በህዝቦች ትግል ያልተገኘ ነጻነት ለአምባገነኖች ባርነት ይዳርገናል::የኢትዮጵያውያን የነጻነት ትግል እና የምእራባውያን ሚና (ምንሊክ ሳልሳዊ) ‪

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – አንድ ሁለት ሶስት …እርምጃዎች በትግሉ አለም ውስጥ አንድ ፈር የሚቀድ የድል ዋዜማ ስኬት መሆኑን አጠያያቂ አይደለም::ማንኛውም የመብት እና የነጻነት ጥያቄዎችን መፍታት የሚቻለው በእኛ በራሳችን መሆኑ እሙን ነው::ለኛ መብት መከበር ለኛ ነጻነት መቀዳጀት ቅጥረኞችን አንገዛም::በራሳችን በህዝቦች ያልተገኘ ነጻነት በድንቡሸት ላይ የተገነባ ስለሚሆን ፈራሽ ከመሆኑም በላይ ለአምባገነኖች ባርነት ይዳርገናል::‪#‎Attention‬=ምእራባውያኑ የመጀመሪያ እርከን የሆነውን የመግባቢያ ምስጢራዊ ድርድር ኣስጀምረዋል።

ኢትዮጵያውያን ለነጻነታችን ዋጋ መክፈል የጀመርነው ከጥንት ጀምሮ መሆኑ ይታወቃል::በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ተንሰራፍቶ የሚገኘው የዘረኛ ቡድናዊ አገዛዝ በዜጎች ላይ ከፍተኛ በደል በማድረስ ላይ ይገኛል::ከዚህ ጨቋኝ አገዛዝ ለመገላገል ለነጻነታችን መታገል ያለብን እኛው ራሳችን እንጂ ምእራባውያን አይደሉም::ምእራባውያን ብሄራዊ ጥቅማቸውን የሚያስከብርላቸው ማንኛውም አስተዳደር ከመደገፍ እና ከማባበል ወደኋላ አይሉም::አምባገነኖች በምእራባውያን እየተረዱ በዜጎቻቸው ላይ የሚያደርሱት በደል እና ሰቆቃን ለመቃወም ከወረቀት ያልዘለለ ተግባር በለጋሽ አገሮች ሲፈጸም አልታየም::ለዚህ ጭቆና ችግሩም መፍትሄዉን የተጨቆነው ማህበረሰብ እንደሆነ ማወቅ ግድ ይላል::ነጻነቱን ለማግኘት የሚታገለው ጭቁን ሕዝብ በትግሉ ገፍቶ ሲራመድ ምእራባውያን ከአምባገነኖች ወደ ነጻነት ታጋዮች ፊታቸውን እንዲያዞሩ ይገደዳሉ::ለለጋሽ አገሮች ቅርብ የሆኑ ዲፕሎማቶች ተቃዋሚዎች ያላቸውን ሃይል አሰባስበው በተገኘው መንገድ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እስካላደረጉ ድረስ በውጪም በውስጥም ያሉትን ለመርዳት እና ለማበረታታት ከብሄራዊ ጥቅም አንጻር እንደማይቻል ከዚህ ቀደም አስረግጠው ተናግረዋል::

ምእራባውያኑ ከአፍ ወሬ ውጪ ምንም የሚተገብሩት ነገር የለም ፡ በእስር ቤት ያሉ የፖለቲካ እና የህሊና እስረኞች በቂ ምሳሌ ሊሆኑ ይችላል ከሰብአዊ መብት ድርጅቶች ጀምሮ እስከ አሜሪካው የውጪ ጉዳይ ሚ/ር ድረስ ድምጻቸውን ቢያሰሙም ለይስሙላ እና ለብሄራዊ ጥቅማቸው እንዲሁም ነገ ሌላ መንግስት ቢተካ እንዲህ ብለው ነበር እንዲባልላቸው እና እዳ ማውረጃ ንግግራቸው ለትግሉ ምንምየሚፈይደው ነገር የለም።በእስር ለሚማቅቁት ወገኖቻችን የሚፈይደው ዋናውና አንዱ ጉዳይ የኛ ጠንክረን መታገል እና አንድ እርምጃ መጓዝ ሲሆን የዛን ሰአት የኛን መጠናከር እና መታገል የተመለከቱ ምእራባውያን ምን እንርዳችሁ ከምን ደረሳችሁ ምናምን ማለታቸው እና መጠየቃቸው ግድ የሚልበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም ፡፤ አሁን የሚፈለገው የኛ መታገል እና መታገል ብቻ ነው። የነጮቹ የከንፈር ልብላቤ ከብሄራዊ ጥቅም ሚዛን ሂደት ምስረታ ላይ ስለተመረኮዘ ከንግግር ውጪ ምንም አይፈይድም::

