(*የፖለቲካ ቀውስ *የዜጎች ሞት *የተቃውሞ ጩኸት *አለመረጋጋት)
ሌ/ጀነራል ፃድቃን ገ/ትንሳይ – በተለይ ለአዲስ አድማስ
በፀጥታ ኃይሎች ችግሮችን ለማስታገስ የሚደረገው ሙከራ ብዙ ርቀት አያስኬድም
ህዝቡ ውስጥ ያለው መሰረታዊ ጥያቄ፣አሁን ባለው አስተዳደር ያለመርካት ነው
በሰላማዊ ሰልፍ የአንድ ሰው ህይወት እንኳ ማለፍ የለበትም
ወልቃይት በትግራይ ሥር እንዴት ተካለለች? ጀነራሉ ያብራራሉ
የቀድሞ የህወሓት ታጋይና የመከላከያ አዛዥ የነበሩት ሌ/ጀነራል ፃድቃን ገ/ትንሳይ፤ በሀገሪቱ
ወቅታዊ ችግሮች ዙሪያ ለቀረቡላቸው በርካታ ጥያቄዎች ሰፊ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የህዝቡ ተቃውሞ መንስኤ—፣ በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች እየተባባሱ የመጡ ግጭቶች-
–፣ተቃውሞዎችን በጸጥታ ኃይሎች ማስታገስ– ፣የወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ ጉዳይ– ወዘተ- —-ከተነሱት ጉዳዮች ውስጥ በዋናነት ይጠቀሳሉ፡፡
የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ አለማየሁ አንበሴ፤ሰሞኑን በሌ/ጀነራል ጻድቃን ገ/ትንሳይ ቢሮ ተገኝቶ
አነጋግሯቸዋል፡፡
በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የሚነሱ ተቃውሞዎች፣ ምንጫቸው ምንድነው ብለው ያስባሉ?
እኔ አሁን በመንግስት የስራ ኃላፊነት ላይ ስለሌለሁ በተደራጀ መንገድ የሚመጣ መረጃ የለኝም። እንደ ማንኛውም ዜጋ ግን የምሰማቸው ነገሮች አሉ፡፡ የመልካም አስተዳደር ችግር አለ፡፡ በአማራ ክልል ደግሞ ዋናው ምክንያት እሱ ነው፣ አይደለም የሚለው ጉዳይ አጠያያቂ ቢሆንም የድንበር ጥያቄ አለ፡፡ በኦሮሚያ ክልል ከማስተር ፕላን ጋር የተያያዘ ጥያቄ ተነስቶ ነበር፤እነዚህ የጥያቄዎች መነሻ እንጂ ህዝቡ ውስጥ ያለው መሰረታዊ ጥያቄ አሁን ባለው አስተዳደር ያለመርካት ነው፡፡
የፖለቲካዊ ስርአቱን ስንመለከት፣በተለይ የፖለቲካ ምህዳሩ እየጠበበ፤ ህዝብ ገዥው ፓርቲ ባስቀመጠለት አደረጃጀት ብቻ ሳይሆን እሱ በፈለገው አደረጃጀት ሃሳቡን የሚገልፅበት ሁኔታ እየጠፋ ነው የመጣው፡፡ አሁን ባለው የመንግስት አወቃቀር፣ገዥው ፓርቲና ለ5 ዓመት አስተዳድራለሁ ብሎ ስልጣን የያዘው መንግስት የሚባለው መዋቅር ምንም ልዩነት በሌለው መልኩ ተደበላልቋል፡፡ በአንድ ፓርቲ ቁጥጥር ስር ውሏል። ይሄ ደግሞ በዲሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት ነው የሚመራው፡፡ በዚህ ምክንያት የህዝቡን የተደራጀ ተሳትፎ በሚፈለገው ደረጃ የማይጋብዝ መሆኑ ሌላው ምክንያት ነው፡፡ በተጨማሪ ሰፊ የስራ አጥነት፣ የኑሮ መወደድ ችግሮች አሉ፡፡ እነዚህ ናቸው ችግሮቹ ብዬ የማምነው፡፡
መንግስት ለተቃውሞዎች እየሰጠ ያለውን የአጸፋ ምላሽ እንዴት ይገመግሙታል? ባለፈው ቅዳሜና እሁድ በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች በተከሰቱ ግጭቶች፣በርካቶች ህይወታቸውን እንዳጡ አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታውቋል፡፡ መንግስት ኃይል መጠቀሙ ተገቢ ነው?
ህዝብ ተቃውሞውን በሠላም የመግለፅ ሙሉ መብት አለው፡፡ መንግስት ይሄን መብት በተሟላ መንገድ መፍቀድ አለበት፡፡ ህዝቡ ይሄ መንግስት አይመቸኝም፤እንዲቀየር እፈልጋለሁ ብሎ ሃሳቡን መግለፅ ይችላል፡፡ የመንግስት ፖሊሲዎች ዘረኛ ከመሰለው፣ ዘረኛ ናቸው ብሎ መግለፅ መብቱ ነው። በአጠቃላይ ህዝቡ፤ ህገ መንግስታዊ መብቱን እስካሁን ሳይጠቀምበት በመቅረቱ ሊወቀስ እንጂ ማንም ሊከለክለው አይገባም፤በተሟላ መልኩ መመቻቸት አለበት፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ መንግስት የሃገር ደህንነትና ፀጥታን የመጠበቅ ሃላፊነት አለበት። እንዲሁም በቀውስና በጫጫታ ሃገር መፍረስ የለበትም፡፡ አንዴ ከፈረሰ መመለሻ ስለሌለው መንግስት ይህን ሃላፊነቱን በተገቢው ሁኔታ መወጣት አለበት፡፡ በአንድ በኩል ህዝቡ ያሻውን ተቃውሞ በሠላም እንዲገልፅ መፍቀድ፣ በሌላ በኩል ደግሞ በውጭ ሃይሎች ተገፋፍተውም ይሁን በራሳቸው ተነሳስተው ወደ ብጥብጥ የሚያመሩትን እየለየ ለህግ ማቅረብ አለበት፡፡
አሁን ባለው ሁኔታ በሃገሪቱ በጣም ከባድ የሆነ የህዝብ ጥያቄ፣በፖለቲካዊ ስርአቱ ላይ እየተነሳ ነው። ፖለቲካዊ ስርዓቱ ዲሞክራሲያዊ ነው? አሳታፊ ነው? የህዝብ ፍላጎትን የሚያስጠብቅ ነው? የሚሉ ጥያቄዎች ከህዝቡ እየተነሱ ነው፡፡ መንግስት ይሄን በጥልቀት ማወቅ አለበት፡፡ አውቆም በሰለጠነ መንገድ የፖለቲካዊ ስርአቱን ሰላም የሚመልስበትን መንገድ ካላበጀ በስተቀር ፀጥታና ሠላም አስከብራለሁ በሚል፣ትናንሽ ችግሮችን ጭምር በሃይል ለመፍታት የሚሞክር ከሆነ ችግሩን ያባብሰዋል እንጂ አይፈታውም፡፡
ችግሩ በዘላቂነት እንዲፈታና ሰላም እንዲሰፍን ምን መደረግ ይኖርበታል?
