አስቸኳይ መልዕክት! ይድረስ ለብአዴ‬ን አመራር (ያሬድ ጥበቡ)

‎ያሬድ ጥበቡ

የትግራይ ማህበረሰብ ውስጥ ለወቅቱ የኢትዮጵያ ሁኔታ ምላሽ ተደርጎ የሚታየው ብአዴን በነፍጠኞች ተይዟል፣ መሪዎች መመንጠር አንገብጋቢ ጉዳይ መሆኑን የድርጅቱ ልሳኖች ከሰሞኑ ዘግበዋል። በመሆኑም ‪እነ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው‬ አልሰሙ እንደሆነ በመቐለ ቤተመንግስት እየ‬ተደገሰላቸው ያለውን ፍጅት ከወዲሁ አውቀው በጀመሩት ከህዝብ ጋር የመወገን ትክክለኛ ፖሊሲ ከዚህ ከተደገሰላቸው እርድ እንዴት መዳን ይቻላቸዋል? ባለፉት 40 አመታት ህወሐትን ከቅርብም ሆነ ከሩቅ እንዳጠናት ሰው የሚከተሉትን ምክሮች መሰንዘር ይጠበቅብኝ ይመስለኛል። ከተሰነዘረባቸው አደጋ ለመዳን የብአዴን መሪዎች የሚከተሉትን እርምጃዎች በአፋጣኝ መውሰድ ይኖርባቸው ይመስለኛል።

  1. የክልል ምክርቤቱን ስብሰባ ጠርተው፣ ‎ያለምክርቤቱ ጥሪ ወደክል‬ል የገቡትን የአግአዚና ፌዴራል ፖሊስ ሀይሎች ክልሉን በአፋጣኝ ለቀው እንዲወጡ ውሳኔ ማሳለፍና፣ ይህንንም ለህዝቡ በመገናኛ ብዙሀን ማስተላለፍ
  2. በዚሁ የክልል ምክርቤት ስብሰባ ወቅት ‎የመከላከያ ሰራዊቱ‬ በሃገር ውስጥ ፓለቲካ እጁን እንዳያስገባና፣ ብቸኛ ተግባሩ ሃገሪቱን ከውጪ ጠላት መከላከል መሆኑን ግልፅ ማድረግ፣ እግረ መንገዱንም የመከላከያና ደህንነት አመራሩ የሃገሪቱን ብሄራዊ ተዋፅኦ የተከተለ እንዲሆን ጥያቄ ማቅረብ፣
  3. በብአዴን ውስጥ ተሰግስገው ‎ለህወሐት የሚሰልሉ‬ እንደ ካሳ ተክለብርሀን፣ ታደሰ ካሳ፣ አለምነው መኮንን ወዘተ የመሳሰሉትን የአመራር አባላት ከአባልነታቸው ማገድና ካስፈለገም ወደ እናት ድርጅታቸው ህወሐት እንዲመለሱ ፈቅዶ ‎ማሰናበት
  4.  የኢህአዴግ አመራርና አደረጃጀት የብሄረሰቦችን ተዋፅኦ የጠበቀ እንዲሆን ማድረግና፣ የህዝብ ቆጠራውን ተከትሎ፣ የኢህአዴግ አመራር 34% ኦሮሞ፣ 28% አማራ፣ 6% ትግራዋይ ወዘተ እንዲሆን ውሳኔ ማስተላለፍና ለተግባራዊነቱ መታገል
  5. ከአማራ ክልል የተወሰዱትን ‎የድንበር መሬቶች‬ ለማስመለስ መወሰንና፣ ይህንኑ ውሳኔ የሚከታተል ከተቀሙት ቀበሌዎች ነዋሪዎች፣ ምሁራንና፣ የፖለቲካ ልሂቃን የተውጣጣ ግብረሃይል ማቋቋም
  6. የክልሉን ፕሬዚዳንትና ሌሎች ‎በህዛባዊ ወገንተኝነታቸው የሚታወቁ‬ የብአዴን አመራር ‎አባላትን‬ ካልታሰበ የህወሐት አፈናና እገታ ሊታደግ የሚችል ጥበቃ‬ እንዲደረግላቸው አስፈላጊው የሰው ሃይልና የፋይናንስ ምደባ እንዲረግ መወሰን። ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ፣ የክልሉን ልዩ ሃይል የጥበቃ አቅም ማጎልበት፣ አስፈላጊውን ሥልጠናና ትጥቅ እንዲያገኙ መወሰን፣
  7. የክልሉ ‎ህዝብ ነቅቶ ለመብቱ‬ ቀናኢ ሆኖ ዘብ ‎እንዲቆምና‬ በእለት ተእለት ህይወቱ አዛዣና ናዛዥ መሆኑ እንዲሰማው፣ ባለፉት 25 አመታት ተግባራዊ ሲደረጉ የቆዩትን ከህወሐት የተወረሱ የአፈና አሰራሮች ለማጥፋት በክልሉ ሸንጎ ላይ ለህዝቡ ቃል መግባት
  8. ብአዴን የሚመራው ክልል ተነጥሎ እንዳይቆምና፣ ህወሐት ሌሎቹን ክልሎች ይዞ እንዳያጠቃው፣ ሌሎቹን ክልሎችም የሚመሩት አባላት የቀድሞ የኢህዴን አባላት እንደነበሩ በማስታወስ፣ በተለይ የኦሮሚያ ክልል አስተዳዳሪዎች ለተመሳሳይ አላማ እንዲቆሙ የወንድማማችነት ግንኙነት መፍጠር፣ የትግል ህብረትን ማጠናከር
  9. በአንዳንድ ቦዘኔዎች ወይም በራሱ በህወሐት ሰርጎ ገቦች ‎በትግራዋዮች‬ ላይ የተናጠል ዘር ተኮር ‎እርምጃ እንዳይኖር‬ ነቅቶ መጠበቅ፣ አዝማሚያው በታየበት ሁኔታ ሁሉ እርምጃ መውሰድ፣

