በሕወሓት ኣሻንጉሊቱ ፕሬዚዳንት ሙላቱና የመኢአድ አመራሮች በወቅታዊ ችግሮች ዙሪያ ተወያዩ
በሕወሓት ኣሻንጉሊቱ ፕሬዚዳንት ሙላቱና የመኢአድ አመራሮች በወቅታዊ ችግሮች ዙሪያ ተወያዩ 
በሕወሓት ኣሻንጉሊቱ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ፤ በአማራና በኦሮሚያ ክልል በተፈጠሩ ተቃውሞዎችና ግጭቶች እንዲሁም በአዲስ አበባ ቤት በፈረሠባቸው ነዋሪዎች ጉዳይ ዙሪያ የመኢአድ አመራሮችን በቤተመንግስታቸው ጠርተው አነጋገሩ፡፡
የመላ ኢትዮጵያውያን አንድነት ድርጅት (መኢአድ) በቅርቡ ለ ኣሻንጉሊቱ ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ፣ ለጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሣለኝ፣ ለህዝብ ተወካዮችና ለፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ-ጉባኤዎች በፃፈው ደብዳቤ፤ በኦሮሚያና በአማራ ክልል በተፈጠሩ ተቃውሞዎችና ግጭቶች እንዲሁም በአዲስ አበባ ቤት በፈረሠባቸው ነዋሪዎች ጉዳይ ዙሪያ መንግስት ችግሩን መርምሮ አስቸኳይ መፍትሄ እንዲያበጅ መጠየቁ ይታወሳል፡፡
ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ፤ ለፓርቲው ማሳሰቢያዎች ፈጣን ምላሽ በመስጠት ደብዳቤው በደረሳቸው በ4ኛው ቀን ወደ ፓርቲው ፅ/ቤት ስልክ አስደውለው ለውይይት እንደጋብዟቸው የመኢአድ ፕሬዚዳንት ዶ/ር በዛብህ ደምሴ ለአዲስ አድማስ አስታውቀዋል፡፡
በተያዘላቸው ቀጠሮ መሠረትም የፓርቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር በዛብህ ደምሴና ተ/ም/ፕሬዚዳንት አቶ አሠፋ ሃብተወልድ፣ ከፕሬዚዳንቱ ጋር ለ1 ሰዓት ተኩል የቆየ ውይይት በቤተ መንግስት አድርገዋል፡፡
በውይይታቸውም በተለይ በአዲስ አበባ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ፣ ህገ ወጥ ተብለው የፈረሡ ቤቶች፤ ህገ ወጥ ናቸው ቢባሉ እንኳ ያለ በቂ ዝግጅትና ውይይት እንዲሁም በክረምት መፍረሳቸው አግባብ አለመሆኑን የፓርቲው አመራሮች እንዳነሱላቸው ጠቅሰው፤ ፕሬዚዳንቱም “ቤቶቹ በክረምት መፍረስ አልነበረባቸውም” ማለታቸውን አመልክተዋል፡፡ ‹‹እስካሁን በፈረሡት ላይ ምንም ማድረግ አይቻልም፤ በቀጣይ እንዲህ አይነቱ ድርጊት እንዲቆም ይደረጋል፤ ቤታቸው የፈረሠባቸውንም መንግስት የትም አይጥላቸውም›› የሚል በተስፋ የተሞላ ምላሽ ፕሬዚዳንቱ እንደሠጡ ዶ/ር በዛብህ ለአዲስ አድማስ አብራርተዋል፡፡
በአማራ ክልል በተለይ ከወልቃይት የማንነት ጥያቄ ጋር እንዲሁም በኦሮሚያ ከአዲስ አበባ ፊንፊኔ ዙሪያ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ የተቀሰቀሱ ተቃውሞና ግጭቶችን በተመለከተም ከፕሬዚዳንቱ ጋር ሰፊ ውይይት መደረጉ ተገልጿል፡፡
የፓርቲው አመራሮች በሁለቱ ክልሎች ያሉ ችግሮች በጥይትና በሃይል ሣይሆን በሠላማዊ መንገድ መፈታት እንዳለባቸው ያሳሰቡ ሲሆን ዶ/ር ሙላቱም ሀሳቡን እንደሚቀበሉና ችግሮች ሁሉ በውይይት መፈታት አለበት ብለው እንደሚያምኑ መግለፃቸውን ዶ/ር በዛብህ ለአዲስ አድማስ አስረድተዋል፡፡
በአንድ ወቅት የሰለጠነችና የተረጋጋች አገር የነበረችው ሶርያ፤ ችግሮቿን በውይይት ለመፍታት ባለመሞከሩ፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎቿ ለሞትና ለስደት መዳረጋቸው በእጅጉ እንደሚያሳዝናቸው የተናገሩት ዶ/ር ሙላቱ፤ በኢትዮጵያ የሚነሱ ማናቸውም የህዝብ ጥያቄዎች በውይይት በመግባባት መፈታት አለባቸው የሚል እምነት እንዳላቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡
“ከፕሬዚዳንቱ ጋር በጥሩ መግባባት ፍሬያማ ውይይት አድርገናል” ያሉት የመኢአድ ፕሬዚዳንት ዶ/ር በዛብህ፤ “በ25 ዓመት የፓርቲው ታሪክ ውስጥ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ድምፃችንን ሰምቶ “ኑ እንወያይ” በማለት ሲያነጋግረን የመጀመሪያችን ነው” ብለዋል፡፡