ሁለት ነገሮች መሠራት ያለባቸው ይመስለኛል፡፡ በአንድ በኩል መበጣበጥ ተፈጥሮ ሃገር እንዳይፈርስና መቋጫ የሌለው ችግር ውስጥ እንዳይገባ፣ መንግስት የሀገሪቱን ፀጥታ የመጠበቅ ኃላፊነት አለበት፡፡ ይሄ እንግዲህ ጊዜያዊ መፍትሄ ነው፡፡ ዋናው መፍትሄ የፖለቲካዊ ስርአቱ ቀጣይነት ትልቅ ጥያቄ ውስጥ ስለገባ፣መንግስት በጥልቀት ማሠብ ይኖርበታል፡፡ ማዘጋጃ ቤቶች አስተዳደር ሰውን ያለማቋረጥ እያስተዳደሩ፣ለህብረተሰቡ የሚወሰነውን ውሳኔ እየወሠኑ፣ የፀጥታ ሃይሎች በበኩላቸው፤የሃገሪቱን ከውስጥም ከውጭም የሚመጡ ጥቃቶችን በተለየ ያልጨረስነው ጦርነት አለ ከዚያ አካባቢ ሊነሱ የሚችሉ የፀጥታ ችግሮችን የማስከበር ኃላፊነት አለባቸው። ይሄን እነሱ እየሰሩ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች አሁን ያለው ችግር በዚህ ሁኔታ መቀጠል የሚገባው መሆኑን አውቀው በዘላቂነት የሚፈታበት ጉዳይ ላይ ማተኮር አለባቸው፡፡ ሁሉም የፖለቲካ ኃይሎች በተለይ ደግሞ ህብረተሰቡ በሚፈልገው መንገድ ይሄን ችግር እንዴት ነው የምንፈታው በሚለው ላይ ቁጭ በለው መወያየት አለባቸው፡፡ ችግሮች ደረጃ በደረጃ የሚፈቱበትን አቅጣጫ ማሳየት ያስፈልጋል፡፡
በፀጥታ ኃይሎች ላይ ያለውን ጫና እያቃለለ መሄድ የሚችለው ፖለቲካዊ ችግሩን ለመፍታት ሁሉም የፖለቲካ ኃይሎች የሚንቀሳቀሱበት እድል ሲኖር ነው፡፡ አሁን ካለው ገዥ ፓርቲ ተፅዕኖ ነፃ መሆናቸውን ህብረተሰቡ እያረጋገጠ የሚሳተፍባቸው ውይይቶችን ነው መፍጠር የሚያስፈልገው፡፡ ይህ ሂደት በዚህ መንፈስ መጀመር አለበት፡፡ መንግስት ውስጥ ካለው ለሀገር የማሰብ ነገር ባልተናነሰ ደረጃ፣ብዙ እውቀት ባለው ለሀገር የሚቆረቆር ዜጋ ዘንድ እንዳለም መታወቅ አለበት፡፡ ይሄን የህብረተሰብ ክፍል አደራጅቶ መፍትሄ ማበጀት ያስፈልጋል፡፡ ይህ ሳይሆን ቀርቶ ሀገር ከፈረሰ በኋላ የፖለቲካ መፍትሄ ሊመጣ እንደማይችል አስቦ በፀጥታ ኃይሎች ላይ ያለውን ጫና እየቀነሱ፣ ህዝቡ በሰላማዊ መንገድ ሀሳቡን ገልፆ፣ ችግሮች የሚፈቱበትን መንገድ ለህብረተሰቡ እያሳዩ መሄድ ያስፈልጋል፡፡ ይሄ ካልተጀመረና እኛ ብቻችንን እንፈታዋለን ወይም ደግሞ በተለምዶ እንደሚደረገው፣ እነሱ መስማት የሚፈልጉትን ንግግር ብቻ የሚናገር ሰው ሰብስበው፣የህዝብ ውይይት አድርገናል የሚል ጨዋታ ውስጥ ከተገባ፣ችግሩ መቼውንም ቢሆን አይፈታም፡፡ መንግስትና ገዥው ፓርቲ መስማት የማይፈልጉትን የሀገር ችግሮች ማሳየት የሚችሉ ሰዎችን አማክሮ፣ የሀገሪቱ ችግር የሚፈታበትን መንገድ ማመቻችት ያስፈልጋል፡፡
የፖለቲካው መፍትሄ ረጅም ጊዜ የሚወስድ ነው የሚሆነው፡፡ ከህገ መንግስቱ በቀር ህጎች ሊሻሻሉ ይችላሉ፡፡ የምርጫ ህጉ ሊሻሻል ይችላል፡፡ መሻሻል ያለባቸው መሻሻል እንዲችሉ ማድረግና የፖለቲካ ምህዳሩን እያሰፉ፣ የሰው ተሳትፎ በዲሞክራሲያዊ ስርአት ተጠናክሮ የሚሄድበትን መደላድል ማስቀመጥ አለብን፡፡
እነዚህ የመፍትሄ ሃሳቦች ተቀባይነት ሳያገኙ ቀርተው፣ ግጭቱ ከቀጠለ መጨረሻው ምን የሚሆን ይመስልዎታል?