እነዚህንና መሰል እርምጃዎችን በመውሰድ የብአዴን አመራር የራሱን አንገት ከተሳለለት ቢላዋ ከማዳን አልፎ፣ ያለምንም ድርጅትና አመራር ጭቆና ስላስመረረው ብቻ እምቢ ለመብቴ ብሎ ለመስዋእትነት የተሰለፈውን የክልሉን ህዝብ ከእልቂት ከማዳንም አልፎ፣ ኢህአዴግ ራሱ የመፍትሄው አካል የሚሆንበትን እድል ሊከፍት ይችል ይመስለኛል።

ይህን ማድረግ አቅቶት ግን የብአዴን አመራር ካመነታ፣ ሳያታሰብ እንደ መብረቅ ብልጭ የሚለው የወያኔ ሰይፍ አናቱን ሊጨፈልቀው ይችላል። ‎ለብአዴን መሪዎች ግልፅ ሊሆንላቸው የሚገባው ነገር፣ ‎ወያኔ ከውልደቱ እስከዛሬ‬ም ድረስ የብዙ ድርጅቶችን አመራርን ደም እየጠጣ ያደገ የተመነደገ ድርጅት ነው።

በጥቅምት 1968 ዘገብላ በተባለ ቦታ ቲ ኤል ኤፍ የተሰኘውን የትግራይ ነፃ አውጪ ድርጅት አመራር አባላት “ኑ ድርጅታዊ ውህደት እንፈፅም” ብሎ ከተሰበሰቡ በኋላ እዚያው አፍኖ በመግደል ደም ከጠጣ ጀምሮ በደም አበላ እንደተዘፈቀ የኖረ ሀይል ነው። የብአዴን አመራርም ደም የመጨረሻው አይሆንም። እንግዲህ ‎ግማሽ እርግዝና የለም‬። የክልላችሁ ህዝብ ሁኔታ ኣሳዝኗችሁ መጠነኛ ወገንተኝነት በማሳየታችሁ፣ በወያኔ የተዘጋጀላችሁ መልስ እርድ መሆኑ ይፋ ተደርጓል። ባለፉት 25 አመታት እንደታዘብኩት ‎ወያኔ አንድ እርምጃ ከመውሰዱ በፊት ትግራይ ኦንላይንና አይጋ ፎረም በተባሉ አፈቀላጤዎቹ መድረክ ለፈረንጆቹ የሚሆን መረጃ መሰል ትንተና በእንግሊዘኛ ይፅፋል፣ ከዚያ በቀናት ውስጥ የማያዳግም እርምጃ ይወስዳል።

አይጋ ላይ የወጣውን የመቐለ ፅሁፍ አንብቤ ይህን ምላሽ ስፅፍ ማምሸቴ የብአዴን ወገኖቼ እጣ ስላሳሰበኝ ነው። ከህዝብ ጎን ስለቆሙ ለምን ይታረዳሉ በማለት። የብአዴን መሪዎች ዛሬ ለሚገኙበት ህዝባዊ ወገንተኝነትና በመቐለ ቤተመንግስት ለተሳለላቸው የእርድ ካራ፣ ባለፉት 25 አመታት ተስፋ ባለመቁረጥ አንድ ቀን ከህዝባችሁ ጎን እንደምትቆሙ የተመሰረታችሁበትን ህዝባዊ መሰረት እንደ ተስፋ መልህቅ በመያዝ፣ “እኔ የማውቃቸው የኢህዴን ልጆች ለጠባብ ብሄርተኝነት እጃቸውን አይሰጡም” በማለት በስደት ስመሰክርና ስከራከር ቆይቻለሁ። የጎንደር ህዝባዊ እምቢተኝነት ላይ ከወያኔ ጋር ተዳብላችሁ ሳትወገዙ፣ የናንተም ልዩ ሀይል በህዝቡ ላይ ሳይተኩስ አብራችሁ ቆማችሁ ሳይ የተሰማኝን እርካታ በቃላት የምገልፀው አይደለም። ሞትን አሸንፋችሁ እንደተነሳችሁ ያህል ነው የተሰማኝ። አሁንም የተጣለባችሁን ጋሬጣ አልፋችሁ በዓይነ ስጋ ለመተያየት ያብቃን። ከህዝቡ ጎን ቆማችሁ ሰማእት ብትሆኑም፣ ስማችሁ ከመቃብር በላይ ይውላል። ተጭበርብራችሁ ግን የወያኔ እርድ ካራ ስር እንዳትወድቁ አደራዬ ጥልቅ ነው። ከክፉ ይሰውራችሁ።

