. At least try to make it subtle and politically professional.
    Personally, I wish The politicians wised up and concentrated on reform and peaceful change.

  15. You know what, this is the plan of the Anglo-Americans, the jews and the CIA to be able to influence Ethiopian policy after their puppet TPLF is gone. But they will not succeed.

    Read below an example where the USA for the first time applied the “doctrine of odious debt” on Spain.

    Quote:

    “Excellent article, as usual, by Dr. Roberts. With reference to Correas repudiation of the foreign debt he refers to, President Correa determined it not to belong to the people of Ecuador, under the doctrine of odious debt having been contracted by pre-existing illegitimate dictatorial regimes. Gee, I wonder who thought THAT one up ? (Turns out, it was the good ol US of A). The US went to war in 1898, on the basis of pretext to get the American population aroused (where have we seen THAT form of behavior before ?) with the battle cry Remember the Maine (a US battle ship which had managed to blow itself up (coal dust) in Havana Harbor). After Spain lost, and the US took over Cuba (and Puerto Rico and the Philippines), Spain claimed that the US owed Spain all the money which Cuba owed to Spain. The US repudiated the debt claiming that it was odious debt incurred by the oppressive government Spain had put in place. So now, a hundred years later, the New York banks squawk when somebody claims the same rationale. (Just a thought. Just maybe a good part of the US National Debt is odious debt. Like, maybe, half. You think ?) .”

    In international law, odious debt, also known as illegitimate debt, is a legal theory that holds that the national debt incurred by a regime for purposes that do not serve the best interests of the nation, should not be enforceable. Such debts are, thus, considered by this doctrine to be personal debts of the regime that incurred them and not debts of the state. In some respects, the concept is analogous to the invalidity of contracts signed under coercion.

    The doctrine was formalized in a 1927 treatise by Alexander Nahum Sack,[1] a Russian émigré legal theorist, based upon 19th-century precedents including Mexico’s repudiation of debts incurred by Emperor Maximilian’s regime, and the denial by the United States of Cuban liability for debts incurred by the Spanish colonial regime.

    According to Sack:

    When a despotic regime contracts a debt, not for the needs or in the interests of the state, but rather to strengthen itself, to suppress a popular insurrection, etc, this debt is odious for the people of the entire state. This debt does not bind the nation; it is a debt of the regime, a personal debt contracted by the ruler, and consequently it falls with the demise of the regime. The reason why these odious debts cannot attach to the territory of the state is that they do not fulfil one of the conditions determining the lawfulness of State debts, namely that State debts must be incurred, and the proceeds used, for the needs and in the interests of the State. Odious debts, contracted and utilised for purposes which, to the lenders’ knowledge, are contrary to the needs and the interests of the nation, are not binding on the nation – when it succeeds in overthrowing the government that contracted them – unless the debt is within the limits of real advantages that these debts might have afforded. The lenders have committed a hostile act against the people, they cannot expect a nation which has freed itself of a despotic regime to assume these odious debts, which are the personal debts of the ruler.

    Patricia Adams, executive director of Probe International (an environmental and public policy advocacy organisation in Canada), and author of Odious Debts: Loose Lending, Corruption, and the Third World’s Environmental Legacy, has stated that:

    by giving creditors an incentive to lend only for purposes that are transparent and of public benefit, future tyrants will lose their ability to finance their armies, and thus the war on terror and the cause of world peace will be better served.

  16. Old TPLF. They never change! I am reminded of the TPLF PAID cadres during the 2005 massacre of the Ethiopian youth by TPLF. They were protesting the rigged election.
    They were posing like one of us and blaming the west/Ferenjis for our current plight.They understand and know Repetitive tactics. It is a different ball game, if they will manage to deceive the west. Wiki leaks portrayed Meles as an insecure loner who hates being with more than 2 people. If the west knows that much, they are just trying to make us think that the west loves TPLF. Dead wrong. The west loves whoever wins. And in the war of TPLF vs The Ethioian people, guess who is a dead rat?

  17. Among ferenjis’ biggest demands on that transitional government is “the respect of international agreements and treaties signed by TPLF”.

    That would mean the recognition of odious debt and the landlocked status of the country, but it is in Ethiopian intetest to reject both.

  18. ወይ በአቃራጭ ስልጣን ላይ ቁጭ አገርን ማተዳደር ቢሮ ቁጭ ተብሎ እያቀላፋህ እንደማለም ቀላል አይደለም ደግሞ ኢ/ር ይልቃል ዶ/ር መራራ ነው አገር የሚመርዋት ወይስ አገር ሊበትንዋት ነው መንጠራራት ጥሩ አይደለም አቅምህ መገመት ብልጥነት ነው

  19. Read, USA is hated globally:

    ” Philippines leader Duterte is about to kick US troops out of country

    “We’ll never have peace”: Philippines leader Duterte wants to boot US troops out of country’s south

    Published time: 12 Sep, 2016 17:18

    The Philippines president says US troops “have to go” from the south of his country. He blames American soldiers for inflaming tensions with the local Muslim population, saying they would “never have peace” with a US military presence.
    Philippines President Rodrigo Duterte says he is opposed to US soldiers being stationed in the southern Mindanao region, recalling how American troops took part in a pacification plan against Muslim Filipinos going back over a century. He said that this has caused a long period of resentment from the minority Muslim population against a majority of Catholics in the south.

    “For as long as we stay with America, we will never have peace in that land,” Duterte said on Monday, as cited by the AP.

    He displayed some black and white photographs dating from the early 1900s that showed women and children that had been killed by US forces. ”

    https://www.rt.com/news/359104-philippines-usa-soldiers-leave/

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*