እንደ እኔ አሁን ባለው መካረር ከቀጠለ፣ ሀገሪቱን እስከመበታተን ሊያደርስ ይችላል፡፡ ሀገራችን ውስጥ ሰፊ የስራ አጥነት ችግር አለ፤ የተማረው ስራ እያገኘ አይደለም፡፡ በዚህና በሌሎች ምክንያቶች በስርአቱ ያለመርካት ነገር አለ፡፡ በሌላ በኩል፣“የተወሰነው ስልጣን የያዘው ክፍል ሀብቱንም ስለያዘ ነው ችግሮች የተፈጠሩት” እያለ ጥላቻ የሚያሰራጭ አካል አለ፡፡ እነዚህ ሁለቱ ነገሮች ሲገናኙ ችግሩን የበለጠ ያባብሱታል። ይሄ “ተደርጓል አልተደረገም” የሚለው ሌላ ጉዳይ ነው። አንዳንዶቹ ችግሮች በቢሮክራሲው ውስጥ ያሉ ሰዎች ይሄን ግርግር እየፈለጉት ይሆን? የሚል ጥያቄ ነው የሚያስነሳው፡፡ አንዳንዶቹ ብዙ ገንዘብ ዘርፈዋል ነው የሚባለው፡፡ ይሄን የዘረፉትን ለመሸሸግ ግርግሩን እንደ መደበቂያ አድርገውታል ይባላል፡፡ ያም ሆነ ይህ ግን ሁኔታው ህዝብን ከህዝብ ወደ ማናቆር ሊሄድ ይችላል። ህዝብ ከህዝብ ከተናቆረ ደግሞ ሀገር ሰላም አይሆንም፡፡ መጨረሻችን ወዴት ሊሄድ ይችላል ከተባለ – አላውቅም። በተለይ ህዝብ ከህዝብ ከተጋጨ አደጋ ነው፡፡ ይሄን ሊያመጡ የሚችሉ አንዳንድ ምልክቶች ይታያሉ፡፡ እነዚህ በቶሎ መፍትሄ ማግኘት አለባቸው፡፡ የሀገር ሉአላዊነትን በማይፈታተን መንገድ ወደ መፍትሄው መሄድ አለብን፡፡ ችግሩን እያዘገየነው በሄደ ቁጥር መፍትሄው እየተወሳሰበ ነው የሚሄደው፡፡ ከስር ያለው ግፊት የፈነዳ እንደሆነ፣ ሁሉንም ጠራርጎ ነው የሚሄደው፤ማስቆም አይቻልም፡፡ የመንግስት ስልጣን ላይ ያሉ ሰዎች ይሄን አውቀው፣ጉዳዩ ከስልጣናቸውና ከፓርቲው በላይ መሆኑን ተገንዝበው፣ የመፍትሄ መንገዱን መጀመር አለባቸው፡፡
ኢህአዴግ በግንቦት 2007 ምርጫ፣መቶ በመቶ ማሸነፉን በገለጸ ማግስት በተቃውሞ መጥለቅለቁን በመጥቀስ የምርጫ ስርአቱ ላይ ጥያቄ የሚያነሱ ወገኖች አሉ፡፡ የእርስዎ አስተያየት ምንድን ነው?
እኔ ምርጫው ችግር አለበት ነው የምለው። በምርጫው ሂደት ውስጥ ስላልነበርኩ በዝርዝር ባላውቀውም እንደ አንድ የፖለቲካ ተከታታይ ሰው ሳየው፣ ምርጫው በትክክለኛ መንገድ ቢደረግ መቶ በመቶ የሚባለው ውጤት አይመጣም ነበር፡፡ ምናልባት ከ50 እና 60 በመቶ በላይ ሊሆን ይችላል፡፡ በአንድ ሀገር ውስጥ ህዝብ በሙሉ አንድን ፓርቲ መርጧል ብሎ ለመቀበል አይቻልም፡፡ ይሄ ሞኝነት ነው፡፡ ራሳቸውን በራሳቸው እያሞኙ ነው የሚል አመለካከት ነው ያለኝ። ምርጫው፤ በህብረተሰቡ ውስጥ ያለውን ፖለቲካዊ እውነታ አያንፀባርቅም፡፡ ራስን በራስ ማሞኘት የትም ርቀት አያስኬድም፡፡ አሁንም ችግሩ ከተፈጠረ በኋላ፣ ራሳቸውን ብቻ የችግሩ አዋቂና ፈቺ አድርገው መቁጠራቸው፣ራሳቸውን ብቻ ከመስማት የዘለለ ፋይዳ የለውም፡፡ ሌላ መንገድ መቀየስ አለባቸው፡፡
አንዳንድ ወገኖች በተለያዩ ሀገራት ያጋጠሙ ክስተቶችን በመጥቀስ፣ግጭቶች ተባብሰው ከቀጠሉ በግርግሩ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ሊከሰት ይችላል ይላሉ፡፡ እርስዎ ምን ይላሉ?
የሀገራችን ወታደር እንዲህ ያለውን ነገር እያሰበ ይሁን አይሁን ማወቅ አልችልም፡፡ ግን እንዲህ አይነት ያለመረጋጋት ሲፈጠር ከወታደር ብቻ ሳይሆን ከህብረተሰቡም፣“ወታደሩ የሚገደለውን ገድሎ አንድ ጊዜ አዋጅ አውጆ ቢያረጋጋልን ይሻላል” የሚል የጭንቀት ሃሳብ ሊነሳ ይችላል፡፡ እንደኔ ይሄ መፍትሄ አይሆንም፡፡ ሀገሪቱን መልሶ ወደ ማትነሳበት አዘቅት ነው የሚከታት፡፡ ደርግ የሰራውን ስህተት መልሶ መድገም ነው የሚሆነው። ወታደሩ ከፖለቲካ ሙሉ ለሙሉ ነፃ መሆን አለበት። በፖለቲካ ጉዳይ እየገባ ተፅዕኖ መፍጠር የለበትም። ፖለቲካውን ለህዝቡ መተው አለበት፡፡ የሀገሪቱን ሉአላዊነትና ፀጥታ የማስከበር ኃላፊነት አለበት፡፡ የሱ ሥራ ፖለቲካ ውስጥ ሳይገባ የሀገር መረጋጋት መፍጠር ነው፡፡
ተቃውሞና ግጭቶች ባየሉባቸው አካባቢዎች፣ዜጎች በቀጥታ በጥይት እየተገደሉ መሆኑን አለማቀፍ ሪፖርቶች ይጠቁማሉ፡፡ የኃይል እርምጃ በመውሰድ፣ ተቃውሞን ለማስቆም መሞከር ምን ያህል ያዋጣል?
