በኦሮሚያ የሚካሄደውን የግብይት እቀባ ኣድማ ተከትሎ ቄራዎች ድርጅት የበግ አቅርቦት እጥረት ገጥሞኛል ብሏል

በኦሮሚያ የሚካሄደውን የግብይት እቀባ ኣድማ ተከትሎ የአዲስ አበባ የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ለመጪዎቹ በዓላት የበግ አቅርቦት እጥረት ገጥሞኛል ፣ የበሬ ነገር ግን አያሰጋኝም ብሏል ለመጪዎቹ በዓላት የበግ አቅርቦት እጥረት ገጥሞኛል ፣ የበሬ ነገር ግን አያሰጋኝም ብሏል

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ለዘመን መለወጫ በዓል 2 ሺህ 500 በጐችን ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች ለማቅረብ ብወጥንም የበግ አቅርቦት እጥረት አጋጥሞኛል አለ፡፡ እስካሁን እጄ ውስጥ የገቡት በጐችም 7 መቶ ብቻ ናቸው ብሏል፡፡
የድርጅቱ ዳይሬክተር አቶ ንብረት በቃ ለሸገር እንደተናገሩት በዘመን መለወጫ በዓል የተለመደው በሰፊው በግ ማቅረብ ነው ይሁን እና በዚህ ዓመት የዘመን መለወጫና የአረፋ በዓል በአንድ ቀን ልዩነት በመዋላቸው ምክንያት የበግ አቅርቦት እጥረት አጋጥሞናል ብለዋል፡፡
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ለአረፋ በዓል ብቻ ለእስልምና እምነት ተከታዬች የቀረበለትን የ5 ሺህ በጐች እርድ ፈፅሞ ለማቅረብ በዝግጅት ላይ መሆኑንም ዳይሬክተሩ ጨምረው ተናግረዋል፡፡ለዘመን መለወጫ በዓል የተለመደው የበግ ሥጋ ቢሆንም የአቅርቦት እጥረት አጋጥሟል ያሉት ዳይሬክተሩ የበሬ አቅርቦት ችግር ግን ስለሌለ 2 ሺህ በሬዎች ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች መዘጋጀታቸውን ለሸገር ተናግረዋል፡፡
ትዕግስት ዘሪሁን
@ShegerFM