በወያኔ ጥይት በግፍ የወደቁ ሰማዕትን ጎንደር ውስጥ ዛሬ ጧፍ በማብራት እያሰቧቸው ነው

ጀግኖቹ የጎንደር አማሮች የቤት ውስጥ ተቃውሟቸውን ጨርሰው በአሁኑ ሰዓት በወያኔ ጥይት በግፍ የወደቁ ሰማዕት ወንድምና እህቶቻቻችንን ጧፍ በማብራት እያሰቧቸው ነው። ግፈኛው የትግሬ ነጻ አውጪ ቡድንን ስናስወግድ ሰው ለማዳን ለወደቁት ሰማዕቶቻችን የክብር ሀውልት አቁመን በየእለቱ እንዘክራቸዋለን። – Achamyeleh Tamiru 

Gondar candle light vigil - August 17, 2016a
Gondar candle light vigil - August 17, 2016b

10 Comments on “በወያኔ ጥይት በግፍ የወደቁ ሰማዕትን ጎንደር ውስጥ ዛሬ ጧፍ በማብራት እያሰቧቸው ነው”

  1. ደማቸው እንደ አቤል ደም ይጮሃል ! እግዚአብሔርም ይሰማል ።ስጋቸው ቢለየንም ስራቸው ግን ህያው ሆኖ ይኖራል። ድል የህዝብ ነው !

  2. If we stop the demonstration then it means weyane wins and we are losers and people have killed for nothing as we didn’t achieve our goals to throw weyane from power.

  3. እውነት ነው ተወልደው ባደጉበት አገር በጥይት ተደብደዋል ለኛ ነፃነት የተሰውትን ሁሌም ልናስታውሳቸው ይገባል፡፡

  4. ትግሉ መቀጠል አለበት. ..አሸባሪው ወያኔ እንደለመደው በሽማግሌ ትከሻ መምጣቱ አይቀርም….የጀግኖች አማሮች ደም በከንቱ አይፈስም ለወደቁትም የትግሉ ሠማዕታት አውልት ሊሠራላቸው ይገባል

  5. የወያኔ ጨፍጫፊነት ዘረኝነት ሌባነት ልክስክስነት…..ወዘተ የታወቀ ነው።የጎንደር ህዝብ ቤት በመዋል ተቃውሞውን ማሳየቱ በፖለቲካ ሂሳብ ያስጨበጭባል።በወያኔ የገማ አስተሳሰብ ግን አብዛኛውን ህዝብ ደሃ ስላደረገው እንዲሁም ቀን ሰርቶ ባገኘው ነዋሪ እንደሆነ ስለሚያውቅ ሲርበው ከቤቱ ወጥቶ ስራውን ይጀምራል ብሎ ስለሚያምን ምንም አይመስለውም።ከዚህ በመቀጠል የ”ብዓዴን”ን የገቢ ምንጭ ከሆኑት አንዱ ከአባላት የሚሰበሰብ ወርሃዊ መዋጮ ስለሆነ ሁሉም አባላት ክፍያ ማቆምና ከአባልነት ራሳቸውን ማውጣት ባስቸኳይ ማከናወን አለባቸው።ዛሬውኑ!!!

  6. በመላው ኢትዮጵያ የምትገኙ የኢህአዴግ አባላት በየወሩ የምትከፍሉት ወርሃዊ መዋጮ የራስህን ወገን መግደያ መሆኑን እወቅ።ስለዚህ መዋጮህን አቁም ከአባልነትም ራስህን አውጣ!!!ይህ ባስቸኳይ መከናወን ያለበት ነው።ኢህአዴግ ገዳይ ነው።ለገዳይ አባል ከሆንክ አንተ ራስህ ገዳይ መሆንህን እወቅ።ስለዚህ ከአባልነትህ ውጣ!!! እያንዳንድህን ከአቃጣሪነት ራስህን አፅዳ!!!