መኢአድ ለችግሮች ሁሉ መፍትሄው ሰላማዊ ውይይት ብቻ ነው ብሎ እንደሚያምን የተናገሩት ዶ/ር በዛብህ፤ ከፕሬዚዳንቱ ጋር ያደረግነው ውይይት በአገሪቱ የፖለቲካ መድረክ በጎ ጅማሮ የሚባል ነው ሲሉ አወድሰዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ ከገዥው ፓርቲም ከተቃዋሚዎችም ወገን ሳይሆኑ ሁሉንም አካላት በገለልተኛነት የማገልገል ግዴታ እንዳለባቸው በማስረዳት፤ በማንኛውም ጊዜ ለውይይት በራቸው ክፍት መሆኑን አረጋግጠውልናል ብለዋል- የመኢአድ ፕሬዚዳንት፡፡
መኢአድን ብቻ ሳይሆን ሁሉንም ተቃዋሚ ፓርቲዎች ፕሬዚዳንቱ በአንድ ላይ ሰብስበው በሀገሪቱ ችግሮች ላይ እንዲያወየዩ ጠይቀናል ያሉት ዶ/ር በዛብህ፤ ለጥያቄያችንም አዎንታዊ ምላሽ እንዳላቸው ተገንዝበናል ብለዋል፡፡
Bullshit what we need is a radical change not to buy weyane time. The only choice is to throw weyane for good.
Mead! !! lemada donkey! !
Ignore all the so called peaceful and legal parties They are good for nothing and are giving the TPLF legal cover for its crimes. This party will not have any thing by talking and appealing to the power less toy of the TPLF. People should continue the struggle.
ውሸቱን ነው አሁን ከላይም ከታችም ሲያስመልሰውና ሲያስቀምጠው ነው ሞላጫ ሌባ።
I agree, the only language the fascists understand is force. They violated
Ethiopia’s sovereignty violently. For a quarter of a century, they have committed the most unimaginable atrocities against Ethiopians.
What good is talking to these career criminal and terrorists? What needs to be pursued is the type of action our people in Gondar did. One determined soul can cause havoc in the enemy camp. Each one of us can injure the enemy in one way or an other. That is what needs to be done.
For disscusion no time and to late and with woyane what to get?
The only choice is every time, every where, none stop strugle. ..That makes woyane regime to die. Ethiopians then after may decide about their future. ..
Doronne Siataleluate……
Lool this tplf plastic toy is not capable of doing anything next time try to discuss this issue with his tplf boses
አይ መአኢአድ
እንኳን ሙላቱ ሃይለማርያም እንኳን ምንም ማድረግ አይችልም። የሙላቱና የመአኢአድ ውይይት አስቂኝ ማቀዝቀዣ ነው። ሙላቱ እንደ እቃ በቤተመንግስት መጋዘን የተቀመጠ ነው። ለመሸወድ ሲባል በል ተብሎ ካልሆነ በህግም በተግባርም ምንም ስልጣን የሊለው ጉልቻ ነው። ምናልባት እንደማቀዝቀዣ ቢያገለግል ብለው ተጠቅሙበት። መአኢአድም ማቀዝቀዣ ውስጥ ገባ። ለነገሩ መአኢአድ ለምን የመጀመሪያ ምርጫ ሆነ። እውነት ካለ አባይ አርከበ ሌላው አባይ ሰማያዊንና ኦፌደንን በኦፊሲኤል ጠርተው ያነጋግሩ›፡ ለነሱ እኮ ኢትዮጵያዊት ወላድ ብድርና እርዳታ ለማግኘት በስሟና በፎቶዋ ይጠቀማሉ እንጂ ደሳሳ ጎጆዋን አፍርሰው ለነሱ ” ጎልፍ ” መጫውጫቸው ሜዳን መስራት የሚአስቀድሙ ናቸው።
እንኳን ሙላቱ ጉ ል ቻ ው ሃይለማሪያም ሮ ቦ ቱ ም
ላማቀዝቀዝ እንጂ ውሳኔ አይሰጡም
ስ ል ጣ ን የ ላ ች ውም
አልነበ ራ ች ው ም
ወያኔ ኦሮሞንና አማራን መግደል ማባረር ህገ መንግስታዊ መብት አለው! አንድ የትግራይ የወያኔ አባል በስብሰባ ላይ የተናገረው ትክክል እየገደሉን ነው እስከ መቼ?
ቆሬ