ባህር ዳር ተቃውሞ እያሰሙ ነው።
ባህር ዳር ተቃውሞ እያሰሙ ነው።
#Ethiopia #Amharaprotests #Bahrdar #MinilikSalsawi
በባህርዳር ያለፈውን ተቃውሞ ተከትሎ እስከ 5000 የሚደርሱ ከዘጠኝ አመት ታዳጊ ህፃን እስከ 80ዎቹ አባት እና እናት የታሰሩበት ባህር ዳር ዛሬ ማለዳውን በአባይ ማዶ ከዲዛይን እና ቁጥጥር አባ ማዶ መጋዝን የታሸጉ ንፁህ ዜጎችን ወደ ብር ሸለቆ ወያኔ ለመጫን ያደረገውን ጥረት ተከትሎ ነው፡፡
ህዛባዊ እሪታ እና እለቅሶ የአባይን ድልድይ ዘግቶት ያረፈደው በአሁኑ ስዓት ወጣቶች ከፊታቸው የተደቀነውን መሳሪያ ሳይፈሩ እናቶች የቀድሞው ክልል ም/ቤትን እየዞሩ ተቃውሞ እያሰሙ ነው። በእስር ላይ የሚገኙ ንፁሐን ዜጎችን ወደ ብር ሸለቆ መንግስት ለመውሰድ እና በዚያም የማስቀየት እርምጃውን ለመቀጠል በማሰብ በምክር የሚለቃቸውንም እራሳቸውን በመላጨት ከዚህ በኃላ ዳግመኛ በህዝባዊ አመፅ ቢገኙ ሊረሸኑ እያሰፈረመ እየለቀቀቻው ነው፡፡
የከፍተኛ አመፅ አካል ናቸው ያላቸውን በቀን አንድ ዳቦ እና ሁለት ዳቦ በማቅረብ ፤ በርሃብ እዚያ እየበሉ፤ እየተፀዳዱ፤ እየተኙ ሞራላዊ ስብራት በማድረስ አመፁን ለማብረድ ከፍተኛ ጥረት እያደረገው ነው፡፡
አምላኬ ከፈሪ ዱላ ጠብቀን፡እንዴት ቢፈሩ ነወ ጃል ይሕን ያህል ጭካኒ፡
any kind of atrocities never stop victory! !
ጥብቅ ማሳሰቢያ፣
ከተከዜ ምላሽ ሁል ጊዜም ጎንደር እንጂ አንድም ሚሊ ሜትር መሬት የትግራይ ግዛት ሆኖ አያውቅም፣ በአሁኑም ወቅት ወራሪ እንጂ ህጋዊ አይደለም፣ ወደፊትም አይኖርም፡፡ ስለወልቃይት ቦታውን በወረራ መልክ በጉልበት የያዘ መራሹ የትግራይ ክልል ይፍረድ ማለት ወንጀለኛ ራሱ ከሳሽ፣ ተከሳሽ፣ መስካሪ፣ ታዛቢና ዳኛ ሆኖ በራሱ ላይ ይፍረድ ማለት ነው፡፡ የዚህ አይነት አሰራር ደግሞ የትም የሚከሰት ሳይሆን በወያኔ ትግሬ ኢትዮጲያ ብቻ ነው፡፡
ለማንም ግልፅ መሆን ያለበት ግን ከተከዜ ምላሽ ሁሉም መሬት የጎንደር ግዛት ስለመሆኑ በተከዜ ወንዝ አማካኝነት ከጥንት ጀምሮ ድንበሩ የተከለለ ስለሆነ ይህን ተፈጥሯዊ ድንበር ማንም ያውራ ወይም ይፍረድ በምን መንገድ ሊሽረው አይችልም፡፡ እንኳን ትግሬ ቀርቶ ማንም ታላቅ ወራሪ ይምጣ የአማራ ህዝብ ግን ይህን ጥንታዊ ሀብቱንና ታሪኩን በአሸናፊነት ሁል ጊዜም ያስጠብቃል፡፡ በዚህ ማንም መጠራጠር የለበትም፡፡