38 Comments on “አስቸኳይ መልዕክት! ይድረስ ለብአዴ‬ን አመራር (ያሬድ ጥበቡ)”

  1. Hi this is timely arice and exactly the same as ” Le Mesa
    Yasebunen kurs adergnavhew”
    so BADEN should act before
    It is late.

  2. Hey, nice article! Try to write more in this issues. It is known that TPLF we try to divide the leaders so tell them as a friend don’t give them a chance!!! God bless Ethiopia we were grat people and soon we will get our stand!!!

  3. በብአዴን ውስጥ ተሰግስገው ‎ለህወሐት የሚሰልሉ‬ እንደ ካሳ ተክለብርሀን፣ ታደሰ ካሳ፣ አለምነው መኮንን ወዘተ የመሳሰሉትን የአመራር አባላት ከአባልነታቸው ማገድና ካስፈለገም ወደ እናት ድርጅታቸው ህወሐት እንዲመለሱ ፈቅዶ ‎ማሰናበት

  4. ” በጥቅምት 1968 ዘገብላ በተባለ ቦታ ቲ ኤል ኤፍ የተሰኘውን የትግራይ ነፃ አውጪ ድርጅት አመራር አባላት “ኑ ድርጅታዊ ውህደት እንፈፅም” ብሎ ከተሰበሰቡ በኋላ እዚያው አፍኖ በመግደል ደም ከጠጣ ጀምሮ በደም አበላ እንደተዘፈቀ የኖረ ሀይል ነው። የብአዴን አመራርም ደም የመጨረሻው አይሆንም። እንግዲህ ‎ግማሽ እርግዝና የለም‬። የክልላችሁ ህዝብ ሁኔታ ኣሳዝኗችሁ መጠነኛ ወገንተኝነት በማሳየታችሁ፣ በወያኔ የተዘጋጀላችሁ መልስ እርድ መሆኑ ይፋ ተደርጓል። ባለፉት 25 አመታት እንደታዘብኩት ‎ወያኔ አንድ እርምጃ ከመውሰዱ በፊት ትግራይ ኦንላይንና አይጋ ፎረም በተባሉ አፈቀላጤዎቹ መድረክ ለፈረንጆቹ የሚሆን መረጃ መሰል ትንተና በእንግሊዘኛ ይፅፋል፣ ከዚያ በቀናት ውስጥ የማያዳግም እርምጃ ይወስዳል። ”

    This is a great advice.

  5. The ANDM people must know if their lives are threatened now by TPLF and what they have to do to protect themselves.

    The TPLF controls the military and Dehninet.

    If ANDM members feel their lives are threatened they need an armed force loyal to them but not to TPLF.

  6. If their lives are threatened by TPLF as the author says, then they have to take determined actions fast. They should not lose time.
    But we have to consider here that the ferenjis are monitoring TPLF, so TPLF might need their permission before taking actions.

  7. የነብር ጅራት አለመያዝ ከያዙ አለመልቀቅ አስከ መጨረሻው ታግሎ(መስዋትንት ከፍሎ ስው በላውን መንግስት ጥሎ) ስልጣን ለህዝብ “ማስረከብ”።
    እግዚአብሔር ይርዳችሁ።

  8. ኢትዮጵያዊ መልኩን ነብር ዥንጉርጉርነቱን ወያኔ እባብነቱን አይቀይርም

    What a famous American Jew named Harold Rosenthal said about Ethiopians in his most revealing and shocking interview with Walter White is quoted below.
    “It’s stupid—stupid. We are what we are! No matter what we join or adopt it doesn’t change what we ARE. I am a Jew and nothing can change me because I take up another religion. Such stupidity! (This concept is verified in Scripture by the rhetorical question: “Can the Ethiopian change his skin, or the leopard his spots?” And in the parable of the Tares and the Wheat we find that the Tares (the children of the wicked) are utterly destroyed. None are saved from the destroying fire, none are converted into Wheat. God is not going to change the tares into something they never were).”
    Please read this revealing and shocking interview part-1 & part-2 as follows.
    SOURCE:http://www.rense.com/general66/rosen.htm