  7. 1)ሻዕቢያዎች ይህ የኢትዮጵያውያን ጉዳይ ስለሆነ ዘወር በሉልን ። Mind ur miracle land Eritrea ,
    2) የንፁሁን ኦሮሞ ሥም እየተጠቀምክ ለሀጭህን የምታዝረከርከ ጀግናው “ጎንደሬ” ተብየ ልብህና ተንኮልህ በኢትዮጵያ ህዝብ የሚታወቅ ስለሆነ አትድከም። ኦሮሞ ሥነ ሥርዐት ያለዉ ጨዋ የሚናገረውንና የሚሠራውን የሚያውቅ ህዝብ ነው። በሥሜ አትነግድ ። ራስህን ቻል ።

  8. ምነው ጎበዝ ኣልበዛም እንዴ? ” ጀግኖቹ የገንደር ኣማሮች” ስትሉ ምን ማለት ነው? ጎንደሬ የሴት ሆቴል ስላቃጠለ ነው ጀግና የሚባለው? ወይስ ሲቪል ሰዎችን ስለደበደበ ነው ጀግና የምትሉት። በጎንደር የተደረገው ድርጊት ጎንደሬ ኅላ ቀር መሆኑ ያስመሰከረበት እና የፈሪ ዱላ የሰነዘረበት ነው። ጎንደር ልብ ቢኖረው ኖሮ ልጆቹ ከእናታቸው ጉያ እየተነጠቁ ሲረሸኑ ወደ ሱዳን ከመሸሽ እና ግጥም
    ከመግጠም ዉጪ ምን ፈየደ?

    መላኩ ተፈራ የእግዜር ታናሽ ወንድም፣
    የዛሬን ማረኝ ዳግም ኣልወልድም።

    ብሎ እያቅራራ ኣይደለም ወይ ልጆቹን ያሳረደው!እውነተኛ ጀግኖች የሰላማዊ ቤት ሳያቃጥሉ፣ ሲቪል ሰዎችን ሳይነኩ ደርግን ተፋልመው የደመሰሱ ናቸው። ጀግንነት ነው ከተባለ ጎንደሬ ኣንድ ኣመት ቤቱን ዘግቶ ሊያለቅስ ይችላል። እባካችሁ ኣናግራችሁ ወደ እናንተ ደረጃ ኣታውርዱን።

  9. “ለሀገር አንድነት ስትል ጠላቷን ጥለህ የወደቅኸው፣
    ለወገን መብት ሲታገል መስዋዕትነት የከፈልከው፣
    የጎሳ አጥርን ደርምሰህ “አንድ አገር፣አንድ ህዝብ” ያልከው፣

    ስምህ፣ስራህ፣ውለታህ፣
    አፈር ከቶ አይለብስም እንደ አካልህ።”
    __________\
    አጀንዳችን አገራዊ፣ጥያቂያችን አሳታፊና ህዝባዊ ይሁን።የህወሀትን የጎሳና የጎጥ አስተሳሰብ በሌላ የጎሳና የጎጥ አስተሳሰብ መታገል ፋይዳ የለሽ፣ የወያኔን “ትግራይና፣ትግሬወች ይቅደሙ” አስተሳሰብ በ” የእኔ ብሄር ይቅደም” መተካት ሀገርን የሚያፈርስ፣ሌላውን አግላይ ብቻ ሳይሆን የወያኔን ስህተት መድገም ነው። ኢህአዴግ ተብየውን በሌላ ኢሀዴግ ለመተካት የሚደረግ “የድርጅቶች ጥምረት” ኢትዮዽያዊነትን አይከተልም፣አይፈጥርምም።

    ህዝባዊ ትግሉ ለአንዲት ሀገር (ኢትዮዽያ)፣ለአንድ ህዝብ (ለኢትዮዽያዊ ዜጋ ሁሉ፣ ዘመናትን ተሻግሮ በሚኖርና ጣሊያንን ጨምሮ የህወሀትንና መሰል ከፋፋይ ድርጅቶችን የተፋጁ ጥሪ ንቅና ርቆ ለሚኖረው ስብስብ) ለአንዲት ባንዲራ (የኢትዮጵያ ህዝብ ማህተመ ህብረት ለሆነችው) በሚል መርህ ተቃኝቶ ይቀጥል!!!

  10. ይገርማል ! ማነህ ባይሳ ነኝ እያልክ አዚህ ያለ የሌለውን እምትሞነጫጭር
    ሥም መጠሪያ ነው ። የአማራው አጋር ነኝ ለማለት ነው ? ኦሮሞ ሥም ይዘህ ስለ ብዐዴን የምታወራው ? ድፋባቸው ነኝ ወይም ግጫቸው ነኝ ሌላም ጫንያለው ሞላ ነኝ ብትል ችግር የለውም ። በጨዋው የኦሮሞ ህዝብ ሥም መቀለዱን አቁም ። እረኛ ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*