የሞቱ ሰዎችን ቁጥር በተመለከተ ብዙ መረጃ የለኝም፤ ግን በእንዲህ አይነት ጉዳይ፣የአንድ ሰው ህይወት እንኳ ማለፍ የለበትም፡፡ እንዲህ ያለው የኃይል አማራጭ መቅረት አለበት፡፡ ህዝቡ ሰላማዊ ሰልፎችን ሲደርግ የተነሱ ነገሮች አሉ፡፡ ከህዝቡ ፍትሃዊና ትክክለኛ ጥያቄ ጋር አያይዘው ጥያቄውን ወደሌላ አቅጣጫ ለማስያዝ የሚሞክሩ ኃይሎች ይኖራሉ፡፡ የመንግስት ኃይሎችም በሰልፉ ወቅት በሚፈጠር ውጥረት፣ከተገቢው በላይ ምላሽ ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ ከዚህ የተለየ አማራጭ አለ ወይ? ከተባለ፣በሌሎች ሀገሮች አለ፡፡ እኛ ሀገር እዚያ አቅም ላይ ስለመደረሱ አላውቅም፡፡ እኔ በነበርኩ ጊዜ ሰላማዊ ተቃውሞ በጥይት ሳይሆን በሌላ የምንበትንበት አማራጭ አልነበረንም፡፡ እስካሁን ግን ያንን አቅም ካልፈጠሩ መፍጠር ነበረባቸው፡፡
አሁን ባለው ፖለቲካዊ ሁኔታ ችግሮችን በፀጥታ ኃይሎች ለመፍታት የሚደረገው ማንኛውም ሙከራ የበለጠ ነገሩን እያካረረ፣ የበለጠ የሰው ህይወት እያጠፋና በሰላማዊ መንገድ ችግሮችን የመፍቻ መንገዱ እየመነመነ ነው የሚሄደው፡፡ በዚህ ረገድ በጣም አሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ ነው ያለነው፡፡ የህዝብ ተቃውሞዎችን በፀጥታ ኃይሎች መልሼ፣እድሜዬን ትንሽ እገፋለሁ የሚል መንግስት ካለ በጣም የሚገርም ነው፡፡ የፀጥታ ኃይሉ ሀገር እንዳይፈራርስ ትንሽ ማቆያ ይሆናል እንጂ መፍትሄ አይሆንም፡፡ ዋናው መፍትሄ፤ ገለልተኛ የፖለቲካ ሂደቱን መጀመር ነው፡፡ በአመፅና በግጭት መንግስትን መቀየር፣ እስካሁን የተሰሩትን ስራዎች ይጠራርጋቸዋል። ከሁሉም በላይ ደግሞ የወደፊቱን ማወቅ አያስችልም፡፡ ይህ እንዳይከሰት ህገ መንግስቱን መሰረት አድርጎ፣ ከህገ መንግስቱ በመለስ ሌሎችን ህጎች ከልሶ፣ በቀጣይ ውጤቱ ተአማኒነት ያለው ምርጫ ማካሄድ ያስፈልጋል፡፡
ህገ መንግስቱ መሻሻል ካለበት፣ራሱ ህገ መንግስቱ ባስቀመጠው መሰረት ነው መሻሻል ያለበት፡፡ ለምሳሌ ዝም ተብሎ አንቀፅ 39ኝን እናንሳ ከተባለ፣ የባሰ ኢ-ዲሞክራሲያዊ ነው የሚሆነው፡፡ ዋናው ነገር ግን በፀጥታ ኃይሎች ችግሮችን ለማስታገስ የሚደረገው ሙከራ ብዙ ርቀት አያስኬድም፡፡
ገለልተኛ የፖለቲካ ሂደት መፈጠር አለበት ሲሉ ምን ማለትዎ ነው?
አሁን ያለውን የሥራ አስፈፃሚ እንቅስቃሴ እያስቀጠሉ፣ በሚቀጥለው ምርጫ ማንኛውም ፓርቲ ተወዳድሮ ተአማኒነት ያለው ውጤት እንዲመጣና፣ በትክክል ያሸነፈ ፓርቲ ስልጣን እንዲይዝ አልያም እንዲጋራ የሚያስችል ሂደት ይጀመር ማለቴ ነው፡፡ እስከዚያ ድረስ ግን የሃገሪቱ ፀጥታ እየተጠበቀ፣ ተከታታይ ፖለቲካዊ ውይይቶች እየተደረጉ፣ የሚሻሻለው እየተሻሻለ መጓዝ አለብን፡፡
አንዳንድ ፓርቲዎች የሽግግር ጊዜያዊ መንግስት ይቋቋም የሚል ሃሳብ ያቀርባሉ?
የሽግግር ጊዜያዊ መንግስት ይቋቋም የሚባለው ሃሳብ፣ በምን የህግ ማዕቀፍ ሆኖ ነው የሚቋቋመው የሚል ጥያቄ ያስነሣል፡፡ አንዳንዴ በምክክር፣ሃሳቦች ከህብረተሰቡ መፍለቅ አለባቸው ስል ፤“ይሄ ሞኝነት ነው÷አሁን ያለው መንግስት ከዚህ ቀደም ይሄን ነገር አድርጎ አያውቅም÷ሁሉንም ነገር የሚያደርገው በሃይል ነው፤ አንተ ደግሞ ከፓርቲውና ከመንግስት ነፃ የሆነ የፖለቲካ ሂደት ይጀምር ትላለህ፤ እንዴ ሆኖ ነው ይህ የሚሆነው?” የሚል ጥያቄ ያነሱልኛል፡፡
እኔ ከሁለት ነገር ነው የምነሣው፡፡ አንደኛ፤ ያለው የህግ ማዕቀፍ የሚፈቅደው ይሄንኑ መንገድ ብቻ ነው። ከዚህ ውጭ ከሆነ፣ ጉልበት ያለው ይህን መንግስት ካፈረሰ በኋላ የሚመጣ ነው የሚሆነው፡፡ ያ ደግሞ ዋስትና የሌለው፣ ጠቃሚ ያልሆነ መንገድ ነው፡፡ እኔ ላልኩት አማራጭ ግን ዋስትና የሚሆነው ህዝቡ ነው፡፡ የትግሉ ባለቤት ስለሆነ፡፡ በኃይል መንግስት የሚያወርደውና ስልጣን ሊይዝ የሚችለው ማን አንድ ጉልበተኛ ኃይል ብቻ ነው የሚሆነው፡፡ ገለልተኛ የፖለቲካ ንግግር ሂደቱ የሚካሄድ ከሆነ ግን በቀጣይ በሚደረገው ምርጫ ውጤት ሊገኝበት ይችላል፡፡ ይሄን ሊያደርግ የሚችለው ህዝብ ብቻ ነው፡፡ እኔ የማምነው ዲሞክራሲ፣ ሀሳብ ያላቸው ግለሰቦች ወይም “እኛ እናውቅልሃለን” የሚሉ ፓርቲዎች የሚያመጡት አይደለም፡፡ ዲሞክራሲ በህብረተሱ ውስጥ ያሉ ፓርቲዎችና አደረጃጀቶች፣ በሚያደርጉት ፍትጊያ የሚመጣ ነው፤ እስከ ዛሬ ግን ያለው፣ ለህዝብ እኔ አውቅልሀለሁ አይነት ነው፡፡ ይሄ ደግሞ የት እንደሚያደርስ አይተነዋል፡፡ ስለዚህ ለወደፊትም ቢሆን ዋስትናው፣ የራሱ የህዝብ ጥቅም ነው፡፡ ይሄን አልፎ ለመቀልበስ የሚፈልግ ኃይል ከወታደሩም ይሁን ከሲቪሉ ቢመጣ፣ ሂደቱ የህዝብ ከሆነ አይቀለበስም፡፡
በሰሜን ጎንደር አካባቢ ያለው ተቃውሞ በተለይ ከ“ወልቃይት አማራነት” ጋር የተያያዘ ነው፡፡ የወልቃይት የማንነት ጥያቄ ጉዳይ በምን አግባብ ነው መፈታት ያለበት?