  9. ይህ የውሸት መድረክ መጨረሻው ምን ይሆን?ነጋጠባ በሬ ወለደ ወሬው ሲነዛ ራሱን ገደል ውስጥ እንደሚከት ምንም ጥርጥር የለውም።ሲፈልግ ህዝቦችን ሲያናክስ ይህ ኣልሆን ሲለው ደግሞ ኣመራር ውጥ ሰርጎ መግባት ይሞክራል። የመጨረሻ ውጤቱ ግን የከፋ ውድቀት እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለውም። የዚህ የውሸት መድረክ ተዋናዮች እነማን እንደሆኑም ድርጊታቸው ገበያ ውስጥ ኣጋልጧቸው ለፍርድ እንደሚቀርቡ ጥርጥር የለውም።

  10. Nobody knows TPLF more than Yared Tibebu, the former EPDM leader before Tamrat Layne. Better ANDEM and the AMHARA regional government leaders listen to his important advice for your survival at first, and then contribute to the winner ship of the people’s struggle which will put you on the record of history. The Amhara and the Oromo people are asking and dying for their exclusive right, equality, fair distribution of wealth in the country, equal opportunity for all citizens, self administration and freedom, no subjugation by a minority regime that took the country to a path of bloodshed and civil war, amassing the wealth of Ethiopia in few hands that came from Tigrai. The regime is changed itself to a colonialist mindset and completely engaged into intrigue politics. It is pushing and propagating the people to indulge into the Rwandan style civil strife. Its media outlets and supporters like Tigrai Online and Aigaforum are actively and keenly playing the role of” Radio Mille Collines (RTLMC). If you read what they are posting the last few weeks in the name of opinion and articles, they resorted to hate and calling the TPLF government to take any and every measure on the people asking their rights peacefully, to the extent of even exercising seceding Tigrai from Ethiopia. Irresponsibility lies much in the few running the so called “Federal Government”. Power is in the hands of the ignorant and we don’t see recognition of the dangerous problem the country is leading into nor any initiative for peaceful transition. It seems darkness and deaf ear prevails.
    This is the time for ANDEM, OPDO cadres and party/government officials to decide-stand with the people or remain servants of the die-harders. They have no time left. The train is about to leave to its destination. No dictatorship is surviving long killing this number of innocent people. How many number of people dies, the struggle intensifies and does not stop before removing dictatorship and the divide and rule politics.

    Again, better listen to Yared’s advice and exercise immediately the ANDEM cadres and the AMHARA Regional Council members. Demand as to why the TPLF involves into the affairs of kilils while the constitution clearly stipulates and forbids that. Why is the Federal Police or the Tigrai Army came into the AMHARA Kilil without the knowledge of the Kilil People’s Council or the Executive branch to take individuals hostage? “The Federal government” has no right to jump into the affairs and administration of Killils. Why is the “Federal Government” is violating the constitution of the country and demands the respect of it when it comes to others, and by citizens.

  11. ምህረት፦ አንትን ብሎ መካሪ እንስሳ ነህ ወራዳ ባለጌ እንዳንተ አይነቱ ወፍ ዘራሽ ነው ወገኖቻቸውና አገራቸውን የሚወዱትን ትግሬዎችን ከወንድሞቻቸው የሚያቃቅር ወሮበላ ባለጌ።

  12. አቶ ያሬድ ጥበቡ ላስተላለፉት እጅግ አስቸኳይና ጠቃሚ መረጃ ላመሰግናቸው እወዳለሁ። የዜግነት ግዴታ መወጣት ማለት ይህ ነው። አሁን ሁሉም ነገር ገሃድ ስለወጣ እውነተኛ የአማራ ልጆች ከአብራኩ ከወጡት ከህዝባቸው ጎን መቆሚያቸው ጊዜ አሁን ነው። አለመስዋዕትነት ድል ስለሌለ እያንዳዷ ለነፃነት የምትረጭ ፍንጣቂ ደም የድል ማብሰሪያ ጎርፍ ውስጥ የምትጠቃለል እንጅ መና የምትቀር አይደለችም። አማራው መሬቱን ከህወሃት ካጸዳ በኋላ የራሱን መሬት በእሳሱ ልጆች የሚያስተዳድርበት ስራዎች በቀጣይነት ይከናወናሉ ማለት ነው።

  13. Nothing surprises me…….the Nazi’s were also praising themselves by murdering 6 million jews in the gas chamber and tried to control the whole of Europe. Minority Tigray zombies didn’t learn from history. They are exactly doing what Hitler did immediately before the 2nd world war. Before Hitler and his xenophobic followers murdered 6 million jews, they expanded German’s territory by desolving the treaty of versales and control the sar coal regine of France. Germany also controlled the suditan land of chekoslovakia by claiming the suditan land people are German speakers. And finally, the Nazis’ blamed the jews for all their past failers. When we compare and contrast the Nazis to that of Tigray fascism, they are exactly the same. Tigray fascism is a direct coppy of German Nazis play book. Look: German Nazis control the suditan land using the pretext of “speaking the German language”, Tigray minority fascists control all historical Amhara lands from Gonder and wello using the pretext of ” speaking Tigregna language”. The German Nazis blamed the jews people for every economic problem the Germans face during the time and use this false propaganda to murder 6 million jews. Tigray fascists blame the Amharas for every problem including natural problems and hence developed a propaganda to systematically murder 2.5 million Amharas. The only difference between the German Nazis and Tigray Nazis is that: German Nazis committed genocide against the minority where as Tigray fascism is commingling genocide against the majority Amharas.
    Top

