አርብ ኦገስት 26/2016 በፍራንክፈርት ከተማ ታላቅ ትእይንተ ህዝብ ተዘጋጀ።
ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ የወያኔ መንግስት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚያደርሰውን ዘርፈ ብዙ በደሎች እንዲያቆምና ለህዝብ ጥያቄ አዎንታዊ ምላሽ እንዲሰጥ ለማስገደድ ብሎም በሀገር ቤት እየተደረገ ላለው ህዝባዊ እምቢተኝነት አጋርነታችንን ለመግለፅ አርብ ኦገስት 26/2016 በፍራንክፈርት ከተማ ታላቅ ትእይንተ ህዝብ ስላዘጋጀን በመላው ጀርመን የምትገኙ ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያዊነት መገለጫ የሆነውን ያልተበረዘ አረንጏዴ፣ ቢጫ እና ቀዩን ባንዲራ ይዛችሁ ቢቻል ጥቁር ልብስ በመልበስ እንድትገኙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን:: ሰልፉ የሚጀምርበት ሰዐት: -12:00 ሰልፉ የሚጠናቀቅበት ሰአት:-17:30 የሰልፉ መነሻ ቦታ:- ፍራንክፈርት ሀብት ቫኸ (Frankfurt Hauptwache) ሰልፉ የሚጠናቀቀው:-ኢትዮጵያ ኢምባሲ በር ላይ የሰልፉ አዘጋጆች:- በዲፒሀር ኢንተርቴይንመንት በጀርመን የኢትዮጵያ የባህል እና የሙዚቃ ማእከል እና በጀርመን የኢትዮጵያውያን የስደተኞች ምክር ቤት በጋራ ለበለጠ መረጃ:- +49 15785114566 +4915218504056 +4961032904352 ይደውሉ:: ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!!!
