ድፍን የቀድሞ የቤገምድር ክፍለ ሃገር በጦርነት ላይ ነው
ይህ ህዝብ ባህር ነው ሲወድህ ለጥ ይልልሀል ሲነሳብህ ግን ማእበል ሁኖ ይውጥሀል። ነጻ ሆነን ተፈጥረናል ነጻነታችንም ይታወጃል! በደቡብ ጎንደር ዞን በጋይንት እና በደብረ ታቦርም ከህወሓት ጋር ፍልሚያው እንደቀጠለ ነው። ጋይንት ላይ መምህር መላክ ታደሰ የተባለ ኢትዮጵያዊ ሕይወቱ አልፏል።
ሰሜን_ጎንደር ዞን አለፋ ጣቁሳ ወረዳ ከህወሓት ጦር ጋር ጦርነት እዬተካሄደ ነው። ሻውራ እና ደልጊ ዜጎንች ተሰውተዋል። በተመሳሳይ የብዙ የሕወሃት ታጣቂዎችም እንደተገደሉ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
በመላው የአማራ ክልል ተቃዉሞውና ዉጊያው እየተቀጣጠለ ነው። ማሩ ቀመስ ደንቢያ ሕዝቡ በአገዛዙ ላይ ጦርነት አውጇል። ቆላድባ ላይ የጦር ግምጃ ቤት ተዘርፎ ህዝቡ ጦር መሳሪያ ተከፋፍሏል ተብሏል። የአርማጭሆ እና ጠገዴ ሰዎች ሰሮቃ፣ ሙሴ ባንብ ፣ ሳንጃ ላይ የቀለጠ ጦርነት እያካሄዱ ይገኛሉ።
ወገራ (ዳባት ደባርቅ እና አካባቢያቸው) በሕወሓት ላይ ጦርነት ከፍተዋል። ወረታ እና አዲስ ዘመን እንዲሁም በለሳ የ#አማራ_ተጋድሎን ተቀላቅለዋል። ከፍተኛ ጦርነት ላይ ናቸው። ቋራ እና መተማም አፈሙዙን በወያኔ ላይ አዙሯል። ስልክ እና ኢንተርኔት ሙሉ ለሙሉ መዘጋቱ የአማራ ተጋድሎን መረጃዎች ለመለዋወጥ ከፍተኛ እክል ገጥሞናል።
#የአማራ_ተጋድሎ ይቀጥላል