  14. ሀሳብህ አደጋ አለው አንተ ያልከውን ተግባራዊ ቢያደርጉ በማግስቱ እጣቸው እስር ቤት ነው። ወያኔዎች ሁሉ ነገር በእጃው ነው ገንዘቡም መሳሪያውም።መሆን ያለበት አሁን ወያኔ እርምጃ ሳይወስድባቸው ህዝቡ ትጥቁን እንዳይፈታ በውስጥ መቀስቀስ፣በተቻለ መጠን መሳሪያ ካለ በውስጥ በፍጥነት ማሰራጨት፣ህዝቡም ለወያኔ በመሰለል ህዝቡን የሚያሰቃዩ ባንዳወች ላይ እርምጃ እንዲወስድ ማድረግ ተገቢ ይመስለኛ።በአንድ ጊዜ ወደ ጫፍ መሄድ የኦነግን ስህተት መድገም ይሆናል። አሁን ባለው ሁኔታ ፍትጊያው መቀጠል አለበት።ወደፊት ምን እንደሚከሰት የሚያውቀው እግዚአብሄር ብቻ ነው። የወደፊቷ ኢትዮጵያ እጣ ማንም አያውቀውም የአማራና ኦሮሞው ትብብር በጣም ቢያስደስትም በሁለቱ ታላላቅ ህዝቦች በተቃውሞ ወቅት ከፍ የሚያደርጓቸው ሁለት የተለያየዩ ሰንደቅ አላማዎች መሆናቸው ሀገሪቷ ወደፊት ምን እንደምትሆን ለማወቅ ከባድ ነው። ሀገሪቷ ያለችው በእግዚአብሄር እጅ ነው መጨረሻዋን የሚያውቅ እሱ ብቻ ነው። በአንድ ነገር እስማማለሁ ወያኔ ከሚቀጥል ሀገሪቷ መጥፋት ካለባት እንኳን ብትጠፋ እመርጣለሁ። ወያኔን ከምን ጋር ልናወዳድረው እንችላለን?ከሁሉም ክፉ ነገሮች ይበልጣል።

  15. But this is accepting tribalism and killils that were imposed on Ethiopians and were rejected by Ethiopians 11 years ago in an election =========> ” Demand as to why the TPLF involves into the affairs of kilils while the constitution clearly stipulates and forbids that. Why is the Federal Police or the Tigrai Army came into the AMHARA Kilil without the knowledge of the Kilil People’s Council or the Executive branch to take individuals hostage? “The Federal government” has no right to jump into the affairs and administration of Killils. Why is the “Federal Government” is violating the constitution of the country and demands the respect of it when it comes to others, and by citizens. ”

    We should never accept tribalism and klils and have to keep Ethiopia united !

    Warning people, CIA and other agents could be here.

  16. ፍቅር ለኢትዮጵያ could you be an ERITREAN ?

    This is totally unacceptable =========> በአንድ ነገር እስማማለሁ ወያኔ ከሚቀጥል ሀገሪቷ መጥፋት ካለባት እንኳን ብትጠፋ እመርጣለሁ። ወያኔን ከምን ጋር ልናወዳድረው እንችላለን?
    ከሁሉም ክፉ ነገሮች ይበልጣል።

    Warning people, CIA and other agents could be here !

  17. Yared Tibebu,

    You live freely in the US without anybody asking what “Gosa” or “Zer” you come from. And yet, you advocate Ethiopians to live as Amhara, Oromo, Tigre, Guragie, etc instead of free Ethiopians. What a hypocrisy!

    You are one of the architects of TPLF’s failed ethnic federalism that is designed mainly to keep the TPLF leaders in power forever. Ethiopians don’t want your quota system of democracy (34%, 26%, blah, blah) and what we want is to exercise our freedom as human beings not as Amhara, Oromo, Tigre, etc. The overwhelming majority of Ethiopians trace their roots to more than two nationalities within Ethiopia and your idea that we are either Amhara, Oromo, Tigre, etc. is flawed and is the main cause of the current chaos in our country. Give people the right to vote freely as human beings and you will see the result. Don’t underestimate the ability of individuals to make choices for themselves.

    America kuch bilewu benetsanet zerina gosa sayiteyeku eyenoru Ethiopia yalewun sewun be gosa tekefafelu malet min yemilut stupidity newu?