የዛሬ 20 አመት አካባቢ ወንዝ ተሻግሮ በመምጣት በጉልበት ይዞ በህገወጥ መንገድ የትግራይ ክልል ነው እሱ ስላለ ብቻ ቦታው ሆኗል ብሎ የሚያስብ ካለ ትልቅ ችግር በራሱ ላይ ያለበት ነው፡፡ ወያኔ ግን ያለው አማራጪ አንድ ሲሆን ይህም ስላለፈው ይቅርታ ጠይቆ የወረረውን ቦታ በአስቸኳይ በሰላም መልቀቅ ነው፡፡ ሌላ መንገድ የሚፈልግ ከሆነ ደግሞ ታላቅና ጀግና የአማራ ህዝብ እንኳን የራሱን ቤት ቀርቶ የትግሬንም ተራራ አድዋ ላይ ከሌሎች ህዝቦች ጋር በመሆን ከትልቅ ወራሪ ጋር ተፋልሞ ነፃ ያወጣ ነው፡፡ አማራ ቆሞ እሰከሄደ ድረስ በምን መንገድ ትግራይ ተከዜን ተሻገሮ በጎንደር ግዛት ላይ የቦታ ይገባኛል ጥያቄ ማንሳት ቀርቶ ማሰብም አይችልም፡፡
በመሆኑም ሁሉም ጎንደሬና የአማራ ህዝብ በሙሉ ይህን ጉዳይ በተመለከተ አቋሙ አንድ ሲሆን የትግራይ ክልል ይበሉት ወይም በሌላ ስሙ ፌደሬሽን ነገር ግን ወልቃይትን በተመለከተ የአማራ ህዝብ የማንንም ፍርድ አይጠይቅም፤ አይጠብቅምም፡፡ ቦታው ምን ጊዜምና ሙሉ በሙሉ የጎንደር ተፈጥሯዊና ታሪካዊ አካል ነው፡፡
“ጠንከር ባለ አገላለጽ የወልቃይት ጠገዴ፤ ጠለምት፤ ቃፍቲያ እና ሁመራ ተከዜ ደንበራችን ነው የሚለው የጎንደር ሕዝብ ጥያቄ ለድርድር የማይቀርብ የማንነት እና የመብት ጥያቄ መሆኑን ተገንዝቦ ጥያቄውን ከግቡ ለማድረስ ጎንደር ህብረት የትግል ቃል ኪዳኑን አድሷል።”
ይህ ለማስጠበቅ የአማራ ህዝብ ከዳር እስከዳርና ከሀገር እስከ ውጪ ሀገር ከሚፈለገው በላይ ዝግጁ ነው፡፡ ወንዝ ተሻግሮ በመምጣት በወረራ መልከ ስለያዘው በጣም ለም፣ ሰፊና ሀብታም የጎንደር ታሪካዊ መሬት እንዴት ወራሪ የሆነ ትግሬ ሊወስን ይችላል፡፡ በሰላም የማይመልስ ከሆነ አማራ የራሱን መሬት በጉልበት ለማሰመለስ ህግ የሚደግፈውና ትልቅ አቅም ያለው መሆኑን ግን አስቀድመው ሊያውቁት ይገባል፡፡
አንድ ጠገዴ ብቻ ያለ ሲሆን ይህም ሙሉ በሙሉ የጎንደር አካል እንጂ ከምን የመጣ ፀገዴ ነው ደሞ፡፡ የፈለጋቸውን ቢያቦኩና ቢፈተፍቱ ትግራይ ግን ተከዜን መሻገር አይችልም፡፡
አንብቡት፣
“በወልቃይት ጉዳይ የትግራይ ክልል ውሳኔ አርኪ ካልሆነ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ለማቅረብ ስምምነት መደረሱ ተገለጸ
የኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ጉዳይ ከአማራ ክልል ውጪ የትም አይታይም›› አቶ ገዱ አንዳርጋቸው
በአማራ ብሔራዊ ክልል አብዛኛዎቹን የጎንደርና የጎጃም አካባቢዎችን ለተቃውሞ ያነሳሳውና ለበርካቶች ሕይወት ማለፍ መነሻ ምክንያት የሆነውን የወልቃይት የማንነት ጉዳይ በተመለከተ፣ የትግራይ ክልል ምክር ቤት ተወያይቶ የሚያሳልፈው ውጤት እንደሚጠበቅ የአማራ ክልል መንግሥት አስታወቀ፡፡ ለዚህም ስምምነት ላይ መደረሱ ተገለጸ፡፡
የጠገዴንና የፀገዴን ድንበር ሁለቱ ክልሎች ተነጋግረው በአጭር ጊዜ ይፈቱታል ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ አስታውቀዋል፡፡ ነገር ግን የክልሉ ምክር ቤት (የትግራይ) የመጨረሻ ውሳኔ ሕዝብን ካላረካ ወደ ፌዴራል መንግሥት ተወስዶ በፌዴሬሽን ምክር ቤት ይታያልም ሲሉ፣ በተለይ በጎንደር ከተማ ለሚኖሩ የላይ አርማጭሆ ወረዳ ተወላጆች ገልጸውላቸዋል፡፡”
