በባህር ዳር በጎንደር ላይ ተጋድሎው ቀጥሎ ውሏል፣ ዛሬ አርማጭሆ ላይ ከፍተኛ ውጊያ እየተደረገ ነው

Gonder Bahir Dar

ዛሬ ነሐሴ 1 ቀን 2008 ዓ ም ከጎንደር ሰቲት ሁመራ መንገድ ደበዝ ላይ በኦራል ሙሉ የወኔ አጋዚ ጦር ሰራዊት ተደመሰሰ፥ 58 አጋዚ ጦር ሲሞቱ ሁለቱ ተማርከዋል፥ ጎንደር ከተማ የሰነበተው የአጋዚ ጦር በአርማጭሆ አቋርጦ ወደ ሁመራ ለመሄድ ፈረስ መግሪያ ሙሴባብ ከተማ ሲደርስ ጥቆማ የደረሰው አርሶ አደር ሕዝባዊ ሰራዊት ደበዝ ወንዝ ላይ ጠብቆ ተኩስ በመክፈት ሙሉ በሙሉ ደምስሶታል። ደበዝ በአርጭሆ ወረዳ ከጎንደር ከተማ ወደ 30 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሙሴባምብ እና ኩርቢ ከተማ መካከል የሚገኝ ወንዝ ነው። በዚህ ሰዓት ከኋላ የመጣ ሌላ ረዳት ጦር ጋር ፈረስ መግሪያና ሙሴባምብ ዙሪያ ከቦ እያሸው ይገኛል፥ ከፍተኛ ሕዝባዊ ጦር ወደ ጎንደር ከተማ እየተጠጋ ነው።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

በባህር ዳር ቀዉስ እንደ ቀጠለ ነው።የሕወሃት ጦር በሰላማዊ ህዝብ ላይ በከፈተው ተኩስ ቢያንስ ከአምሳ በላይ ወጣቶች ጥይት አግቷቸዋል። በፈለገ ህይወት እና በጋምቢ ሆስፒታሎች መተኛታቸውን ነዋሪዎች እየተነጋሩ ነው። ከጎንደር ወደ ባህር ዳር ለሰልፍ የመጣ ህዝብ አጋዚ ወደ ባህር ዳር አላስገባም በማለቱ በተጀመረው ተኩስ ብዙ ሰዎች ቆስለዋል። ባህር ዳር ነገሮች ከቁጥጥር ዉጭ ሆነዋል። ለሰዓታት ሰላማዊ የነበረውን ሰልፍ ፣ ሬንጀር የለበሱ አማርኛ የማይችሉ ታጣቂዎች ከተማዋ ከገቡ በኋላ ግን ነገሮች ከቁጥጥር ዉጭ ሆነዋል።

በርካታ የመለስ ዜናዊ ፎቶዎች ተቃጥለዋል። ወልቃይት የትግራይ ናት ብለው በሕዝብ የተሳለቁ የብ፤አዴን ከፍተኛ አመራር ቤት ተቃጥሏል። በድፍን ባህር ዳር ባለ ኮከቡ ባንዲራ ወርዶ ትክክለኛው የኢትዮጵያ ሰንድቀ ተዉለብልቧል። የቤት ሰራተኛ ሳይቀር ነው ድፍን ባኅር ዳር ነቅሎ የወጣው።