እኔ የወልቃይት ጉዳይ ለአንዳንድ ፖለቲካዊ አላማዎች ሽፋን ነው ብዬ ነው የማምነው፡፡ እንዴት ነው የሚፈታው ላልከው፣እኔ የሚታየኝ ህገ መንግስቱን መሰረት አድርጎ ነው፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ፣ ይሄ ትልቅ ጉዳይ መደረግ አልነበረበትም፡፡ ህውኃትና ብአዴን ተመካክረው መፍታት የሚችሉበት ደረጃ ላይ መድረስ ነበረባቸው፡፡ ማቆየት ካስፈለጋቸውም ህዝብ አሳምነው ማቆየት ይችሉ ነበር፡፡ አሁንም ያለውን ችግር ማወሳሰቢያ እንዳይሆን ሁለቱ አካላት ቢነጋገሩበት ጥሩ ነው፡፡ ደም ከመቃባትና ቁርሾ ከመፍጠር ይልቅ በአካባቢው ያሉ የሀገር ሽማግሌዎች ሰብስቦ መምከር ያስፈልጋል። በህጋዊ መንገድ ስትሄድም ህገ መንግስቱን መሰረት አድርጎ መፍታት ያስፈልጋል የሚል እምነት አለኝ፡፡ የህገ መንግስት ሊቅ አይደለሁም ግን ክልሎች በሚወሰኑበት ወቅት ከፍተኛ የፖለቲካ ውሳኔ ሰጪ አካል ውስጥ ነበርኩ፡፡ በወቅቱ ቋንቋና የህዝብ አሰፋፈርን መሰረት አድርገን እንወስን በሚል ነው የወሰነው፡፡ በዚህ መሰረት ደግሞ የተወሰነው ተወስኗል፡፡
በወቅቱ ወልቃይት እንዴት ነው ወደ ትግራይ የተካለለው?
አሁን እየጠየከኝ ያለኸው መረጃ ነው፡፡ ይሄን መረጃ አሁን አላስታውሰውም፡፡ እንደዚህ ሆኖ ነበር ብዬ ለማለት አልችልም፡፡ የተጠቀምንበት አቅጣጫ ግን የፌደራሊዝሙን መነሻ ነው፡፡ የህዝቦች ቋንቋና ባህልን መነሻ አድርገን ነው የከለልነው፡፡ እኔ እስከማውቀው ድረስ እዚያ አካባቢ ያለው አብዛኛው ህዝብ ትግርኛ ተናጋሪ ነው፤ ባህሉ የትግራይ ነው፤ በትግራይ ውስጥ ሊካተት የሚችል ህዝብ ነው፡፡ የሆነውም በዚህ አግባብ ነበር፡፡ ግን ቆይቶ የማንነት ጥያቄ ሊነሳ ይችላል፡፡ ያኔ ስለተወሰነ በቃ መነሳት የለበትም ተብሎ መታሰብ የለበትም፡፡ ጥያቄው ሲነሳ ህገ መንግስታዊና ሰላማዊ ሆኖ ነው መነሳት ያለበት፡፡ በህዝቦች መካከል ግጭት መፈጠር የለበትም፡፡ ህገ መንግስቱንና አሁን ያለው የፌደራል ስርአት የተዋቀረበት መርህ መነሻ አድርጎ ነው መፈታት የለበት፡፡ አሁን ያለው የፌደራል ስርአት አወቃቀር፣በህገ መንግስቱ ይከለስ ተብሎ ተቀባይነት ካገኘ ደግሞ ጉዳዩም ይከለሳል፡፡ ስለዚህ በእነዚህ አግባቦች ነው መፈታት ያለበት፡፡
እርስዎ፤ በወልቃይት ጉዳይ የተፈጠረውን ችግር፣ ህውሓትና ብአዴን መፍታት ነበረባቸው ብለዋል፡፡ ሆኖም የሁለቱ ግንኙነት ሻክሯል የሚሉ ወገኖች አሉ፡፡ እርስዎ የሰሙት ነገር ይኖር ይሆን?