  18. ማርም ሲበዛ ይመራል እንኩዋንስ የወያኔ አገዛዝ:: ብዙ የህውሃት ደጋፊ የነበርን በዚህ ሳምንት ወደ ህዝቡ ትግል ደጋፊ ለመሆን ወስነናል:: በባህር ዳር ከተማ በሚገኝ አንድ የመከላከያ ካምፕ ውስጥ ሰኞ በጸጥታ ሃይሎች መካከል በተፈጠረ የእርስ በዕርስ ግጭት በትንሹ አራት ህውሃት ደጋፊ አባላት መገደላቸውን በከተማዋ አለመረጋጋት መኖሩን የተናገሩት ምክንያቱ “ጠው ጠው አንልም!!” ታወቀ :: በወታደራዊ ካምፑ ውስጥ በተፈጠረ የተኩስ ልውውጥ አባላቱ ሊገደሉ መቻላቸውንና ድርጊቱ አዲስ “ጠው ጠው አንልም!!” ማንገሱን ታውቋል።

    በሳምንቱ መገባደጃ በባህር ዳር ከተማ የተካሄደውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ እስከ ማክሰኞ ድረስ የግልም ሆነ የመንግስት አገልግሎት መስጫ ተቋማት ስራ አለመጀመራቸው ታውቋል።
    የመንግስት ባለስልጣናት ነዋሪው መደበኛ እንቅስቃሴውን እንዲቀጥል በማግባባት ላይ ቢሆኑም የከተማዋ ነዋሪዎች የተለያዩ ተቃውሞዎችን በማሰማት ትዕዛዙን ተግባራዊ አለማድረጉን በተመሳሳይ ሁኔታ በጎንደር ከተማ የአገልግሎት መስጫ ተቋማት ስራቸውን ያልጀመሩ ሲሆን፣ የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ጨለማን ተገን በማድረግ ነዋሪዎችን በማሰር ላይ መሆናቸውን ለመረዳት ተችሏል።

    የሃይማኖት አባቶችን ጨምሮ የዞንና የቀበሌ አስተዳደሮች ነዋሪው የዕለት ተዕለት ‘ጠው ጠው አንልም!!” እንቅስቃሴውን እንዳይቀጥል በማግባባት ላይ ቢሆኑም ነዋሪዎች የተለያዩ ጥያቄዎችን በማንሳት ጥሪውን እንዳልተቀበሉ ተገልጸዋል።

  19. Writing on FB is easier but giving your life for change is very hard so those of Oromo and Amhara living in diaspora instead of writing on FB do this and that you have to help your people financially and arrange demonstrations supporting the revolution because you can’t clap with one hand.

  20. Anchi leba ashqabach weyane….kenish dersoal yene megbiya qedada yeleshm….kelay shabiya ketach welo kegon Gonder ende sandwich bechachkew new yemibelush maferiya

  21. To so called “Mihiret”. Your comments and your name are at the opposite side of reality. Your mother is not wise to call you ” Mihret”. She should have named you terrorist because you are a terrorist in slaved by the TPLF/Woyane thugs. You and your family must be ashamed of your actions. No Ethiopian of right mind will listen to your hateful words. The wheels of liberation for rule of laws, democratic governance, respect for citizens, real leadership and progress is now at full speed and nothing can stop it.

  22. ታጋይ ያሬድ ጥበቡ፤
    መጥፎ መካሪ ምን ያስደርጋል ነው የሚባለው፤
    ያንተን ምክር ሰምተው ቢከተሉ ምን እንደሚከተላቸው ያውቁታል፤ የራሳቸውን መውጫ አዘጋጅተዋል።
    አንድ የጦር መሪ በስሩ ያሉትን ወታደሮች ምን ማድረግ እንዳለባቸው ቀድሞ ነው በቅደም ተከተል የሚያስረዳቸው እንጅ ዉጊያ ውስጥ ከገቡ በኋላ አይደለም።
    ቀሽም ነህ፥ ይህንን ምክር መንገር የነበረብህ መጀመሪያ ነው። አሁንማ ጅብ ከሄደ ዉሻ ጮኸ ነው የሆነው። ያንተ ምክር፣ የተስፋ መቁረጥና እጅ መስጠት ምክር ቦታ የለዉም። ኃላፊነት የጎደለው ምክር፥ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል።
    ባለህበት አገር ጡረታህን እየበላህ በሰላም ኑር፥ በረሃ እያለህ ልትበትን ሞክረህ ያልተሳካልህ አሁን ባንዳንድ ሙሰኞች ተንተርሰህ ገብተህ ልታፈርሰን ይመስልሃል?
    የነብርን ጅራት አለመያዝ፥ ከያዙም አይለቁትም።

  23. This time is a learning curve for all concerned. Regional division is dangerous for a country as diversified as our nation. The Tigreans are secretly manipulating tactical politics to divide in to the route. Every Tigre is a member of Weyane. Every Tigre living or working in other regions are purposely sent to serve their troublesome party. No Tigre was or is or will be killed by the party. Ethinic-based party lies on the specific group. No demonstration in Tigray suggests the truth. Ashamed of it b/c of the cooperation.