ከማእከላዊ አፍሪካ እስከ አፍጋኒስታን ከሶርያ እስከ ኢራቅ በተለያዩ የአፍሪካ እና የመካከለኛው እንዲሁም የኢስያ ሃገራት ም እራባውያኑ የሚያካሂዱት የፕሮክሲ ጦርነት የተነሳ ሌላ ዙር ቀውስ በምስራቅ አፍሪካ እና ውጥረት እንዲከሰት ስለማይፈልጉ ከወያኔ ጋር እጅና ጓንት ሆነው ለመስራት አለመቦዘናቸው የሚያመለክተው እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሃገራት ላይ በአሁኑ ሰአት ሊፈጠር የሚችለውን አመጽ እና ችግር መቆጣጠር ይዞ የሚመጣውን ውጤት እርግጠኛ ሆነው ለማወቅ አለመቻላቸው ከወያኔ ጋር እንዲተሳሰሩ አድርጓቸዋል።እንዲሁም ደቡብ ሶማሊያ ላይ ነዳጅ መኖሩን ስካን አድርገው ስላረጋገጡ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ25 አመት በኋላ እንግሊዝ ኤምባሲዋን ሞቃዲሾ የከፈተች ሲሆን ይህን ተከትሎ ከ100 በላይ የብሪታንያ ካምፓኒዎች ካልተረጋጋችው ሶማሊያ ፍቃድ እንደተሰጣቸው ለማረጋገጥ ተችሏል። ይህንን ከሶማሊያ ሊያገኙትን ብሄራዊ ጥቅም ሊያስጠብቅ የሚችለው አገር ቢኖር ወታደሮቹን ለሞት እየገበረ የሚተባበራቸው የወያኔው መንግስት ብቻ ስለሆነ ያላቸውን ሃይል ሁሉ በመጠቀም ሕዝብን በዲፕሎማሲያዊ ቋንቋ በመደለል የአምባገነኖች እድሜ እንዲረዝም ሚናቸውን ይጫወታሉ።

እንዲሁም ታጥቀናል እንዋጋለን ስለሚሉ ድርጅቶች እንቅስቃሴ በቂ መረጃ ስለሌላቸው እንዲሁም እነሱ የማይደግፉት እና የማይቆጣጠሩት አመጽ ላይ ሪስክ/ሃላፊነት ስለማይወስዱ የሚያደርጉል አስታውጾ አነስተኛ ሲሆን እኛ ታግለን አንድደርምጃ ወደፊት እስካልሄድን ድረስ እና ትግላችንን አሳይደን የድጋፍ እና የቁጥጥር ሰንሰሎችን ከም እራባውያን ጋር እስካልፈጠርን ድረስ በመግለጫ እና ድህረገጽ ወሬ ጋጋታ ምንም የምናመጣው ነገር እንዳሌለ ለመናገር እወዳለሁ፡፤ ዋናው ቁም ነገሩ ግን ጠንክረን የዲፕሎማሲውን እና የትጥቁን ትግል እና የሃገር ቤቱን ሕዝባዊ እምቢተኝነቱ ከየኣቅጣጫው የፈጠረውን ንቅናቄ ትግል ከያዝነው ወያኔ ፈንግሎ ለመጣል በፍጹም ኣይቸግርም።

ብቸኛው እና ዋናው ጉዳይ ትግሉ\ጦርነቱ በመሃል እና በዳር አገር ከተፋፋመ ፣ ሕወሓት እና አመራሩ አደጋ ውስጥ መግባት ሲለጀመሩ ምእራባውያኑ በሌላው አለም እንደለመዱት ድርድር መግባባት ጉባዬ ወዘተ የሚባለዉን እንደ ጆከር ካርድ ስለጀመሩ መግባባት በማለት የመጀመሪያ እርከን የሆነውን የመግባቢያ ምስጢራዊ ድርድር ኣስጀምረዋል።

ወያኔ ያሰራቸውን የፖለቲካ እና የህሊና እስረኞች የተወሰኑትን እንዲፈታ ተደርጎ ድርድር እንዲጀመር ያደርጋሉ ከዚህ ውጭ ግን የሃይል ሚዛኑ በወያኔ እጅ ባለበት የመንግስትን ወንበር ተቃዋሚዎች ባላዩበት ሁኔታ ምእራባውያኑ የሚያሰሉት ከወያኔ ጋር ያላቸውን ቁርኝት ነው። ይህንን ለመበጠስ ደሞ የግዴታ የተኩስ ትግል መጀመር አለበት ። ወያኔም ቢሆን የትጥቅ ትግሉ በመሃል አገር እና በዳር አገር ሲስፋፋበት ጭንቀት ውስጥ ስለሚገባ ከአጣብቂኙ ለመውጣት ሲል ያለውን አማራጭ ለመጠቀም ይሞክራል። ወያኔ ደጋፊዎቹን እና ካድሬዎቹን በጥቅም ስለገዛቸው ጦርነት ከተስፋፋበት ያለውን ሃይል ሁሉ ወደ ዛው ስለሚያጋድለው ለካድሪዎቹ ጥቅሞች ጊዜ ስለማይኖረው አብዮታዊ መበላላት በፓርቲው ውስጥ ስለሚፈጠር እድሜውን ማቀጨጭ ከዛም መጣል ይቻላል። ጠንክረን በሃገራዊ የጋራ አጀንዳችን እና የህዝብን ነጻነት በማረጋገጥ ላይ አስረግጠን መታገል ካልቻልን ባሁኑ በተገኘው ነገር ላይ ሁሉ ተስፋ በመጣል አካሄዳችን ወያኔን እንድማንጥለው ማወቅ አለብን። ምእራባውያኑም የኛን መጠናከር ሲያዩ የዛኔ ይፈልጉናል፥፤አትኩሮታችንን ሁሉ በትግሉ ላይ የማድረግ ግዴታ አለብን። ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