የአሁን ግንኙነታቸውን አላውቅም፡፡ የድርጅት አባልነቴን ካቋረጥኩ 20 ዓመት አልፎኛል፡፡ ችግር አለባቸው የሚለውን እንደ ማንኛውም ሰው በወሬ ነው የምሰማው፡፡ ድሮ ግን ጠንካራ የትግል አጋርነት ነበረን። አብረን ተዋግተናል፤ ብዙ ስራ ሰርተናል፡፡ ብአዴን እንዲጠነክር ህውሓት ረድቶታል፡፡ ጥሩ መግባባትና አብሮ የመስራት ባህል ነበረን፡፡ ይሄ ማለት በወቅቱ የሚነሱ ጥቃቅን ችግሮች አልነበሩም ማለት ሳይሆን ሲነሱ በውይይት ነበር የምንፈታው፡፡ እንደዚያ ጊዜ ቢሆኑ ኖሮ አሁን ያለው ችግር በምንም መመዘኛ እዚህ ደረጃ አይደርስም ነበር፡፡ በቀላሉ ሊፈታ የሚችል ነው፡፡ ከዚያ ግንኙነት በመነሳት ነው፤ አሁን ያለው ችግር እንዴት እዚህ ደረጃ እንደረሰ ለኔም የሚገርመኝ፡፡
በትግራይ ክልል መዲና መቀሌ ለ 1 ዓመት ተኩል ያህል ሠርቻለሁ። በቆይታየም አብዛኛውን የትግራይ ከተሞች ተዘዋውሬ ለማየት ችያለሁ ። እንደታዘብኩት አንዳንድ ጭፍን አመለካከት ያላቸው ሰዎች እንደሚሉት ህዝቦቿ በምቾት የሚኖሩ አይደሉም። የትኛውም ክልል ያለ ህዝብ የሚኖረውን ኑሮ ነው ሚኖሩት እንዲያውም ከዛ የከፋ ቢሆን ነው። ተፈጥሮ እንኳን እንደ ሌላው ክልል የተመቸ አይደለም። ኑሯቸውን ለመቀየር ግን ማይፈነቅሉት ድንጋይ ማይገፉት ተራራ የለም። በጣም ጠንካራ የስራ ሰዎች ናቸው። ሌላው ክልል ያለ የአስተዳደር ችግር ሙስና የፍትሕ ችግር የመሰረተ ልማት ችግሮችና የመሳሰሉት ትግራይም በሰፊው አለ። ስለዚህ ይሄ ምስኪን ህዝብ ከመንግሥት የተለየ ድጋፍና እንክብካቤ እንደሚደረግለት የሚያስቡ አንዳንድ ሰዎች እንደተሳሳቱ በደንብ ይወቁት። የፖለቲካ ቁማር ለመጫወት ብሔርን ከብሔር በማጋጨት የተሳሳተ ወሬ ሚነዙትን የፖለቲካ ምሁር ነን ባዪች በላይክና በኮሜንት ከማወደስ እንቆጠብ!
ይልቅስ የጋራ ችግራችን በጋራ እየታገልን ላገራችን እድገት በአንድነት እንቁም! የሚስማማ ለወደፊት የተሻለች ኢትዮጵያን ማየት የሚሻ ላይክ ያርገው።
ይድረስ ለሌ/ጀኔራል ፃድቃን
ምንም እንኳን ቀደም ሲል በሃገራችን መከላከያ ሃይል በከፍተኛ ስልጣን አሁን በስልጣን ካለዉ መንግሥት ጋር ቀደም ሲል ከጫካ ጀምሮ የያዘዉን ሃገርና ህዝብ የማጥፋት ሴራ ተሳታፊ የነበሩ ቢሆንም በዚህ ወቅት በተወሰነ ደረጃም ቢሆን የሥርዓቱን መድከምና መፈራረስ ይህም በሃገሪቱ ላይ ያስከትላል ያሉትን አሉታዊ ሃሳቦች መዘርዘረዎ እንደ አንድ ዜጋ ጥሩ ነዉ ለማለት እወዳለሁ፡፡ ምክንያቱም እኔም እንደርስዎ አንድ ዜጋ ነኝ ብየ የማስብ ስለሆነ እኔ አዉቃለሁ ምን አገባህ አንተ ምናምን ፣ ጠባብ ፣ ትምክተኛ በማለት ከሃሳብዎ ጀረባ ያለዉን ስብእናዎን ለመንካት አልፈልግም ፡፡ ይህ የወያኔና የዘረኞች መለያ ፀባይ ነዉና ፡፡ ይሁንና ከታች በተቀመጡት ሃሳብዎ አልስማማም
1. በአንድ በኩል ህዝቡ ያሻውን ተቃውሞ በሠላም እንዲገልፅ መፍቀድ፣ በሌላ በኩል ደግሞ በውጭ ሃይሎች ተገፋፍተውም ይሁን በራሳቸው ተነሳስተው ወደ ብጥብጥ የሚያመሩትን እየለየ ለህግ ማቅረብ አለበት፡፡
የሃሀሪቱ ዜጎች ከሰሜን እስከ ደቡብ ያንቀሳቀሰዉን የዲሞክራሲና የነፃነት ጥያቄ በዉጭ ሃይሎች ተገፋፍተዉ የሚለዉ አበባል ጥያቄዉን ለአነሳዉ ሰፊ ህዝብ ያለዎትን ንቀት ያመለክታል ምክንያቱም የኦሮምያን ጥያቄ መንግሥት ራሱ በማመን የተቀበለዉ ሲሆን የወልቃይት ጥያቄ በሌሎች የዉጭ ሃይሎች የተገፋ ሳይሆን በደል ያንገሸገሸዉ ህዝብ በቃኝ ለማንነቴ ብሎ ያነሳዉ ግፍና በደል ያስቆጣዉ ህዝብ ጥያቄ መሆኑ የአደባባይ ሚስጢር ነዉ ፡፡ ከ1972 ዓ.ም ጀምሮ ወያኔ የቦታዉን ለምነትና ስትራቴጅክ አቀማመጥ በማጥናት አስቦና አቅዶ ቦታዎችን ወደ ትግራይ እንዲከለልና ይህንንም ተከትሎ የመንግሥት ሥልጣን በያዘበት ማግስት የተመረጡ የአካባቢዉን ቦታዎች ወደ ትግራይ ክልል ከልሏል፡፡ እርስዎ ለዚህ መልስ ነዉ ያሉት ሰዎቹ ትግሬኛ ስለሚናገሩ ነዉ ያሉት ይህ ማለት አማርኛ አይናገሩም ለማለት ነዉ ወይስ ትግሬኛ የሚናገር ወይንም ትግሬኛና ሌላ አንድ ወይም ከዚያ በላይ ቋንቋ የሚናገር ህዝብ ሁሉ ወደ ትግራይ ክልል መካለል አለበት ለማለት ነዉ፡፡ ጄኔራል ሁሉንም የሰዉ ልጆች የሚያንገበግበዉ ማንነትን እንደ መኪና ታርጋ ፈቃድ የሚሰጠዉ ወያኔ መሆኑ ብቻ ሳይሆን አቶ መለስ ያሉትን በአካባቢዉ Demographical change ለማምጣት ተብሎ የተፈፀመዉ ሰቆቃ የሰዉ ልጆች ሁሉ ለዘለዓለም የሚያስታዉሱት ወንጀል ነዉ፡፡
2. መንግስት ውስጥ ካለው ለሀገር የማሰብ ነገር ባልተናነሰ ደረጃ፣ብዙ እውቀት ባለው ለሀገር የሚቆረቆር ዜጋ ዘንድ እንዳለም መታወቅ አለበት፡፡
ለእኔ የሚገባኝ አንድ ሃገሩን የሚወድ መንግሥት አንድ ማህበራዊ ኢኮኖሚክ ማህበረሰብ ለመፍጠርና በህዝቡ ዘንድ ማህበራዊ ዕሴቶችን በማጎልበት ለሃገር አንድነትና ለሃገሪቱ ህዝቦች በሙሉ ብልፅግና የሚተጋ ነዉ ፡፡ በእርግጥ የወያኔ መንግሥት ለሃገር ያስባል ? ይልቁንም ለከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲያቸዉ ይመች ዘንድ የበሬ ወለደ ጥላቻ ፕሮፓጋንዳዎችን በመንዛት አንዱን ብሄር / ብሄረሰብ በማጋጨትና አነርሱ የሰላም አባት በመሆን የህዝቦችን የጋራ እሴቶች ለመናድ ቀና ደፋ የሚል በጠቅላላዉም ወያኔ በስልጣን ላይ እስካለ ብቻ ኢትዮፅያ የምትባል ሃገር የምትኖረዉ ይህ ካልሆነ ኢትዮፅያ ገደል ትግባ ብሎ የሚሰራ መንግሥት በምን ሚዛን ነዉ ለሃገር አሳቢ የሚደረገዉ፡፡ የአንድ ሃገር ዜጎች በእኩልነት የማይስተናገዱባት ሃገር እንዴት ሃገሩን በሚወድ መንግሥት እየተመራች ነዉ ይባላል ፡፡ በዛሬዋ ኢትዮፅያ እነ ማን ዜጋ እንደሆኑ ሌሎች ደግሞ ከሁለተኛም ዜጋ በታች መሆናቸዉን ለማወቅ ወደሚከተሉት ተቋማት መሄድ ብቻ በቂ ነዉ