  24. Ethnic Federalism is putting Ethiopia in the wrong path. Those who would like to have strong Ethiopia can do their best, and it is not late.
    This can be done by systematic transition of the government without extra blood shed. God help your country and save your people. Those who you think that history will remind you badly please save the people from extra blood shed. May God be with his people!!!

  25. ለ25 ዓመታት ያማራ ክልል መንግስት ነኝ
    ያለው በአዴን እና የኦሮሞ ክልል መንግስት
    ነኝ ባዩ ኦሆድድ ሁለቱም ለወያኔ የጭን ገረድ ሆነው ሕዝብን አስጨርሰዋል
    የታሪክ ማፈርያወች ህዝባቸውን የሸጥ
    በቁም የሞቱ እፉኝቶች ናቸው

  26. Yared, what a wicked person you are? you are living in a very peace full environment enjoying your life, but you are adding a gasoline in to the flame already created by selfish individuals like your self. The vast majority people in Ethiopia are working hard to elevate our country to the next stage of development. Please live our country to us who are working day and night to make change and bring prosperity to all. If you are positive thinker to your country why you did not fight instead of retreating and Running from the strangle.

  27. @ Ethio,

    i think you are aware why tribalism and killilism were imposed on Ethiopians.

    Not to liberate “oppressed tribes” but to dismantle the ancient African country in the interest of ferenjis, also arabs.

  28. የመጨረሻው ሰዓት የዳግም አድዎ ዘመቻ ጥሪ ፣ ቁጥር 21 አሰቸኳይ አዋጅ ( Very Urgent last Call for all oposition party’s to come up under one umberella of great Adowa re-union freedom movement to save Ethiopia first!!!) አገር አድን አዋጅ የ24 ሰዓት መረ ጃ ትእዛዝ በኢሳት ሬድዮ ደረጃውን ከፍ አርጎ ያስተላለፈል። ኢሳትን፣ ግንቦት 7 ፣ የአቶ ኦባንግን ድርጅት ተስፈዎቻችን ናቸው ና እባካቹ እርዱ!ለሁሉም ድርጅቶች እና ኢትዮጵያዊ በሙሉ ኢትዮጵያን የማዳን ጥሪ ዛሬ ነው። እንደ ቋንቋው ሁሉም በአገሩ ተከባብሮ የሚኖርባት ኢትዮጵያን ዛሬ ማዳን ያለብን ግዜ ላይ ነን። አዎጅ፣ አዋጅ ፣ አዋጅ ኢትዮጵያዊ ነኝ የምትሉ በትርጓሜው መጠሪያ ከእግዚአብሔር የወርቅ ስጦታ ተብለህ የምትጠራ። አረንጓዴ፣ ብጫ፣ቀይ ቀስተ ደመና ህቡር መለያህ፣ የጋኔኖች ኮከብ በሌለው ባንዲራ በአንድነት የምትጠራ። ከአለም በፈት ክርስትናን ተቀብለህ የወንድሞችህን የምትኮራበትን መስሊም እምነት አሰጠልለህ ዛሬ ለአለም የበረከትክ በአንድነት ተነስ።
    ወልቃይት ጎንደሬው፣ ጎጃም በላይ ዘለቀ፣ ወሎ እራስ ሚካኤል፣ ኦሮሚያ የስንቱ ደም የእነ አብዲሳ አጋ፣ ባልቻ አባነፍሶ፣ደቡቡ፣ሱማሌው፣ ጋምቤላው ተነስ መቼ? ዛሬ የጎበዝ አላቃ መርጠፍ በፈጣሪ ስም ተማምነህ ቀጥል ምሳሌ ተከተሉ የ ኮለኔል ደመቀ አርእያ ወልቃይት የጎንደር አማራ ኢትዮጵያዊ ፈለግ ተከተሉ። ሆዳሞችን ጠራርገህ አውጣ ፓሊሶች ከህዝብ ጋር ተባበሩ የመጣውን ፌደራል ከህዝቡ ጋር መክት፣ ትእዛዝ አስመጭዎችን ቀድመህ ቅለበቸው።
    1ኛ ፓርለማው በአስቸኳይ ተሰብስቦ ስልጣኑን እንዲያሰረክብ እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2008 ጊዜ እንስጣለን።
    2ኛ ይህ ባይሆን ቢቀር ግን የትግራይ ነፃ አውጭ ቡድን አሁን የባለሥልጣኖችን ከትግራይ ህዝብ ትከሻ ለማውረድ ሲል በአስቸኳይ ከትግራይ እና አዲስ አበባ ወስጥ እየስራ ነው። በትግራይ ማህበረሰብ ውስጥ በአገር እና ውጭ ገብተው ስለላውን ጨርሰው በአጭሩ የመከራ ግዜውን ለማሳጠር ከጠበቂዎቻቸው ጋር እየተደራደሩ ይገኛሉ።
    3ኛ መስከረም 30 ቀን 2009 አዲሱ የሽግግር መንግሱቱ ፔሬዝዳንት በመሰቀል አደባባይ ንግግር ታሪካዊ ንግግር የረጋሉ።
    4ኛ የሐይማኖት አባቶች እስስቶች ስለሆኑ እንዳትዘናጉ፣ የስው ደም እያፈሰሱ እና እስር ቤት እያሰቃዩ ስልጣን ላይ መቆየት ከቶም አይቻልም። 5ኛ የሚቀጥለው ላይ ህዝቡ በሰሜን፣ደቡብ፣ምዕራብ፣ምሥራቅ በእኩል ይወጣል።ከሽግግር በፈት እና በኋላ በውዱ አቶ ኦባንግ ሜቶ በኩል ይተላለፈል። ህዝባችን ጨዎነት በተሞላ መልክ ትእዛዝ ተቀብላቹ ከሽግግሩ ሰላማዊ አስተዎፃኦ እንደታደረረጉ እናሳስባለን። ህዝባችን በሽግግር መንግስት ፔሬዝዳንት በደ/ር ብርሐኑ ነጋ እና ጦሩ በሙሉ በጄ/ር ከማል ገልቹ እና የትግራይ ነፃ አውጭ ጥምረት ይመራል። ከአምስት አመት በኋላ ህዝቡ በመረጠው እና ሁሉንም ኢትዮጵያዊውን በአንድ አይን ማየት በሚችል መሪ ይተካል።
    ውርደት ሞት ለ ሆዳም 1000 ለአደዎ፣ ወቅሮ ሐዲጊዎች ወያኔዎች ኢትዮጵያን ታላቅ መሆኗን ሳያቋት ፣ ከአልበሽር ጋር ተባብረው በኢትዮጵያና እና በኤርትራ ህዝብ አና መሪዎች ላይ መስሪይ መርዝ በ$42 ሚሊዮን ጉርሻ የረጫቹ ሞት ለእናንተ! ኢትዮጵያ ከሁሉም በፈት እግዚአብሔር አላት ቀጥሎም ጀግኖችም ኢትዮጵያዊያን በአመራ፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብ፣ በሱማሌ፣ በአፋር፣ በጋምቤላ ዛሬም ነገም አላት!!!
    ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ፣ ከእግዚአብሔር እርዳታ ጋር!
    ንጉሡ ሞቱማ የኦሮሞ ኢትዮጵያዊያን ማሕበር የአምቦ ዋና የለውጥ ኮር አስተባባሪ እና አዛዥ።