Image may contain: text

11 Comments on “በህዝቦች ትግል ያልተገኘ ነጻነት ለአምባገነኖች ባርነት ይዳርገናል::የኢትዮጵያውያን የነጻነት ትግል እና የምእራባውያን ሚና (ምንሊክ ሳልሳዊ) ‪”

  1. Woyanes may receive ‘advice’ from their handlers to engage the ” opposition” as if the whole nation is not at war with the enemy, TPLF..

    The Woyane terrorist outfit has had an unwavering support of the major Western powers from their very inception. It usurped power in a country which the TPLF had denied to have been part of.

    The Ethiopian people will not trust any mediation, much less from those which had installed the avowed an anti-Ethiopian ethnic group that represents some 5% of Ethiopia’s population.

    Would any nation ever consider another government legitimate, if the latter vociferously ceded an integral part of its own territory to another entity?

    Ethiopia’s current government just did that. The Tigre invasion force that has not only given away Eritrea but also decided to make land-locked, however has been the darling of the west as well as the East regardless of the horrendous destruction it wrought on one of the oldest nation states. The TPLF mercenary outfit sacrificed the sovereignty of one hindered million Ethiopians with the connivance of its foreign handlers. Woyane is our problem. Let foreigners stay away.!!

  2. I have yet to read the article, but i like the title. The likes of ESAT and many learned Ethiopians based in the USA and the West are very much afraid to blame the USA & co., which is wrong.

    We live at a time when even ferenjis accuse their own governments.

    Ethiopian so-called intellectuals need to wake up, more importantly, they should not dumb down Ethiopian audiences in the interests of ferenjis, say by saying: “ferenjoch ityopyan yiwedalu”. Let alone their support for TPLF, even their siwir tsere ityopyawiyan zemecha in their lands (like siccing a dog[their population] on pedestrian [Ethiopian immigrants]) shows that they hate and fight Ethiopia.

    Ferenji Americans accusing USA to be behind the crisis in Syria ==========> “… it (USA) has no choice but to accept that they have lost a war they directly and indirectly started through covert CIA operations that began in 2011 (and as some would argue, well before that). “

  3. Call the bastard ferenji countries by name according to their role,

    1. USA

    2. UK

    3. Germany

    4. Vatican

    .

    .

    .

  4. Why this =========> ” በራሳችን በህዝቦች ” ?

    Is the author tribalist or is that just habit ?

    Never trust the white devil ! ==========> ” ::#‎Attention
    =ምእራባውያኑ የመጀመሪያ እርከን የሆነውን የመግባቢያ ምስጢራዊ ድርድር ኣስጀምረዋል። ”

    These ferenji bastards should stop supporting, training, arming and protecting their slave TPLF. That is what is expected from them, not secret negotiations.

  5. The truth is they are parasite countries ========> ” ለጋሽ አገሮች ”

    CUDP was such a group but ferenjis did not support it, worse, they fought it ! ============> ” ለለጋሽ አገሮች ቅርብ የሆኑ ዲፕሎማቶች ተቃዋሚዎች ያላቸውን ሃይል አሰባስበው በተገኘው መንገድ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እስካላደረጉ ድረስ በውጪም በውስጥም ያሉትን ለመርዳት እና ለማበረታታት ከብሄራዊ ጥቅም አንጻር እንደማይቻል ከዚህ ቀደም አስረግጠው ተናግረዋል:: ”

    Bad influence from USA based Ethiopians ==========> ” የነጮቹ “

  6. crying for amhara or oromo is expired formula.the one who crys for all ethinic,respect all ethinic,love for all ethinic will get arespect &love from all ethinic &will be aleader of all ethinic to bring achange to all ethinic.this should be the new formul.in ever corner there is suffering due to lack of democraciy&bad governance.

  7. Ethiopia’s ethnic makeup
    1. Oromo – 34.4%
    2. Amhara – 27 %
    3. Somali – 6.2%
    4. Tigray – 6.1%
    5. Sidama – 4%
    Respect before too late and hand the power to the people.

  8. Nobody takes this trash seriously.

    1. In Ethiopia over 70% of Ethiopians come from 2 or more ethnic backgrounds, where are they in the statistics ?

    2. Until the Derg times there were more Amharas than Oromos, why is that different ?

    The statistics are as fake as woyanes’ double digit growth propaganda.

  9. Barking barking barking barking. You have been barking for 25 years and the CAMEL has been continuing his journey for 25 years. You will bark for another 25 years and the CAMEL is determined to walk for another 25 years. Stop hating and love all Ethiopians unconditionally. If not you will never achieve your goal.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*