ተከዜን ተሻግሮ ትግራይ አንድም ሚሊሜትር የመሬት ባለመብትነት በፍፀም የለውም፣ አይኖረውም፣ ሊኖረውም አይችልም፡፡ ይህ የሆነ እለት የአማራ ህዝብ ሊወጣበት ከማይችል ጉድጓድ ለዘላለም የሚገባና መጥፊያውን በራሱ ፈቃድ አመቻቸ ማለት ነው፡፡ ትግራይን ከወንዙ ባሻገር በርቀት እንጂ በቅርበት ከሆነ ግን እሳትን መጨበጥና በራሰ ቤት ለኩሶ ከዜያው እንደመኖር ማለት ነው፡፡
ይህ በምን መንገድ መሆን የለበትም፡፡ ትግራይ ከተከዜ ማዶ ብቻ ነው ቦታው፡፡ ይህ ለሁሉም የአማራ ህዝብ ግልፅ ሲሆን ይህን በተመለከተ ማንኛውም ውሳኔ የሁሉም አማራ መሆን አለበት እንጂ ማንም የወያኔ ተላላኪ ባንዳ በዚህ ጉዳይ ላይ በግል ወይም በቡድን አያገባውም፡፡ አማራ ተጠንቀቅ፡፡ ትግሬ እንጂ ትግራይ ግን በፍፁም ተከዜን መሻገር የለበትም፡፡ ለዚህም አላማ ነው ያን ያህል ወጣት፣ ህፃናት፣ እናቶችና አባቶች በወያኔ አጋዚ ጦር በአማራነታቸው ሰሞኑን ሊጨፈጨፉ የቻሉ፡፡ ከዚህ የከፋ መስዋዕት ይከፈላል አንጂ ትግራይ ግን በፍፁም ተከዜን ተሻግሮ አንድም ሚሊሜትር ብትሆን የቦታ ባለቤት መሆን አይችልም፡፡ እነሱን በርቀት ማሰቆም ነው፡፡
የከተማውን ሰው አስረውም ገለውም አይጨርሱትም።ትግሉ መቀጠል አለበት።የታሰሩት ወደ ማሰቃያ ቦታ እንዳይሄዱ ህዝቡ መታገል አለበት።ኢህአዴግ በሚዲያዎቹ ስለ ሰላም እየሰበከ ውስጥ ለውስጥ እንደለመደው ለማሰቃየት በተቃውሞ ግዜ ያፈሳቸውን ወደ ማሰቃያ ካምፕ መውሰዱ ይታወቃል።በካምፑ ሁሉንም በሰፈር በሰፈራቸው ከመደብ በኋላ የአውጣጪን ስራ በመርማሪዎች ያከናውናል።እዚያ ቦታ ላይ ያሉትን በመጀመሪያ በማግባባት ይቀርባሉ፤በሂደት ጠበቅ በማድረግና ጨከን ብለው ምርመራ ያካሂዳሉ።ይህ በሚሆንበት ግዜ ምርመራው የሚካሄድባቸው ወገኖች ምግብ ፣ማረፊያ…..ወዘተ መከራ ሆኖባቸው ራሳቸውን እስኪጠሉ ድረስ ስቃይ ይቀበላሉ።ከማጣራቱ ስራ በኋላ በአፋቸው ጤፍ የሚቆሉ ካድሬዎች መጥተው የኢህአዴግን መልካም ስራ ይሰብካሉ።ታሳሪው ከዛ የመከራ ቦታ ለመውጣት ሁሉን አሜን ብሎ ይቀበላል።ኢህአዴግ ወሬ ሊያቀብሉት የሚችሉትን በምስጢር ይመለምላል።በውስጣቸውም ያሰማራል።ሲፈቱም ትንሽ ገንዘብ ጣል እያደረገላቸው ይጠቅምባቸዋል።እንግዲህ ይህን ለማድረግ ያመቸው ዘንድ ንፁሃንን ወደ ማጎሪያ ይወስዳል።ይህ መፍትሄ እንደማይሆን ይታወቃል።ህዝቡ የሚለውና ተቃውሞ እያሰማ ያለበት ጉዳይ “ኢህአዴግ በቃህ!”ነው።ይህን ደግሞ እነሱም ያውቃሉ።የተነቃነቀ ጥርስ መውለቁ አይቀርም።ኢህአዴግ ያልሞት ባይ ተጋዳይነት እንቅስቃሴ ላይ ነው።ህዝባችንም ይህን አውቆ ትግሉን አጥብቆ መቀጠል አለበት።