ሀ. ኢትዮፅያ አየር መንገድ
ለ. ቴሌ ኮምንኬሽን
ሐ. ማህበረ ቅዱሳን
መ. ጉምሩክ
ሠ. የመረጃ መረብ …
ረ. መከላከያና ሌሎች ደረጃ አንድ ተቋራጭ ወይንም ኢንቨስተር እየተባሉ የሚሞካሹትና ሌሎች ሥራ ማግኘት አይደለም የሚልሱት የሚቀምሱት ያጡትን ኢትዮፅያዉያንን ማየት ብቻ ይህ መንግስት ለሃገርና ለጠቅላላ ህዝቧ ሳይሆን ለአንድ ቡድን የቆመ ዘረኛ መንግሥት መሆኑን ማንም ጤነኛ አዕምሮ ያለዉ ሰዉ ያዉቀዋል፡፡ ስለዚህም “የተወሰነው ስልጣን የያዘው ክፍል ሀብቱንም ስለያዘ ነው ችግሮች የተፈጠሩት” እያለ ጥላቻ የሚያሰራጭ አካል አለ፡፡ እነዚህ ሁለቱ ነገሮች ሲገናኙ ችግሩን የበለጠ ያባብሱታል ፡፡ ይቅርታ ጄኔራል ቢያንስ ይህን በገሃድ የሚታይ ነገር ካለመኑ በተከታታይ የሚሰጡዋቸዉ መግለጫዎች በቀናነት ለሃገር በማሰብ እንደ ዜጋ የሰጡት ነዉ ለማለት እቸገራለሁ፡፡
3. የመንግስት ኃይሎችም በሰልፉ ወቅት በሚፈጠር ውጥረት፣ከተገቢው በላይ ምላሽ ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ ከዚህ የተለየ አማራጭ አለ ወይ? ከተባለ፣በሌሎች ሀገሮች አለ፡፡ እኛ ሀገር እዚያ አቅም ላይ ስለመደረሱ አላውቅም፡፡
ይህ አበባል ምን ማለት ነዉ ? አስለቃሽ ጢስ ስለሌለዉ በሰልፍ የታደመዉን ሰዉ በጥይት እንጨርስ ማለት ነዉ? ምን አልባት የህዝብ ሃብትና ንብረት እንዳይጠፋ ወደ ሰማይ ተኩሰናል በስህተትም አንድ ሰዉ ተጎድቷል ማለት ከሆነ ጥሩ ባይባልም አይን ያወጣ ፍጅት አልተፈፀመም ማለት ይቻላል ፡፡ ጄኔራል እኔ በአለሁበት ከተማ የተፈፀመዉን እርስዎም አያጡት ፣ ሰላማዊ ሰልፍ እንደተጠራ ተነገረ አንድ ቀን ሲቀረዉ መንግሥት ህገ ወጥ ነዉ አለ የም ሆነ የባህር ዳር ህዝብ ለሰላማዊ ሰልፍ ወጣ ፣ በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ህዝብ ተሳታፊ ሆነ ሰልፉ ከማህል ከተማ ተጀመረ በሰላም ሲካሄድ ቆየ በመጨረሻም ከሌላ አካባቢ የሚመጡ ሰዎችን ለመቀበል አባይ ማዶ ሄደ ፣ በንፅፅር አባይ ማዶ ብዙ የፋይናንስ ተቋማትም ይሁን የመንግሥት ቢሮዎች በብዛት አይገኙም ይሁንና ንፁሃን በገፍ ተጨፈጨፉ፣ ነገ ሃገር ተረካቢ የተባሉ ወጣቶች ረገፉ፣ ባዶ እጃቸዉን የነበሩ ወጣቶች ከሰዉ የተፈጠሩ በማይመስሉ የወያኔ አጋዚዎች ታረዱ፣ አዲዎስ፣ ባህር ዳር በንጽሃን ደም ታጠበች ፡፡ ይህ በርስዎ አስተያየት ምን አለበት እንደ አዉሮፓ ሌላ መከላከያ ስለሌለን በጥይት ይጨፍጨፉ ማለት ነዉ ፡፡ በጣም አሳፋሪ ነዉ እዉነቱን ልንገርዎት ይህ ዘረኛ መንግሥት በጥላቻ በተገፋ ስሜት ንፁሃንን በግፍ ጨፈጨፈ ፣ ለዚህ ደግሞ ምንም ማስተባበያ ሊሰጥበጥ የማይችል Atrocity motivated massacre በአማራ ህዝብ በተለይም በባህር ዳር ህዝብ ላይ ተፈፀመ፡፡
4. እኔ የወልቃይት ጉዳይ ለአንዳንድ ፖለቲካዊ አላማዎች ሽፋን ነው ብዬ ነው የማምነው፡፡ እንዴት ነው የሚፈታው ላልከው፣እኔ የሚታየኝ ህገ መንግስቱን መሰረት አድርጎ ነው፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ፣ ይሄ ትልቅ ጉዳይ መደረግ አልነበረበትም፡
የወልቃይት ጉዳይ ከላይ እንደጠቀስኩት ብሶትና እልቂት ያነሳሳዉ ህዝብ ጥያቄ ነዉ ስለዚህ ቀላል ነዉ ተብሎ ወደ ጎን የሚተዉ አይደለም፡፡ ጄኔራል ወያኔ የህዝቦች የማንነት ጥያቄ እያለ ሲለፈልፍ ትልቅ የፖለቲካ ጥያቄ ፣የወልቃይት ህዝብ ማንነት ሲመጣ ደግሞ መናኛ ጥያቄ ለምን ማለት እንደፈለጉ አይገባኝም ማንነትን በጉልበት ማላበስ ወይንም መንፈግ አይቻልም፡፡ አፈታቱን በተመለከተ በህገ-መንግስቱ ይፈታል በእርግጥ በህገ መንግሥቱ ሁሉም ህዝቦች ተወያይተዉና ተወካያቸዉ በተገኙበት ሆኖ ቢሆን ጭራሽ አስተማማኝ ነዉ ባይባልም ይሻል ነበር ፡፡ ይሁንና ወያኔና ሌሎች ቡድኖች የራሳቸዉን የግዛት አንድነትና ግዝፈት በጠበቀ መልኩ ያካለሉትንና ከዚያም በኃላ ላለፉት 40 ዓመታት በተለያዪ ሴራዎች የአካባቢዉን ህዝብ በመግደል ፣ በማፈናቀልና በማሰደድ በምትኩ 100ሽህ የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆችን በማስፈር በህገመንግሰቱ መሠረት ይፈታል ማለት አይናችሁን ጨፍኑና ላታላችሁ ማለት ነዉ ፡፡ በአንድ ጀምበር የባህር ደርን ህዝብ በማፈናቀልና ትግሬ በማስፈር በሪፍረነደም ትግራይ ነኝ እንዲል ማስቻል ይቻል ይሆናል ፣ ምን አልባት ሁሉም ነገር ኢትዮፅያ ዉስጥ የሚሆነዉ በጉልበት ከሆነ ማለቴ ነዉ ስለዚህ ታሪካዊ መረጃዎች ታይተዉና ቀደምት ህዝቦች ታሪካዊ ትስስርን ከግምት ዉስጥ ያስገባ ፍትህ ለወልቃይት የአማራ ህዝብ ካልተሰጠ በቀር በጉልበት የተወሰደ ሁሉ በጉልበት ይመለሳል በዚህም አገር ሲሰራና ሲፈርስ ይኖራል እንጅ ሃገርና ሃገራዊ ስሜት አይገነባም፡፡
በጠቅላላዉ ጄኔራል የህዝቡ ጥያቄ ሥር ነቀል የሥርዓት ለዉጥ እንጅ የይስሙላ Reform አይደለም ስለዚህም ሣሞራን በገ/ኪዳን ለመቀየር ሳይሆን ከየትኛዉም ወገን የመጣ ለህዝብ ለሠላምና ደህንነት የሚተጋ መሪና ጄኔራል እንፈልጋለን ፡፡ ደህና ይሁኑ፡፡
In my opinion zis man had a good idea but swallowed by those dictatorship groups