  29. እነ ቅዱሳን ነጋ ምሳ ሶበሉ ሰሞኑን ያሉት” ወንዶቹ መጠጥ ማታ ሲጠጡ እቅድ አውጥተው ሰሞኑን ያስገድላሉ፣ እስርቤት የሰቃያሉ”
    እነሱ እርስ በእርስ ወይን ይጨራረሳሉ ዉይም ሌላው ይጨርሳቸዋል። መጨረሻ ሰሞኑን እረፈት ብለው ሚስቶቻቸውን፣ልጆች ላኩ፣ እነሱ መወጫ ያዘጋጃሉ እኛ ላይ ነው መከራው ያለው። ብለው አርስ በእረስ ያወሩ ነበር።

  30. ጥበቡ፥
    የከሰረ ነጋዴ የድሮ መዛግብቶቹን ከኣቧራ ኣንስቶ ይመረምራል ይባላል። ለሃገሪቷ ኣታስብላትም እንዴ። እንዲሁ እንድ ጥሬ ስጋ መብላትና ኣርቄ መጠጣት ቀላል ይመስልሃል? ይገርማል የእውቀት ድህነት። በል ያሬድ እንግዲስ ምን ይደረግ። በእጅ ያለው ወርቅ እንደመዳብ ይቆጠራል ይባላል። እዛው ኣገርህ መኖር ይሻልህ ነበር። ሃገሪትዋ ከ25 በፊት እንዴት እንደነበረች ኣሁን ዬት እንደደረሰች ህልናንህን ብደምብ ያውቃል። ለወደፊቱ 20 ዓመት ቢጨመር እንዴት ትሆናለች ብታስብ ኖሮ ይሄ ዬኪሳራ ጽሑፍ (ታብሎይድ) ኣትጽፍም ነበር። በማንኛውም መስፈርት ያለው ሁኔታና የተግባር እውነታ ራሱ ምስክር ነው። ይሄው የኣስክፊው የዘመናዊ ባርነት ኑሮና ውርደት እዚሁ ውጭ ሃገር እየኖርክ ይህን መጻፍክን ዬሚጠበቅ ነው። ያው ዬዬቀኑ ጭንቀትና ሰብኣዊነት ዬሚፈታተን ገድል መጋፈጥ ነው። ምን ይደረግ ኣምላክ ወገን ነህና ኣምላክ ያቅናልህ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*