It is good to come to this point General, but it looks too late. General did not tell the truth. He did not admit all the military generals are from a minority, ruling the other majority. He tries to be away from a question that the economy is also controlled my these minorities, as he is part of garbing the economy. So for the true peace you need to be rational. How come the constitution is unchangeable? It is impossible to keep on killing people and lying all the life. The people finally is the winner. Please come with rationale, so that people can listen you. The people need change period.
Tsadkan Is NoW Expliter And Share HolDer In Tplf, He Gate Benefits With Out Hard Work,
Tigrians In Wolkayit Ar Not Wolkiyite But Imigrants For Work In Wolkait
You Big Eater Wolkait Is For Amhara Gonder.
You Shamles Tsadkan Why You Did Not Give Autonomy fOr Amharas Imigrants In guraferda ben Shagul As You Did Wolkayit Tigray.
But You Push other Tribes To Murder And Burn Everything They Have,
You See The Truth.
Tell Tplf To Leave Alone Amharas . We Amharas Were House Food For All During The King And Mengistu
God Bless Amhara Gonder Gojam And All
We should not be deluded by this traitor.
He did not even have the decency to admit that Wolqait was annexed by Tigre TPLF.
The fellow must be an outright liar or plainly stupid. I speak his bloody language as well as Arabic. Could Sudan claim my ancestral Wolqait because I speak that country’s language.
How disingenuous of this stupid idiot who has so much blood of my relatives on his hands.
Does he think readers are as daft as himself to buy the nonsense he is peddling?
It is this murderer and his primitive Tigre Peoples’ Liberation Front who should establish any peoples’ identities? Or should such crucial matters be left to the people in question?
If I say I am an Amhara (and a Gondere at that), what business is it of a Tigre, to say that I am not let alone to label me a Tigrean?.
This traitor is of course patently dishonest. He does not even need any brains, to condemn his TPLF for the annexation of Begemdir, Wollo and Afar. The current massacre of Oromos and Amaras is at genocidal scale. That does not bother him either. He threatens us that he fears the country will disintegrate anymore than what he and his Tigre cohorts have done.
TPLF has made him multimillionaire in occupied Ethiopia. He is impelled to defend them as well as himself.
Ethiopians will be liberated from Tigres soon. But Tigres including this man will rue the day they decided to undo Ethiopia.
Egzer wagahin yikfelih ante nefse gedaay Tigre!! Ye Ethiopia dmenga telaatoch indehonachihu ager awqual.
Tige mehonin yemitregmubet qen dersual
ማህበረ ቅዱሳንን እንዴት ጥቅም ከሚታፈስባቸው አየር መንገድን ከመሳሰሉ ለጥቅም ከተጠራሩ የቤተዘመድ ድርጅት ጋር አዛመድከው?ግለጽልኝ
ይቅርታ ማህበረ ቅዱሳን ያልኩት የኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ሴኔዶስ ማለቴ ነዉ ፡፡ አምስት ኪሎ የሚገኘዉን ከቅድስት ማሪያም ወደ ታች ያለዉን ለማለት ነዉ ፡፡ ትልቅ ይቅርታ፡፡ ለጥያቄህ ክብር አለኝ